የጎዳና ተዳዳሪዎቹን ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ ተቀጣ!
(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)
•የሦስት ሰዎችን ሕይወት በተመሳሳይ አጥፍተዋል የተባሉት ግለሰብ አንድ ሰው ላይ ሙከራ አድርገዋል
በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ኸለት ልዩ ሥሙ አሜን ሆስፒታል ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ሚሊዮን ዘሪሁን የተባለ የጎዳና ተዳዳሪ በሌላ ጎዳና ተዳዳሪ ላይ በበቀል ስሜት በመነሳሳት በፈፀመው የግድያ ወንጀል ተፈረደበት።
ሟች በራሱ ላይ በተጫነበት ከፍተኛ መጠን ያለውን ድንጋይ፣ የራስ ቅል አጥንት መሰባበር እና የአንጎል ወደ ውጪ መውጣት ደርሶበት ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ተከሳሽ በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ሲመለከት በቆየው መዝገብ ላይ እንደተረጋገጠው፣ ተከሳሽ ሟች እና ጓደኞቹ ጋር ‹‹የጉልበት ሥራ በመሥራት የተገኘውን ገንዘብ ሳይከፍሉኝ ቀርተዋል፤ በጋራም በመሆን ድብደባ ፈጽሞብኛል›› በሚል ምክንያት በቂም በመነሳት ወንጀሉን ፈፅሟል። በዚህ ምክንያትም ሟች የሚያድርበትን አካባቢ ሲያጠና ከቆየ በኋላ በግምት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ሲሆን ሟች በጎዳና ላይ የግንብ አጥር ስር ተኝቶ ባለበት ቦታ በጭካኔ ሕይወቱ እንዲልፍ አድርጓል በሚል ተከሷል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-27-3
@tikvahethiopia @tikvahethiopiabot

በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረው ግድያ አሁንም ቀጥሏል!
በምዕራብ ኦሮሚያ "በመንግስት ባለስልጣናት" ላይ ያነጣጠረው ግድያ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ። ትናንት በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ሁለት የወረዳው ባለስልጣናት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።
በትናንትናው የጎጆ ከተማ ግድያ ሕይወታቸውን ያጡት የጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ረጋኔ ከበደ እና በወረዳው የኦዲፒ ጽ/ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ገረመው መሆናቸውን የወረዳዋ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ባለሞያ አቶ ቢቂላ አበበ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ገልጸዋል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-27-4
(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህይወት ቁጥር አንድ የአፀደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት የመማር ማስተማሩን ሂደት ጎብኝተዋል!
በጉብኝታቸውም ወቅት ተማሪዎች የገጠማቸው ሁኔታ ከምግብ መመረዝ ጋር ግንኙነት እንደሌለው እና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እንዲሁም የመማር ማስተማሩ ሂደት በተለመደው መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመልክተዋል፡፡
በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ ቁልፍ የልማት ስራዎች አንዱ የሆነው የምገባ ፕሮግራሙን ተቋማዊ ለማድረግ በከተማው ምክር ቤት በአዋጅ እንደሚፀድቅ እና ተቋሟዊ በሆነ መልኩ የምገባ መርሃ-ግብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢ/ር ታከለ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
በጉብኝታቸው ላይ የተማሪዎችን የመመገቢያ ክፍልን ጨምሮ የመማሪያ ክፍሎችን ፣ የማብሰያ ቦታዎችን እና የእጅ መታጠቢያ ስፍራዎችን የጎበኙት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋርም ቆይታ አድርገዋል፡፡
(Mayor Office AA)
@tikvahethiopia @tsegabwolde

የአርባ ምንጭ ጊዜያዊ ፀጥታ ኮማንድ ፖስት!
በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ-ገጾች በሚለቀቁ የሃሰት መረጃዎች ህብረተሰቡ እንዳይወዛገብና የጸጥታ አካሉ ምንጊዜም ለህዝብ የቆመ መሆኑን ሊረዳ እንደሚገባ የአርባ ምንጭ ጊዜያዊ ፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳሰበ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስትና ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለአንድነት ፤ለፍቅር ፤ለእርቅ ፤ለህዝቦች የእርስበርስ ግኑኝነት መጠናከር እየሰራ ባለበት በአሁኑ ወቅት ህገመንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ፤እንዲሁም ህዝብና መንግስት እያስመዘገቡ ያሉትን ድሎች ለመቀልበስና የህዝቡን ሰላም ለማፍረስ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ- ገጾች በሚወጡ የሃሰት መረጃዎች ህብረተሰቡ እንዳይወዛገብና የጸጥታ አካሉ ምንጊዜም ለህዝብ የቆመ መሆኑን ሊረዳ እንደሚገባ የአርባምንጭ ከተማ ጊዜያዊ ፀጥታ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢሻለቃ አውራርስ ሙሉነህ ገለጹ፡፡
ኮማንድ ፖስቱ ስራ ከጀመረ ወዲህ መንግስት እና ሕዝቡ ባደረጉት የፀጥታ ማስከበር ስራ ከምንጊዜውም በላይ የከተማዋ ሰላም ተጠብቆ መቆየቱን ያወሱት ሻለቃ አውራርስ የአርባምንጭ ከተማ ህዝብ ሰላም ወዳድ እና ለሌላው አከባቢ ተምሳሌት መሆኑን ገልጸው ይህንን ሰላም ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ሊያስቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች የፀጥታ ኃይሉን ስም ለማጉደፍ ጥረቶች መደረጋቸውን የተናገሩት የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ሻለቃ አውራርስ በኮማንድ ፖስት የተከለከሉ ተግባራትን የተላለፉ አካላትን በህግ ተጠያቂ የሚሆኑበት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሕዝቡን ለመረበሽ የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡
(የከተማው ኮሚኒኬሽን)

ደኢህዴን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በሀዋሳ ማካሄድ ጀምሯል!
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን አስቸኳይ እና ልዩ ጠቅላላ ጉባዔ በሀዋሳ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ደኢህዴን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚያደርገው ጉባኤው የብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡- ደኢህዴን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የጌዲዮ ዞን ፌደራል መንግስት በክልልነት እንዲያዋቅረው ጠየቀ!
የጌድዮ ዞን አዋሳኝ የሆነው የሲዳማ ዞን በህዝበ ውሳኔ ወደ ከልልነት ማደጉን ተከትሎ ከደቡብ ክልል ጋር ያለው የየብስ ግንኙነት ይቋረጣል።
በጌዲዮ ዞን ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ቦጋለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳሉት ሲዳማ ዞን ከደቡብ ክልል እራሱን ችሎ በክልልነት ደረጃ ሲወጣ የጌዲዮ ዞን ከየትናውም የደቡብ ክልል ዞኖች ጋር በጂኦግራፊ አቀማመጥ የማይገናኝ መሆኑን ተከትሎ የአስተዳደር ሁኔታው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ብለዋል፡፡
በ56 ብሔር ብሔረሰቦች የተዋቀረው የደቡብ ክልል ባሳለፍነው ሳምንት የሲዳማ ዞን በህዝበ ውሳኔ ወደ ክልልነት ማደግ የሚያስችል ውሳኔ ተላልፏል። በመሆኑም ቀሪዎቹ 55 ብሔር ብሔረሰቦች በአንድ የአስተዳደር መዋቅር ይቀጥላሉ የሚል ጭምጭምታ መሰማቱን ተከትሎ የጌድዮ ዞን ከተቀረው የደቡብ ክልል ዞኖች ጋር ስለማይዋሰን በክልልነት እንዲዋቀር ተጠይቋል።
(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

የዋለልኝ "የብሄሮች ጥያቄ በኢትዮጵያ" 50ኛ አመት መታሰቢያ እየተካሄደ ነው!
የዋለልኝ "የብሄሮች ጥያቄ በኢትዮጵያ" ከ 50 ዓመታት በኃላ በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው። ከ50 ዓመታት በፊት በዋለልኝ መኮንን የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦችን የተመለከተው ባለ 5 ገፅ ፅሁፍ ውስጥ ያሉ ዕሳቤዎች ያሳደሩትን ተፅህኖ የሚፈትሸው ውይይት በኢትየጵያ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ተቋም የተዘጋጀ ነው።
(ኢቢሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የዋለልኝ "የብሄሮች ጥያቄ በኢትዮጵያ" ከ 50 ዓመታት በኃላ በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው። ከ50 ዓመታት በፊት በዋለልኝ መኮንን የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦችን የተመለከተው ባለ 5 ገፅ ፅሁፍ ውስጥ ያሉ ዕሳቤዎች ያሳደሩትን ተፅህኖ የሚፈትሸው ውይይት በኢትየጵያ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ተቋም የተዘጋጀ ነው።
(ኢቢሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Ethio-India Application form.docx
149.1 KB
የውድድር ማስታወቂያ!
የኢትዮ- ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕግራም የኢትዮጵያና የህንድ የንግድና የፈጠራ ስራ ባለሙያዎች የሽርክና ውል በመፍጠር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰሩ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
በህንድ በኩል ፍላጎቱ ያላቸውና ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ተቋማትና ግለሰቦች ተመርጠዋል፡፡
በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የንግድና የፈጠራ ስራ ባለሙያዎችና ድርጅቶችን ለመምረጥ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡
የማስታወቂያውን ዝርዝር መስፈርት እና የአመልካቾች የመረጃ መሙያ ቅፁን ከዚህ ልጥፍ ጋር ያያዝን በመሆኑ
ፎርሙን ሞልታችሁ በኢሜል አድራሻችን [email protected] ላይ መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አልያም ፒያሳ ከቴዎድሮስ አደባባይ ዝቅ ብሎ ከሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት ጀርባ ከሚገኘው መስሪያ ቤታችን በአካል በመቅረብ ማመልከቻውን ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
(የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)

ፍሬህይወት ቁጥር 1...
በልደታ ክፍለ ከተማ የፍሬህይወት ቁጥር 1 አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በትናንትናው እለት ችግሩ ተከስቶባቸው የነበሩ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘታቸውንና የምገባ ፕሮግራሙም እንደቀጠለ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ገለፀ፡፡ የመማር ማስተማር ሂደቱም እንደወትሮው ሁሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የመማር ማስተማር ሂደቱንም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ዛሬ ጠዋት በትምህርት ቤቱ በመገኘት አስጀምረዋል፡፡

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Lammiilee Itoophiyaa maraaf, ejennoo fi hawwii Paartii badhaadhinaa ilaalchisee ergaan isiniif dabarsu.
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብልጽግና ፓርቲን አቋምና ምኞት በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለመላ ኢትዮጵያውያን ያስተላለፉት መልእክት...
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የብልፅግና ፓርተ መሰረቱ በኦሮሚያ ክልል የቄሮን ትግል፤ በአማራ ክልል የፋኖን ትግል፤ በደቡብ ዘርማና ሌሎች ወጣት አደረጃጀቶች በጋራ ያደረጉትን ትግል ከተረት ተረት ወደ እውነተኛ ብልፅግናና ሰላም፣ ዴሞክራሲያዊና አንድነት ለማሸጋገር የተደረገ ሂደት መሆኑ ታምኖ ቄሮዎች፣ ፋኖዎች እንኳን ደስ አላችሁ፤ የታገላችሁበት ፓርቲያችሁ ተመስርቷል! ከፓርቲያችሁ ጋር ሆናችሁ ስታነሱ የነበረውን ጥያቄ ወደ ተግባር እንዲመለስ አስፈላጊውን ጥረት እንድታደርጉ ጥሪዬን ላቀርብላችሁ እፈልጋለሁ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ድርጅታችን የፋኖን እና የቄሮን ትግል የሚያስታውስ የተግባር ማስታወሻ እንደሚያስቀምጥ ሳበስርላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአክሱም ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓልን ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል!
የአክሱም ፅዮን ዓመታዊ ክብረ በዓልን የፊታችን እሁድ በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የከተማው ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት አስታወቀ። በዓሉ ለቱሪዝም እድገት አስተዋፅኦው የጎላ ነው ተብሏል። የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገብረመድህን ፍጹምብርሃን ዛሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት በዓሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር አስፋላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።
"የህዳር ጽዮን በዓል" - ከሃይማኖታዊ በዓልነቱ ባለፈ ለቱሪዝም መስህብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል። በተለይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ከማሳደግና የህዝብ ለህዝብ ግንኝነት ከማጠናከር አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። የበዓሉ ታዳሚዎች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱንና ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።
(ENA)
ፎቶ: ፋይል

#UNESCO #ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት የዓለም አቀፍ የቅርስ ኮሚቴ የዩኔስኮ አባል ሆና ተመረጠች። ኢትዮጵያ በተመሳሳይ የዩኔስኮ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እና የዓለም አቀፍ ቅርስ ኮሚቴ አባል ሆና እንደምታገለግልም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል(የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና) አይሰጥም!
10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከዚህ ዓመት (2012 ዓ/ም) ጀምሮ አይሰጥም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ እንደቻለው የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወዲሁ ቅድም ዝግጅት ጀምሯል። በአዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረት ቀደም ብሎ በ10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በ12ኛ ክፍል እንዲሰጥ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ይታወቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ሳምንታት ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

"በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት የለም" - የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት!
በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት አለመኖሩን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የእንግሊዝ መንግስት ባለፈው ሰኞ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት በመኖሩ በተለይ ነፍሰጡር እናቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት አለመኖሩን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን አንዳስታወቁት የዚካ ቫይረስ አምጪ ትንሽ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለም አገራት ትገኛለች። ይሁንና “ትንኟ አለች ማለት በሽታው ተከስቷል” ማለት አለመሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም የአገሪቷ አካባቢ በትንኟ አማካኝነት በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም ብለዋል። የእንግሊዝ መንግስት ለዜጎቹ ያሰራጨው መረጃ ከምን ተነስቶ እንደሆነም ግልጽ አለመሆኑን ተናግረዋል።
የዚካ ቫይረስ ‘ኤደስ’ በምትባል የወባ ዝርያ የሆነች ትንኝ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው በደም ልገሳ፣ ከእናት ወደ ልጅ እንዲሁም በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የመተላለፍ ዕድል አለው።
(ኢዜአ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ደኢህዴን የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል ወሰነ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል በሙሉ ድምጽ ወሰነ። ደኢህዴን በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ባካሄደው አስቸኳይና ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ነው የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል በሙሉ ድምጽ የወሰነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል በሙሉ ድምጽ ወሰነ። ደኢህዴን በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ባካሄደው አስቸኳይና ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ነው የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል በሙሉ ድምጽ የወሰነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦነግ ስለ ኦሮሚያ ባለስልጣናት ግድያ...
በምዕራብ ኦሮሚያ በባለስልጣናት ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ በመንግስት የውስጥ አሻጥር የሚፈጸም ነው ብሎ እንደሚያምን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በተለይ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ገለጸ። ኦነግ በግድያዎቹ “እጁ እንደሌለበት፤ የሚያዘውም ሰራዊት እንደሌለው” አስታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ስላሉ ግድያዎች በጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጥያቄ የቀረበላቸው የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ “በእኛ ግምት እና በአንዳንድ ምልክቶች፤ የውስጥ አሻጥር የሚመስል ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። “ከመንግስት የውስጥ መዋቅር በተለይም ከመከላከያው እና ጸጥታ ክፍሉ ውስጥ ሆን ብለው አሻጥር (ሳቦታጅ) የሚሰሩ ይኖራሉ” ብለዋል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-28-2
(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ~ DW)

የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መጠቀም የሚያስችል የኤቲኤም አገልግሎት ተጀመረ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የኤቲኤም (ATM) ማሽን በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ።
አዲስ የATM የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የATM ማሽን አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍንፍኔ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ንጉሴ ለማ አስታውቀዋል።
እንደ አቶ ንጉሴ ገለፃ ቀደም ሲል አገልግሎት ላይ ከዋለው የገንዘብ መክፈያ የATM ማሽን በተጨማሪ አዲሱ ማሽን ወጪ ብቻ ሳይሆን ደንበኞች ገንዘብ ወደ ሂሳባቸው ገቢ ማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚችሉበት ነው።
ይህ አገልግሎት ለመጀመርያ ጊዜ በስራ ላይ የዋለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ ፤ ማሽኑ በአሁኑ ሰኣት በሙከራ ደረጃ በፍንፍኔ ቅርንጫፍ አገልግሎቱ መጀመሩን ተናግረዋል።
ይህ ማሽን ስራ ከማቀላጠፍና ከማቃለል በተጨማሪ በተለይ ባንኮች ክፍት በማይሆኑበት ዕለታት ደንበኞች የእለተ እለት ስራቸውን ለማቀላጠፍ እንዲችሉ ታሳቢ ተደርጎ እየተዘጋጀ መሆኑን አቶ ንጉሴ ጠቁመዋል።
https://telegra.ph/ETH-11-28-3
(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የኤቲኤም (ATM) ማሽን በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ።
አዲስ የATM የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የATM ማሽን አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍንፍኔ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ንጉሴ ለማ አስታውቀዋል።
እንደ አቶ ንጉሴ ገለፃ ቀደም ሲል አገልግሎት ላይ ከዋለው የገንዘብ መክፈያ የATM ማሽን በተጨማሪ አዲሱ ማሽን ወጪ ብቻ ሳይሆን ደንበኞች ገንዘብ ወደ ሂሳባቸው ገቢ ማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚችሉበት ነው።
ይህ አገልግሎት ለመጀመርያ ጊዜ በስራ ላይ የዋለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ ፤ ማሽኑ በአሁኑ ሰኣት በሙከራ ደረጃ በፍንፍኔ ቅርንጫፍ አገልግሎቱ መጀመሩን ተናግረዋል።
ይህ ማሽን ስራ ከማቀላጠፍና ከማቃለል በተጨማሪ በተለይ ባንኮች ክፍት በማይሆኑበት ዕለታት ደንበኞች የእለተ እለት ስራቸውን ለማቀላጠፍ እንዲችሉ ታሳቢ ተደርጎ እየተዘጋጀ መሆኑን አቶ ንጉሴ ጠቁመዋል።
https://telegra.ph/ETH-11-28-3
(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ሃሙስ በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ፤ የምሥጋና ቀን እየተከበረ ነው!
የሕዳር ወር በገባ አራተኛው ሃሙስ በየዓመቱ በዚህ ዕለት ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመድ ጓደኛ ተሰባስቦ የሚያከብሩው የምሥጋና ቀን በዓል እየተከበረ ነው። ይህ ቪድዬ በደቡባዊ ካሊፎርንያ የሚኖሩ አሜሪካውያን ዓመታዊውን የምስጋና ቀን ለማክበር ትናንት ዕሮብ ዕለት ወደ የቤተሰቦቻቸው ጉዞ ሲያደርጉ ያሳያል፡፡ በዚሁ ዓመታዊ ክብረ በዓል ወደ 55 ሚሊዬን የሚጠጉ አሜሪካውያን ወደ ቤተሰቦቻቸው፣ ዘመድና ወዳጆቻቸው የሚጓጓዙ ሲሆን ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮ ቀጥር ጨምሯል፡፡ በዚህ ዓመታዊ በዓል ዩናይትድ ስቴትስ አውራ ጎዳናዎችና የአውሮፕላን ማረፍያዎች በተጓዦች ይጨናነቃሉ።
(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ)