TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MekelleUniversity #MelesZenawiCampus

ኩሓ የሚገኘው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ "መለስ ዜናዊ ካምፓስ" የ2012 የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል። ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ለተማሪዎች ጥሪ ያላደረገ ሲሆን ተማሪዎች የመግቢያ ቀናቸው በይፋ እስኪገለፅ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

የሬጅስትራር ዳ/ፅ/ቤት

በ2012 የትምህርት ዘመን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፦ ወደ ዩኒቨርስቲያችን የምትመጡበት ቀን በዩኒቨርስትያችን ድረገፅ፣ በፌስቡክ እና ትዊተር እንዲሁም በሬድዩና ቴሌቪዥን እና በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገፅ በቅርቡ እስከምናሳውቃችሁ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን ለመግለፅ እንወዳለን።

የሬጅስትራር ዳ/ፅ/ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመታወቂያ ደብተርን የሚተካ ሶፍትዌር በቅርቡ አዘጋጀተዋል። «ስማርት አይዲ» የተባለዉ ማንነትን መለያ መተግበርያ ወይም application የዜጎችን ዝርዝር መረጃዎች የሚይዝ፣ የወረቀት አሰራርን የሚያስቀር እና  ሕገ ወጥ መረጃን ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡ አበልፃጊዎቹ የመቐለ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የ2011 ዓ.ም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቃን የሆኑት ኪዳነ ገብረመድህን፣ አረጋዊ ሀይለየሱስና ሌሎች ባልደረቦቻቸው ሲሆኑ ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት አልመው እንደሰሩት ተናግረዋል፡፡ሶፍትዌሩ በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የሚሰራ መሆኑም አበልፃጊዎቹ ገልፀዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ህዳር 06/2012 ዓ/ም የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ከንድያ ገ/ህይወት፣ ወ/ሮ ሊያ ካሳ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ወንድወስን አንዱሃለም የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ አካላት በተገኙበት ተመርቆ መደበኛ ስርጭቱን ጀምሯል።

(ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

2 ኛው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን መድረክ "የአልሙናይ ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ ታህሳስ 4፣ 2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ሃርመኒ ሆቴል ይካሄዳል። በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የክብር እንግዶችን ጨምሮ ከ200 በላይ ታዳሚያን እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia