TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NobelPeacePrize

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወይዘሮ ፅዮን ተክሉ ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን በማስመልከት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና በ "እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር ስም የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ - የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ! #NobelPeacePrize

#TikvahEthiopia
#NobelPeacePrize

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድርስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላፉ፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ለFBC እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የሰሯቸዉ ስራዎች ከዚህም በላይ ሊያስመሰግኗቸውና ሊያሸልሟቸው የሚችሉ በመሆናቸው ኮርተንባቸዋል ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቅ ሽልማት የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ መሆን ነው ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር በዚህም መላዉ የኢትየጵያ ህዝብ ደስ ሊለው እንደሚገባ ገልፀዋል። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ መልካም ተግባር መስራት ምን ያህል አስፈላጊና ተጽእኖ መፈጥር እንደሚችል ማሳያ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማት ያሳያል ብለዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የኖቤል የሰላም ሽልማት" በማሸነፋቸው የሀገራችንን ስም በዓለም መድረክ ከማስጠራት ባለፈ 918,000 የአሜሪካ ዶላር በገንዘብ፣ የወርቅ ሜዳልያ እንዲሁም ዲፕሎማ ይሸለማሉ!!

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በነገው ዕለት በመላ ኦሮሚያ የደስታ መግለጫ ሰልፎች የሚደረጉ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንዲኖር አድርገዋል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት በማሸነፋቻው በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ዱከም፣ ገላን፣ ሻሸመኔ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ሱሉልታ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጅማ፣ መቱ፣ በደሌ፣ ባቱ፣አዳማ፣ ጉጂ ዞን፣ ቦረና ዞን፣ እኔ ሌሎች በርካታ ከተሞች የደስታ ሰልፎች እየተደረጉ ናቸው።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች ተደርገዋል፦ ዱከም፣ ገላን፣ ሻሸመኔ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ሱሉልታ፣ ባሌ ሮቤ፣ ጅማ፣ መቱ፣ በደሌ፣ ባቱ፣አዳማ፣ ጅማ ዞን /ጌራ/፣ ድሬዳዋ፣ ቢሾፍታ፣ ሰበታ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሀረር፣ጭሮ፣አሶሳ/ቤኒሻንጉል ጉምዝ/ ደንገሃቡር/ሱማሌ ክልል/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የዓለም የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን በማስመልከት የሰላም ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡

በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚሊኒየም አዳራሽ የሚከናወነው ይህ የደስታ መግለጫ ዝግጅት እሁድ ጥቅምት 9፣2012 ዓ.ም ከቀኑ 11 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንደሚዘልቅ የሰላም ሚኒስቴር መግለጫ አስታውቋል።

Via #WaltaTV
@tsehabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #DrAbiyAhemed

"ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር"--- የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር

"የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት"--- የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም

የኖርዌይ የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኦላቭ ጆልስታድ ጠ/ሚር አብይ ከአምስት ቀን በሁዋላ ሽልማታቸውን በሚቀበሉበት ወቅት ጥያቄዎች የሚጠየቁበት ፕሮግራም ላይ እንደማይገኙ ገልፀው "ይህ በጣም ችግር ነው። ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር" ብለው ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል።

ዛሬ የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም ለAssociated Press ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት በሰጡት መረጃ - "የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት። ስለዚህ ጠ/ሚሩ በተመረጡ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ላይ ከኖቤል ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር ይካፈላሉ" ብለዋል።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ባሰራጨው መረጃ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በ2009 የኖቤል የሰላም ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት የሚድያ ፕሮግራሙ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተው እንደነበር አስውሷል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NobelPeacePrize

ዶ/ር አብይ ኦስሎ....

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማታቸውን ለመቀበል የኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማታቸውን የሚቀበሉት ነገ ማክሰኞ ህዳር 30/2012 ዓ.ም ነው። ጠ/ሚሩ በዚሁ ጎዟቸው ወቅት ወደ ስዊድን ጎር ብለዋ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሎቨን ጋር በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነቶች ላይ ተነጋግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia