TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሰላም ገብተናል...#ArbaMinch
#ARBAMINCH የ2011 ዓ/ም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የማጠቃለያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ARBAMINCH

የትራፊክ አደጋን #ለመቀነስ በሚያስችሉ 58 የተመረጡ ስፍራዎች ላይ ዘመናዊ የፍጥነት መቀነሻና የእግረኛ ማቋረጫ ግንባታ ስራዎችን በከተማዋ እያከናወነ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ትራንስፖርትና መንገድ ጽ/ቤት ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነገው ዕለት በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚካሄደው ሩጫ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል። #ARBAMINCH
#ARBAMINCH

በአርባምንጭ ከተማ በዝርፊያ፣ በህገ-ወጥ መሳሪያና ኮንትሮባንድ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ሠላምና ጸጥታ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉን ሠላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ማወጁን መነሻ በማድረግ ከመከላከያና ልዩ ሃይል ጋር በቅንጅት በመስራት የቡድን ዘረፋን ጨምሮ ህገ-ወጥ መሳሪያና የተለያዩ ኮንትሮባንድ ንግዶችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደቻለ የአርምንጭ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል መስፍን አንዳርጌ ገልፀዋል፡፡

የነዋሪውን ደህንነት ለማስጠበቅ የከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንዳለ ያሳውቁት ኃላፊው በከተማው በውህ ምንጭ ቀበሌ በተለምዶ ቆንጥር ሰፈር በሚባልበት አከባቢ ለበርካታ ጊዜያት በመመሸግ የተለያዩ ዝርፍያዎችን ሲፈፅሙ የቆዩና የነዋሪውን የቤት እንስሳ ሰርቀው በማረድ ለሆቴሎች በሽያጭ ሲያከፋፍሉ የነበሩ 12 ግለሰቦች ለእኩይ ተግባራቸው ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙበትን ገጀራና ሰንጢዎች ፤ አደንዛዥ እፆች እንዲሁም ስልክና የተለያዩ ክህብረተሰቡ የዘረፏቸው ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በኤግዝብትነት መያዛቸውን አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Arbaminch

ከጠቅላይ ሚኒስተር ጽህፈት ቤትና ከውጭ ሃገር የመጡ የቴክኒክ አባላት በአርባምንጭ ከተማ ለሚገነባው ስመጥርና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴልና ሪዞርት ግንባታ ጅማሮ የሚሆን የቦታ መረጣና ቅኝት ስራዎችን አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ ለህዝብ እንደራሴ አባላት በአፍሪካ ሲሼልስ ከሚገኘው ግዙፉ ሆቴልና ሪዞርት በመቀጠል በአርባምንጭ ከተማ ስለሚገነባው ሆቴልና ሪዞርት ገለፃ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-13

ምንጭ፦ የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ArbaMinch

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማስመልከት የአ/ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የእርሳቸው ውጥን እንዲሳካ በማሰብ ችግኝ በመኮትኮት ደስታቸውን ዛሬ እየገለፁ ነው።

Via ብርሽ ዘውዴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ArbaMinch

በአርባምንጭ አባያ ኃይቅ ላይ በደረሰ የጀልባ መስመጥ አደጋ 6 ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ያካባቢው ፖሊስ አስታውቀቋል። አደጋው የደረሰው ላንቴ ተብሎ ከሚጠራው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ አካባቢ ሰዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን ጭና ወደ አርባምንጭ ከተማ ስትጓዝ የነበረች አንዲት ጀልባ በመስመጧ ነው።

በአደጋው ከጀልባዋ ኦፕሬተር ውጭ በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩ 6 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አይንሸት ቦርኮ ተናግረዋል። ጀልባዋ ከአቅም በላይ ጭና ነበር ያሉት ኮማንደር አይንሸት አደጋው ትናንት ሰኞ ከቀኑ 9:00 አካባቢ መድረሱን ገልፀዋል። የጀልባዋን የነዳጅ ታንከር በመጠቀም እየዋኘ ራሱን ከአደጋው የታደገው የጀልባዋ ኦፕሬተር "ፉራ "በሚባል አካባቢ ከምሽቱ 3:00 ላይ በፓሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉንና በምርመራ ላይ መሆኑን ፖሊስ አዛዡ ገልፀዋል። ኮማንደር አይንሸት አያይዘውም የደረሱበት ያልታወቀውን የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ፖሊስ እያፈላለገ ነው ብለዋል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ArbaMinch

"የአርባምንጭ ደም ባንክ" ሰሞኑን በተካሄደው ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ መረሃ ግብር 411 ዩኒት ደም መሰብሰቡን ገለፀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ArbaMinch

የጋሞ ዞን አስተዳደር ከአ/ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ የከተማዋ ሰላም÷ ለልማት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር። በውይይቱ ማጠቃለያም የነበረውን የከተማን ሰላም ማስቀጠል÷ ልሜቷን መማፋጠን እና የአካባቢውን መረጋጋት የማይፈልጉ የግል ጥቅም ፈላጊዎች በማህበራዊ ሚድያ ከሚያሰራጩት ከሀሰት ወሬዎች እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል። የከተማዋም መገለጫ የራሱን ሰላም የሚያስጠብቅ ህብረ-ብሔራዊ ህዝብ ያላት መሆኑ÷ ድንቅ አፈጣጠሯ እና ሰላማዊ ከተማ መሆኗ የሚያኮራ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ ገልፀዋል።

Via ብርሽ ዘውዴ(TIKVAH FAMILY)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለትውስታ ከአምናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቲክቫህ ቤተሰቦች ጉዞ...

ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ፤ በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩና በማህበራዊ ሚዲያ(ቴሌግራም) ብቻ የተሰባሰቡት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች...

በልዩነቶቻቸው ተከባብረው፤ በሰውነታቸው ተዋደው፤ ከምንም ነገር በላይ ሰብዓዊነታቸውን አስቀድመው፤ ጥላቻን፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ሰዎችን በማንነታቸው ማሸማቀቅን፣ መግፋትን፣ ሰዎችን በሰውነታቸው አለማክበርን #ተፀይፈው "ነጩን የሰላም ምልክት፣ባንዲራ ተሸክመው ለሀገራች ህዝቦች ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር።

ለሀገራቸው ሰላም እና ፍቅር ቀና አስበው፤ ያለ አንዳቸው የግለሰብም ሆነ የድርጅት ድጋፍ፣ የትምህርት ጊዜያቸውን ሰውተው፤ ረጃጅም ጉዞዎችን እየተንገላቱ ተጉዘው፤ ከቤተሰባቸው ከሚላክላቸው ገንዘብ ቀንሰው ለጉዞ አውለው፣ ከራሳቸው ኪስ አውጥተው ተመገበው፣ የሚስማማቸውን ምግብ ካገኙ በልተው ከሌለም ፆም አድረው፤ ለፍቅር እና ለሰላም ሲሉ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። እንደ አንድ #ዜጋ ከራሳቸው የሚጠበቀውን በዚህ እድሜያቸው አድርገዋል። የህሊና ተወቃሽ ከመሆንም ድነዋል። ሁሌም ለሰው ልጅ ባላቸው ቀና አመለካከት ስናከብራቸው እና ስናወድሳቸው እንኖራለን።

የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
.
.
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"

#Jimma #Wollo #Haramaya #DebreBrihan #Mekelle #Woldia #ArbaMinch #Hawassa #WolitaSodo #Wachamo #Wolkite

የቲክቫህ ቤተሰቦች ትውስታ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia