TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Day1 #ኡቡንቱ #Ubuntu

አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ - #ኡቡንቱ በሚል ርዕስ ያዘጋጀነው የግንዛቤ መፍጠሪ መድረክ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ስኬታማ ነበር። ሁሉንም አካላት ከልብ ለማመስገን እንወዳለን! ከወጣቶች ጋር የምናደርገው ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴ እስከ ህዳር 27 ይቀጥላል።

“Ubuntu is about a community coming together to help one another.”— Paul Pierce

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ፒስሞዴል
#ጋሞዞንአስተዳደር

"ኡቡንቱ" ላይ የምንሰራቸው ሀገር አቀፍ ስራዎች ላይ አስተያየታችሁ፣ ሃሳባችሁን አካፍሉ። በምን በኩል ብንሰራ ውጤት እናመጣ ይሆን? ልታግዙን ይምትችሉ አካላትም አናግሩን! @tsegabwolde
@tikvahethiopiaBot 0919743630
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ!

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ሊገጥሟት የሚችሉ አራት ሴናሪዮዎች ይፋ ተደረጉ። አራቱ ሴናሪዎች /እጣ ፈንታ/ ይፋ የተደረጉት ትናንት ማምሻውን (ህዳር 23/2012 ዓ.ም) በስካይላይት ሆቴል "የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032" በሚል ርእስ በተደረገዉ የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ።

በመድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፣፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የዴስቲኒ ኢትዮጵያ በአገሪቱ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ክልሎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ምሑራን የተውጣጡ 50 ሰዎች በጥንቃቄ በመምረጥ ላለፉት ስድስት ወራት ዝግ ስብሰባዎችን በማካሄድ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት አገራችን ሊገጥሟት የሚችሉ አራቱን ሴናሪዎች መቅረፁን የዴስቲኒ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ንጉሴ አክሊሉ ተናግረዋል። አራቱ ሴናሪዎች አፄ በጉልበቱ ፣ ሰባራ ወንበር ፣ የፋክክር ቤት እና ንጋት ናቸዉ።

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ-ባሕር ዳር የቦይንግ አውሮፕላን በረራ በድጋሚ ተመጀረ!

ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ - ባሕር ዳር የቦይንግ አውሮፕላን የበረራ አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በአዲሱ መርሃ-ግብር መሰረት ቦይንግ ወደ ባሕር ዳር በሳምንት አራት ቀን ማለትም ማክሰኞ፣ ሐሙስ፣ ቅዳሜና እሑድ የሚበር ይሆናል።

ቦይንግ ወደ ባሕር ዳር በረራ መጀመሩ ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ለቱሪዝም ፍሰቱ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የገለፁት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ናቸው።

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በዋጋ መውደቅ ምክንያት ሰሊጥ ወደ ምርት ገበያ ድርጅት ማቅረብ አቋርጠናል" –ሰሊጥ አቅራቢ ነጋዴዎች

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሚገኙ ሰሊጥ አቅራቢ ነጋዴዎች በዋጋ መውደቅ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት ያቀርቡት የነበረውን የሰሊጥ ምርት ማቋረጣቸውን ገለጸ።

አቅራቢዎች እንዳሉት መንግስት ባስቀመጠው የመግዣ ዋጋ ተንተርሰው ለተከታታይ ወራት ከአምራቹ በመግዛት ለምርት ገበያ ድርጅቱ ቢያቅቡም ከፍተኛ ኪሰራ ስለደረሰባቸው ምርቱን ማቅረብ ለማቋረጥ መገደዳቸውን አስረድተዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
‹‹አባሎቼ ይለቀቁልኝ›› አብን!

‹‹አመራርና አባሎቼ በግፍ ታስረውብኛል›› ሲል መንግሥት እንዲለቃቸው የጠየቀው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተቃውሞውን በአድማና ሰልፎች እንደሚገልፅ አስታወቀ፡፡

በሰኔ 15ቱ የባለሥልጣናት ግድያ ትክክለኛ ተጠያቂዎች ተይዘዋል ብሎ እንደማያምን የገለፀው ንቅናቄው አባላቱ እንዲፈቱለትና መንግሥት በወንጀሉ ፈፀሚዎች ላይ አሁንም ጠንካራ ምርመራ እንዲደርግ ጠይቋል፡፡ ይህ ካልሆነና አባሎቹ ካልተፈቱ ግን የአደባባይ ሰልፎችና የተለያዩ አድማዎችን በማድረግ በተቃውሟቸው እንደሚቀጥሉ ሊቀ መንበሩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ይሁንና የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥት ምርመራ ቡድን በሰኔ 15ቱ የባለሥልጣናት ግድያ ላይ ጥልቅ ምርመራ ማድረጉንና ተሳትፎ እንዳለቻው ባመነባቸው ግለሰቦች ላይ ክስ እንደሚመሰርት ከሳምንታት በፊት መግለፁና ክስም መመስረቱ ይታወቃል፡፡

የአብን ሙሉ መግለጫ👇
https://telegra.ph/NMA-12-04

(NMA - AHADURADIO)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር በኢትጵያ የስሎቫኪያ አምባሳደር ድራሆሚር ስቶስን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ አነጋግረዋል፡፡

በሁለትዮሽ ውይይታቸውም በአገራቱ መካከል ለረጅም አመታት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የስሎቫኪያ አምባሳደር ድራሆሚር ስቶስ እንደገለጹት በሁለቱ አገራት መካከል ለዘመናት የቆየውን ትስስር ተከትሎ አሁንም የስሎቫኪያ ባለ ሃብቶች በኢትዮጰያ በሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KOKA

የእንቦጭ አረም በቆቃ ሐይቅ ላይ እየተስፋፋ ያለበት ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡ የቆቃ ግድብ፣ ኤሌክትሪክ ከማመንጨትም በተጨማሪ፣ ለቱሪስት መስህብነት እንዲሁም በዓመት ከ625 ቶን በላይ የዓሳ ምርት የሚገኝበት ነው፡፡ አረሙን በዘላቂነት ለማስወገድ፣ ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻልበት መንገድ እየተፈለገ መሆኑም ተሰምቷል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

More(ENA)👇
https://telegra.ph/ETH-12-04-2

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FakeNewsAlert

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሕወሓት ጠሪነት “ሕገ መንግሥትና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓትን ማዳን" በሚል ርዕስ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፍ ለጠሪው አካል እንዳሳወቀ ጠቅሶ በማኀበራ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው ደብዳቤ ግን የሐሰት ዜና መሆኑን በትዊተር ገጹ አሳውቋል፡፡

(አዲስ ዘይቤ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ላይ የሚያገለግል ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ። ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለጊዜው የተጀመረው በ10 ኤርባስ 350 አውሮፕላኖች ላይ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከ6 ቢልዮን ብር በላይ ወጪን የሚጠይቁ የአስፋልት መንገዶች ሊገነቡ ነው!

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከ6.1 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ አስፋልት መንገዶች ሊያሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ከ6.1 ቢልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የ299 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸውን አራት መንገዶች በአስፓልት ደረጃ ሊያስገነባ ነው፡፡

ባለስልጣኑ ለሚያስገነባቸው አዳዲስ የአስፋልት መንገዶች ከአሸናፊ የስራ ተቋራጮች ጋር ነገ ህዳር 25/2012 ዓም ይፈራረማል። በዕለቱም እየተባባሰ የመጣውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያስችል በመሰረተ ልማት ግንባታና ማሻሻያዎችን በተመለከተ በተዘጋጀው መረሃ ግብር ላይ የመስሪያ ቤቱ የበላይ ሃላፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሏል። በነገው እለት መስርያ ቤቱ ከተቋራጮቹ ጋር የሚፈራረምባቸው አራቱ መንገዶች የሀሙሲት-እስቴ፣ የፍስሀገነት - ኮሌ- ሰገን - ገለባኖ ሎት 2 የጩልሴ-ሶያማ፣ የጎዴ ቀላፎ-ፌርፌር እና የአደሌ- ግራዋን መንገዶች ሲሆኑ አጠቃላይ 299 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖራቸዋል ተብሏል።

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ጂቡቲ ውስጥ ለማቋቋም የተደረሰ ስምምነት የለም ተባለ!

እስካሁን ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን በጂቡቲ ለማቋቋም የተደረሰ ስምምነት እንደሌለ ተገለጸ። የባሕር በር አልባዋ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ሦስት አስርት ዓመታት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ ጂቡቲ ውስጥ መልሳ ልታቋቁም መሆኗ ተነግሯል።

ባለፈው ሳምንት ካፒታል የእንግሊዝኛ ጋዜጣ የኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን ጂቡቲ ውስጥ እንደምታቋቁምና ዋና የማዘዣ ጽህፈት ቤቱም በባሕር ዳር ከተማ እንደሚሆን ዘግቦ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይሏን መልሳ የማደራጀት ፍላጎት እንዳለት በከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በይፋ መነገሩ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር የሆኑት መሐመድ እድሪስ ፋራህ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጉዳዩን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና የጂቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኢል ኦማር ጊሌ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ እንዳሉት የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል ጂቡቲ ውስጥ ማቋቋምን በሚመለከት ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ያመላከቱ ሲሆን፤ ነገር ግን "እስከ አሁን የተደረሰ ህጋዊ ስምምነት የለም" ብለዋል።

More👇
https://telegra.ph/BBC-12-04

(BBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሮፌሰር መረራ ስለ ዶ/ር አብይና አቶ ለማ...

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ቢለያዩም ልዩነታቸው የተሻለ ሐሳብና ሥራ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህ ግን በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ነው መሆን ያለበት”

(ሸገር 102.1)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
#EPRDF #NEBE #ProsperityParty

በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውህደቱ አካል ለሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝና በአዋጅ አንቀጽ 91(4)ሀ መሰረት በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስረከቡን ፓርቲው ገልጿል።

(EPRDF Official)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia