ይጎብኙንና የመኖሪያ ህልሞን እውን ያድርጉ!
3ተኛው አመታዊ የሪልስቴት ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል ታህሳስ 11 እና 12 ይጀምራል፡፡ እርሶም በዚህ ኤግዚቢሽኑ በመሳተፍ ሁሉንም የሪልስቴት አልሚዎችንና በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በአንድ ቦታ እንዲያገኙ እንዲሁም የመኖሪያ ፍላጎቶን እንዲያሟሉ አዘጋጆቹ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሳይጉላሉ ሁሉን በአንድ ጥላ በኤክስፓው ያገኛሉም ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ሀይል ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸውን 50 የአየር ወለድ አባላት አስመረቀ!
ተመራቂዎቹ በብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በከማንዶ ወታደራዊ ሙያ ሲሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን ባላቸው ብቃትና ዲሲፕሊን የአየር ወለድ ስልጠናን ለ2 ወራት ሲወስዱ ቆይተው ነው የተመረቁት።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የፈረንሳይ መከለከያ ምክትል ኢታማዦር ሹም በርናንድ ባሬር፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ የልዩ ዘመቻ ሀይል ጥብቅ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሹማ አብደታ እና ለሌች ወታደራዊ አመራሮች ተግኝተዋል።
(ኢቲቪ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተመራቂዎቹ በብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በከማንዶ ወታደራዊ ሙያ ሲሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን ባላቸው ብቃትና ዲሲፕሊን የአየር ወለድ ስልጠናን ለ2 ወራት ሲወስዱ ቆይተው ነው የተመረቁት።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የፈረንሳይ መከለከያ ምክትል ኢታማዦር ሹም በርናንድ ባሬር፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ የልዩ ዘመቻ ሀይል ጥብቅ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሹማ አብደታ እና ለሌች ወታደራዊ አመራሮች ተግኝተዋል።
(ኢቲቪ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SportsBetting
"ትንሽ ብር ከፍለው በመቶ ሺዎች ማግኘት ይችላሉ፤ በሚል ከአቋማሪዎች የሚነገረው አሳሳች ማስታወቂያ ለአገሪቱም ሆነ ለወጣቶች ጠቀሜታ የሌለው ጎጂና የነበሩ እሴቶችንና ባህሎችን የሚሸረሽር፣ ጤናማ ሕይወታቸውን አልፎም የማህበረሰቡን ኢኮኖሚ የሚጎዳ ነው። ድርጊቱ በተለያዩ የዓለም አገራት የተለመደ ቢሆንም እንደ ኢትዮጵያ ላለ ታዳጊ አገር በወጣቶች ላይም ሆነ በአገር ደረጃ ጠቀሜታ የለውም ፤ ወጣቶች የራሳቸው ገቢ ሳይኖራቸው በዚህ ተግባር ላይ መግባታቸው ለመስረቅና ተያያዥ ወንጀሎችን ለመፈጸም በር ይከፍታል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በቤተሰብ ደረጃ ሠላም እንዳይኖርና መልካም ግንኙነት እንዲሻክር በማድረግ ግጭትን እንደሚያስከትል፤ ለአገር ፀጥታም ስጋት ይሆናል። በየትኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ፈቃድ ሲሰጥ ዘርፉ ለአገሪቱ ያለው መልካም ገፀ በረከትና ጉዳት በሚገባ ሊመረመር ቢገባም ይህ ተግባራዊ ሲደረግ አይታይም።" አቶ አለሙ ሠዒድ (በሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የወጣቶች ሰብዕና ልማት ዳይሬክተር)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለፍቅር እንሩጥ፤ ጥላቻን እናምልጥ!
ሚስባህ ከድር በአሸባሪነት ተከሶ በእስር የነበረ ሲሆን በቅርብ ከተለቀቁት እስረኞች አንዱ ነው፡፡ ከእስር ከወጣም በኀላ ፍቅር ያሸንፋል የሚል የሲቪክ ማህበር አብረው ከነበሩ የእስር ጓደኞቹ ጋር አቋቁሞ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በቅርቡም "ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ" የተሰኘ የ5 ኪሜ. የጎዳና ሩጫ አዘጋጅተዋል፡፡ ዋና አላማውም የተለያየ የፓለቲካ አቋም ያላቸውን ፓለቲከኞች፣ አክቲቪስቶችና ታዋቂ ግለሰቦችን ማቀራረብ እንደሆነ በነበረን ቆይታ ገልጾልናል፡፡ በውድድሩም በሀገሪቱ ትልቁ እንጀራ ይጋገራል ይህም ሰፊ እንጀራ አለን ተካፍለን እንብላ እርስ በእርስ አንባላ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ሩጫው ጥር 17 በአዲስአበባ የሚጀምር ሲሆን በተለያዩ ከተሞችም ይቀጥላል፡፡
#TIKVAH_ETHIOPIA

ፌደራል ፖሊስ ወደዩኒቨርሲቲዎች ከገባ በኃላ ምን አይነት ለውጥ መጣ?
"መረጋጋቱ የሚታይ ቢሆንም አሁንም ተማሪዎች ላይ ያለው ስጋት የቀነሰ አይደለም። ምደባው ያስፈለገበትና ጥበቃውን ማጠናከር ያስፈለገበት በዚህ ምክንያት ነው። ጥበቃው በቅርብ ጊዜ የተጀመረ ስለሆነ ውጤቱን ለማየት እና ለመለካት ጊዜ የሚወስድ ይሆናል። በእኛ አረዳድ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በተለይ የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ሁሉንም ዜጋ በእኩል አይን አይቶ የማገልገል፤ በእኩልነት የማገልግለ ስራ ስለሚሰሩ ይሄን ችግር ይቀርፋሉ ብለን ነው የምናምነው። ፌደራል ፖሊስ የራሱ የሆነ ሃይማኖት የለውም፤ የራሱ የሆነ ብሄር የለውም ስለዚህ ተቋሙ ገለልተኛ ሆኖ ነው ሁሉንም በሚዛናዊነት እያየ ሁሉንም በእኩል የሚያገለግለው። ለዚህ ነው ልጆች ፌደራል ፖሊስ ሊጠብቀን ይገባል እያሉ ያሉት፤ የተማሪዎችም ጥያቄ የነበረውም እሱ ነው፤ በዛም መሰረት ይሄን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተባብሮ በቅንጅት ኃይሉን የማጠናከር ስራ በመስራት አሁን ካለው ሁኔታ የተሻለ ነገር ይመጣል ብለን እንጠብቃለን።" አቶ ጀይላን አብዲ (የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ)
(Sheger FM 102.1)

ዛሬ ታህሳስ 09/2012 ዓ/ም - በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተፈጥረው የነበሩ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኙ በርካታ ሳምንታት አልፈዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵዮጵያ ከቤተሰቦቻችን እንደተረዳው፦
- ባደረባቸው ስጋት ሳቢያ ግቢያቸውን ለቀው የወጡ በርካታ ተማሪዎች ዛሬም አልተመለሱ። ይህ ማለት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ከወር በላይ ተቀምጠዋል።
- በተለያዩ ግቢዎች ውስጥ የሚሰራጩና በየግድግዳው የሚለጠፉት የማስፈራሪያ እና የውጡልን፣ ትምህርት አንማርም መልዕክቶች አሁንም አልቆሙም። ዛሬም በግቢ ውስጥ ለቀሩ ተማሪዎች የማስፈራሪያ መልዕክቶች እየደረሳቸው እንደሆነ ተረድተናል።
- አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው በወጡበት የትምህርት ስርዓት የማስቀጠል ተግባር እያከናወኑ እንደሆኑ ተረድተናል። ባለፉት ቀናት ደግሞ የተጀመረው ትምህርት የተቋረጠበትም እንዳለ ሰምተናል።
- የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች (የዩኒቨርሲቲ ሴኔት) ተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ በዘለለ ይህ ነው የሚባል ለውጥ መጥቶ ሁሉም ተማሪዎች ወደ መደበኛ ትምህርታቸው የመመለስ ስራ እስከዛሬ አልተሰራም።
የ2012 ዓ/ም የመጀመሪያው አጋማሽ የትምህርት ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜ በቀረበት ሁኔታ እስከዛሬ አስተማማኝ እና ዘላቂ መፍትሄ አለመሰጠቱ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ እናምናለን። ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ከወር በላይ መቀመጣቸው ሁሉንም የሀገሪቱን ዜጎች ሊያስጨንቅና ሊያሳስብ የሚግባው ጉዳይ ነው። አሁንም መንግስት እና ሁሉም የሚመለከተው አካል፣ የሀገራችን ጉዳይ ያስስበናል የሚል በሙሉ ከዚህ በላይ ጊዜው ሳይረፍድ ችግሮች እንዲፈቱ እንዲሰሩ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን።

ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ሱፐር ኢንቴንደንት አስገለ ወልደ ጊዮርጊስ ክሳቸውን አስተባብለዋል!
ከቂሊንጦ ማረሚ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ኢሰብዓዊ ድርጊት ፈጽመዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ሱፐር ኢንቴንደንት አስገለ ወልደ ጊዮርጊስ ክሳቸውን ተቃወሙ። ተከሳሹ ሱፐር ኢንቴንደንት አስገለ የማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ደህንነት ዘርፍ የአደጋ መከላከል ኦፊሰር ነበሩ። ትላንት በዋለው ችሎት መቃወሚያቸውን ያቀረቡት በጠበቃቸው በኩል ነው።
መቃወሚያው “አቃቤ ሕግ ተጎጂ ናቸው ባላቸው ግለሰቦች ላይ ተፈፀመ ብሎ ባቀረበው የወንጀል ክስ፤ ተከሳሽ ሆን ብሎ፣ ለመጉዳት አስቦ ወንጀሉን እንደፈፀመ በማስመሰል ክስ መስርቷል፤ ነገር ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው” ይላል። የግል ተበዳይ እየተባሉ በክሱ የተጠቀሱት ሰዎች ከተከሳሹ ጋር ምንም አይነት የግል ግንኙነት የሌላቸው ናቸው ሲልም በመቃወሚያው ተጠቅሷል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-12-19-2
(ENA)

20 የሚሆኑ አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክች የጨረታ ሂደታቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል!
የአዲስ አበባ ከተማ መንዶች ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት ግንባታቸውን ለማስጀመር በዕቅድ ከያዛቸው በርካታ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል 20 የሚሆኑት የጨረታ ሂደታቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
ባለስጣኑ በተያዘው በጀት ዓመት40 የሚሆኑ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን የጨረታ ሂደታቸውን አጠናቆ ወደ ግንባታ ስራ ለማስገባት በእንቅስቃሴ ላይ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 20 የሚሆኑት የመንገድ ፕሮጀክቶች የጨረታ ሂደታቸው በመገባደድ ላይ ይገኛል፡፡ ቀሪዎቹ 20 የሚሆኑት ደግሞ በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሂደታቸው ይጀመራል፡፡
በአሁኑ ወቅት የጨረታ ስራቸው ተጠናቆ ወደ ግንባታ ይገባሉ ተብሎ ከሚጠበቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል፡-
- ከአየር ጤና -ወለቴ
- የቢ-2 ኮሊዶር የፈጣን አውቶቢስ መስመር ግንባታ
- ከአውግስተ- ወይራ መጋጠሚያ
- በሻሌ ኮንደሚኒየም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት
- ከፉሪ- ሀና ማሪያም
- ወታደር ኮንደሚኒየም ሳይት
- ቦሌ ጃክሮስ
- ንፋስ ስልክ ኢንዱስትሪ መንደር
- ቦሌ አራብሳ ኮንደሚኒየም ሳይት
- ጨሬ ኮንደሚኒየም ሳይት
- የአቃቂ ድልድይ
- ቦሌ አራብሳ እና ቦሌ ቸሪ ኮንደሚኒየም የመንገድ ዲዛይንና የግንባታ ስራ
- ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም ሳይት
- ድልድዮች
- ቦሌ አራብሳ 6ኛ መንገድ
- ቦሌ አራብሳ ሎት 11 እና በመሀል አዲስ አበባ የተለያዩ ቦታወች ላይ የሚሰሩ የመንገድ ዳር መብራቶችን ማዘመን የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
https://telegra.ph/ETH-12-19-3

#ETHIOPIA
የኢትዮጵያ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ፤ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ያስመዘገቡትን ኃብት ለማንኛዉም ዜጋ መረጃ እንደሚሰጥ አስታወቀ። ያለምን ቅድመ ሁኔታ እና ምክንያት መረጃ እንደሚሰጥ ያስታወቀዉ የፌደራል የፀረ ሙስና ኮሚሽን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ መስተዳደር ባለስልጣናት ዳተኝነት ይታይባቸዋል ሲል አስታዉቋል ። የፌደራል የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ እንደተናገሩት ነሕገ መንግሥቱ መሰረት የመንግሥት አሰራርን ለሕዝብ ግልፅ ለማድረግ ነዉ።
(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

#WNM
የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የወላይታን ክልልነት ጥያቄ ለማፈን የመከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ወደ ዞኑ እየገባ ይገኛል ብሏል ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ፡፡ በዞኑ ግጭት ቢፈጠር ተጠያቂው መንግሥት ይሆናል፡፡ ወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ለደቡብ ክልል ካቀረበ ነገ ዐመት ይሞለዋል፡፡ እናም ሕገ መንግሥቱ ባለመከበሩ መንግሥት ለወላይታ ክልልነት ባስቸኳይ ዕውቅና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡ በተያያዘ፣ ዛሬ በሶዶ ከተማ የባጃጅ ሹፌሮች ጥያቄውን በመደገፍ ሰልፍ አድርገዋል፡፡
(WazemaRadio)

በዋስትና የተለቀቁት የአቶ አብዲ ኢሌ የክስ መዝገብ ተጠርጣሪ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጠ!
ፌዴራል ፖሊስ በዋስትና የለቀቃቸውን የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር /አብዲ ኢሌ/ የክስ መዝገብ ተጠርጣሪ የሆኑትን 37ኛ ተከሳሽ እንዲያቀርብ የፌዴሬሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።
በእነ አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር የክስ መዝገብ የተጠረጠሩ ሶስት ሰዎች ዛሬ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
ፖሊስ ከዚህ በፊት በዚሁ መዝገብ ከተካተቱ 47 ተከሳሾች መካከል ይዣቸዋለሁ ያላቸው 37ኛ ተከሳሽ የስም ስሕተት በመኖሩ በዋስትና እንዲለቀቁ መደረጉን አስረድቷል።
https://telegra.ph/ETH-12-19-4

አቶ አንዱዓለም በቁጥጥር ስርዉለዋል ተባለ!
የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን በእጭሩ) ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱዓለም ታደሰ በኮማንድ ፖስቱ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ንቅናቄው አረጋግጫለሁ ብሏል። ሁኔታውን እንተከታተልኩ ነው ያለው ዎብን ዝርዝር መረጃ ለህዝብ አቅርባለሁ፤ የዎላይታ ሕዝብን ሕገመንግስታዊ ጥያቄ በኃይል ማፈን በአስቸኳይ ይቁም ሲል በፌስቡክ ገፁ መልዕክት አስተላልፏል።

#CBE
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገር አቀፍ ደረጃ 30 የሚደርሱ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎች መክፈቱን አስታወቀ። በመላ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ የባንክ ቅርንጫፎች ቁጥር 30 ማድረሱና ሌሎች ተጨማሪ ቅርንጫፎችንም በፍጥነት በመክፈት ላይ እንደሚገኝ የባንኩ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሪክተር አቶ የአብስራ ከበደ ተናግረዋል።
(EPA)

የቻይናዋ ሃንዥ ግዛት ልዑካን ቡድን ወደ መቐለ እንዳይጎዝ መከልከሉ ተሰምቷል!
የሃንዥ ግዝት ምክርቤት ምክትል ሊቀመንበር እና ልኡካቸው ወደ መቐለ ለመጓዝ ትናት ምሽት አውሮፕላን ውስጥ ነበሩ ባልታወቀ ምክንያት ከአውሮፕላን እንዲወርዱ ና ወደ መቐለ መሄድ አንደማይችሉ ተነገራቸው። በመቐለ በምክትል ርእሰ መስተዳድሩ የሚመራ ልኡክ ሊቀበላቸው አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ እየተጠባበቃቸው ነበር የልኡካን ቡድነ መቅረት ክልሉ ያወቀው አውሮፕላኑ እንደ ኣረፈ ነበር።
ከዛም ለምን እንዳልመጡ ለልኡካኑ ሲጠይቁ በማያውቁት ምክንያት ወደ መቐለ መጓዝ አንደማይችሉ እነደተነገራቸውና እንደተመለሱ ክልሉ ሰመቷል። ይህነ ተከትሎ ዶክተር አበርሃም ተከሰተ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ልኡኩ አነጋግረ የመግባብ ያሰነድ ተፈራምዋል። የሁለቱን ክልሎች ግንኙነት ያመቻቸው የፌደራል መንግስት ነበር በውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር በኩለ፤ እስከአሁን የከለከለው አካል አልታወቀም የፌደራል መንግስት ሊያሳውቀ ነይገባል ሲሉም ዶክተር አብርሃም ተናግረዋል።
በዛሬው በአዲስ አበባ ውይይት በቱሪዝም፤ በማእድን ማውጣት ና በግብርና በትበበር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስመምነት ተፈራርመዋል። ዶክተር አበርሃም እንዳሉት የፌደራል መንግስት ባለስለጣናት እንዲህ አይነት ተግባራት በተደጋጋሚ በመፈፀም የሀገሪቱን ገፅታ እያበላሹ ነው ብለዋል።
(ድምፂ ወያነ)

#ETRSS01
ነገ 21 ጊዜ መድፍ ስለሚተኮስ እንዳትደናገጡ!
በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያዋ የሆነችው ETRSS- 01 የተሰኘችው የመሬት ምልከታ ሳተላይት ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 12፡00 ሠዓት ላይ ወደ ጠፈር የምትመጥቅ ሲሆን ይህን ታሪካዊ ቀን በማስመልከት 21 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር በግልባጭ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል። በመሆኑም በሚተኮሰው መድፍ ድምፅ ህብረተሰቡ እንዳይደናገጥ ኮሚሽኑ ያስታውቃል፡፡
(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

የደቡብ ክልል ኮማንድ ፖስት-ወላይታ ዞን FormateConversion
My Recording
የደቡብ ክልል ኮማንድ ፖስት በዎላይታ ባለው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሰጥተዋል፦
ዛሬ በዎላይታ አከባቢ ያለው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ነገ ታህሳስ 10/12 ዓ ም ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ እንደማይደረግ አስተውቀዋል። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ መንገዶች ነገ ሰላማዊ ሰልፍ አለ በሚል በግለሰቦች እየተነገረ ያለው ህጋዊ ፍቃድ የለለውና ኃላፊነት የሚወስድ አካል የለለው በመሆኑ ህዝቡ የሚከተለውን መመሪያ እንዲከተል መግለጫ ተሰጥቷል።
1 - ነገ ማንም ከመደበኛ መከላከያ ሠራዊት ውጪ ማንም የሠራዊቱን ደንብ ልብስ መልበስ አይቻልም።
2 - በዎላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
3 - በዎላይታ በሁሉም ቦታ ዛሬ ማታ ከ12 :00 ጀምሮ ነገ ቀን ሙሉ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ከተማ ውስጥ ማሽከርከር በፍጹም አይቻልም።
4 - በማህበራዊ ሚዲያ ሆነ በሌላ መንገዶችም ህዝብን ለግጭትና ለሰልፍ መጥራት አይቻልም።
5 - ሥራዊቱ የህዝብን መብት ሰጪም ከልካይ ስላይደለ ህዝቡ ከሠራዊቱ ጎን መቆም እንዳለበት ተገልጿል።
6 - ነገ ህዝብ ህገመንግስታዊ መብት ጥያቄዎቻቸው በህገወጥ መንገድ ታፍኗል በሚል በዎላይታ ውስጥ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ውይይት አድረገው በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከታቸው አቤቱታ እንዲያቀርቡ ተፈቅዷል።
7 - ነገ በዎላይታ ከማለዳው ጀምሮ በሁሉም ቦታ እስከ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ እንዲቆዩ ተብሏል።
በአጠቃላይ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ሳይጋጩ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያቀርቡና ነገ በሁሉም ቦታ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል በጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
(ኮሎኔል ተስፋዬ ሀጎስ)
#WT
@tikvahethiopiaBot

የወላይታ ዞን አስተዳደር ዛሬ ማምሻውን በወቅታዊ ዞናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል!
የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ህገ-መንግሥታዊ ጥያቄ በቀበሌ ምክር ቤቶችና በወረዳና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ደረጃ ተወስኖ በመጨረሻም በዞኑ ምክር ቤት ተወስኖ በጽሑፍ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት መቅረቡን አስታውሰዋል።
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከወላይታ ዞን ምክር ቤት በህገ -መንግሥቱ መሠረት ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ አንድ ዓመት ማቆየቱ አግባብ እንዳይደለ የዞኑ ህዝብ ሲያወግዝ ቆይቷል ብለዋል።
በህዳር 30/2012 ዓ-ም የተሰበሰበው የዞኑ ምክር ቤቱ የወላይታ ብሔር በክልል የመደራጀት ህገ-መንሥታዊ ጥያቄ ዙሪያ ውክልና የተሰጠው አስፈጻሚ አካል ጥያቄው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም በሰላማዊ መንገድ መሄድ እንዳለበት ሀሳብ መስጠቱን አውስተዋል።
ምክር ቤቱ በቀሪዎቹ ቀናት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ በህገ መንግሥቱ መሠረት አቤቱታ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መቅረብ እንዳለበት አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቁመዋል።
ሰሞኑን ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ነጋዴ ማህበረሰብ፣ ፐብሊክ ሰርቫንት እንዲሁም የባጃጅ አሽከርካሪዎች ጭምር በሶዶ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የእግር ጉዞ በማድረግ የደቡብ ክልል ለወላይታ ህዝብ ጥያቄ አለመስጠቱን አውግዘዋል ብለዋል።
የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀርቦ ምላሽ ሳይሰጥ አንድ ዓመት የሞላው በመሆኑ ይህንን ለማውገዝ ህዝቡ ነገ ታህሳስ 10/2012 ዓም ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ጥያቄ ሲያቀርብ የቆየ ቢሆንም በክልሉ ኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ስላልተሰጠ ነገ ሰላማዊ ሰልፍ እንደማይካሄድ ገልጸዋል።
More👇
https://telegra.ph/WRS-12-19

#FAKE_PHOTO #ERSS01
ይሄ ዛሬ ማምሻውን 'ይህችናት ሳተላይቷ' ነገ ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት (#ERSS01) ይህቺ ናት እየተባለ ሲሰራጭ የነበረው ፎቶ ሀሰተኛ ነው። ፎቶው 2013 ላይ የተነሳ ነው። በሚግርም ሁኔታ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች ሳይቀሩ ፎቶውን ሳያጣሩ ሳያረጋግጡ ሲቀባበሉት ነበር።
ማስታወሻ፦ #ETRSS01 -- ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ ሳታላይቷን ነገ አርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዋ የምታመጥቅ ይሆናል። የቲክቫህ ቤተሰቦች ከወዲሁ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ኢትየጵያ ለመጀመርያ ግዜ የምታመጥቃት #ETRSS01 ሳተላይት ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡
ከደቂቃዎች በኃላ ወደህዋ የምትመጥቀው የኢትዮጵያ ሳተላይት ETRSS-01፦
• የሳተላይቷ ጠቅላላ ከሸብደት 72 ኪሎ ግራም ሲሆን ነገ ታሕሳስ 10 ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡
• ሳተላይቷ በተወነጨፈች በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የህዋ ጥግ ላይ የምሕዋር ቦታዋን ትይዛለች፡፡
• በኢትዮጵያና ቻይና መንግስት በጀት የተገነባችው የመረጃና ኮሙኒኬሽን ሳተላይት የምትመጥቀው ከቻይና የጠፈር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው።
• ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ ለመስጠት ነው፡፡
• የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ እንጦጦ ላይ የተሰራ ሲሆን ከማምጠቅ ስራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ እንጦጦ ላይ በኢትዮጵያውያን ይከናወናል።
• እንጦጦ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ እንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና የምርምር ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግትት ተዘጋጅቷል፡፡
• ጣቢያው የሳተላይቷን ደህንነት ክትትል የሚደረግበትና ከሳተላይቷ የሚገኙ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት ነው፡፡
(A/A City Press Secretariat Office)

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
READY FOR LAUNCH? ለምጥቀት ዝግጁ?
#ETRSS1 #ESSS #ESSTI #Ethiopia #SpaceGeneration #SatelliteLaunch
#እውንሆነ
(Ethiopian Space Science Society)