TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በውህድ ፓርቲ ፕሮግራም (ማኒፌስቶ) ላይ ዝርዝር ውይይት እና ክርክር በማካሄድ ረቂቁ ለኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲቀርብ መወሰኑ የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ ስራ አስፈፃሚው በተዋሃደው ፓርቲ ሕገ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲመራ ወስኗል። ምክር ቤቱ በዛሬው እለት በሚያካሂደው ስብሰባ ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

(ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AIW

በዛሬው የAIW (Africa Industrialization Week) ስብሰባ ላይ የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር ተገኝው ንግግር አድርገዋል። በስብሰባውም ላይ እየተካፈሉ ይገኛሉ።

(Amanuel Eticha - Tikvah Family)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
🤔#WALTA ምን ነካው??

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥን አስመልክቶ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ አሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ እርሳቸው ያላሉት ነው!

"በሀዋሳ ከተማ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገበዉ መራጭ ዉስጥ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ ሰጥቷል"- ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ
.
.
ትናትና በተካሄደዉ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የነበረዉ ሂደት በሰላም መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ድምጽ ለመስጠት በመራጭነት ከተመዘገበዉ ህዝብ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ መስጠቱን በየምርጫ ጣቢያዎች እየወጣ ያለው ውጤት እንደሚያሳይም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

በድምፅ መስጫው ቀን እንዲቋረጡ ተደርገዉ የነበሩ መንግስታዊ አገልግሎቶችና የንግድ እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ተግባራቸዉ መመለሳቸዉንም ተናግረዋል፡፡

የሲዳማ ህዝበ ዉሳኔ በሀገሪቱ ለታየዉ የዴሞክራሲ ሂደት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ “ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ቀድሞ የነበረውን አንድነታችንን በማጠናከር ከድህነት ለመዉጣት መተባበር ይኖርብናል” ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡

(EBC)

ትክክለኛው መረጃ የፋና ብሮድካስቲንግ እና የEBC ነው!

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
EBC ዋልታ የሰራውን ዘገባ #FakeNews ብሎታል!

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥን አስመልክቶ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ እርሳቸው ያላሉት መሆኑን አስታወቁ!

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ በሀዋሳ ከተማ የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በሰጡት መግለጫ “90 በመቶ የሻፌታ ምልክት አሸነፈ” ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ እርሳቸው ያላሉት መሆኑን ምክትል ከንቲባው ለኢቲቪ አረጋግጠዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የተናገሩት “በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ድምጽ ለመስጠት በመራጭነት ከተመዘገበዉ ህዝብ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ መስጠቱን በየምርጫ ጣቢያዎች እየወጣ ያለው ውጤት ያሳያል፡፡” የሚለውን ነው፡፡

(EBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Misinformation_Alert

ዋልታ ኢንፎርሜሽን ዛሬ ጠዋት በሰራው ዘገባ የሃዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ የከተማው ነዋሪ 90 በመቶ ሻፌታን መምረጡ ተረጋገጠ በሚል የሰራው ዘገባ የተሳሳተ መረጃ ሲሆን ምክትል ከንቲባው የመራጮችን ተሳትፎንና ጸጥታን እንጂ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት የሚመለከት ምንም አይነት መግለጫ አልሰጡም፡፡ የምርጫ ውጤትን ማሳወቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሃላፊነት ብቻ መሆኑ እየታወቀ የሚዲያ አካላት የምርጫን አይነት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ዜናዎች ሲሰሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ትኩረት እንዲያደርጉ እንዲህ አይነት የተሳሳቱ መረጃዎች ሰላምንና ደህንነት የሚያናጉ በመሆናቸው እና በወንጀልም ስለሚያስጠይቁ ጋዜጠኞች ከዚህ አይነት ተግባራት እንዲቆጠቡ ቦርዱ ያሳስባል፡፡

(የኢትዮጵየ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዋልታ ይቅርታ ጠየቀ!

(ዋልታ ቴሌቪዥን)

ይቅርታ ስለመጠየቅ፦

በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ የሀዋሳ ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ድምጽ ውጤት ከ90 በመቶ በላይ መራጭ ሻፌታን መምረጡን ማረጋገጣቸውን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ አስታወቁ በሚል የተዘገበው መረጃ ስህተት መሆኑን እየገለጽን፤ ለዚህም ዋልታ ይቅርታ ይጠይቃል።

(ዋልታ ቴሌቪዥን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JimmaUniversity

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዛሬ በ11/03/2012 ባደረገው ሁለተኛው አስቸኳይ ስብሰባ አሁናዊ ሁኔታውን በመገምገም ትምህርት ለማስጀመር አስሸኳይ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ከሰኞ 15/03/2012 ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ወስኗል።

ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ከአርብ ህዳር 12 እስከ 14/ 2012 ዓ/ም ድረስ በየካምፓሳቸው "ዳግም ምዝገባ" በማካሄድ ሰኞ 15/03/2012 ትምህርት እንዲጀምሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GondarUniversity

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአፄ ፋሲል እና አፄ ቴዎድሮስ ግቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ የማይማሩ ከሆነ ከነገ 12/03/2012 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ አገልግሎት እንደሚያቋርጥ፤ እንዲሁም በማይማሩ ተማሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳታውቋል። ዩኒቨርሲቲው አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የመማር ማስተማር ስራውን በአግባቡ በማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳለም ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ዊዝድረዋል

በ2012 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር ተማሪዎች የሚያቀርቡት በጊዜያዊነት ትምህርት ማቋረጥ (ዊዝድረዋል) ጥያዌ እንዳማያስተናግድ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

በዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በጊዜያዊት የትምህርት ማቋረጥ (ዊዝድረዋል) ማድረግ እንደማይችሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዩኒቨርስቲዎች በላከው ደብዳቤ እንዳመለከተው በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር ተማሪዎች የሚያቀርቡትን በጊዜያዊነት ትምህርት ማቋረጥ (ዊዝድረዋል) ጥያቄ ዩኒቨርስቲዎች እንዳያስተናግዱ አሳስቧል፡፡

በተወሰኑ ዩኒቨርስቲዎች በተፈጠሩ ክስተቶች መነሻ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ባሉበት ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ተቆምጧል የሚለው ሚኒስቴሩ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በላከው ደብዳቤ ችግሮቹን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን አስታውሷል፡፡

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተፈጠሩ ችግሮች ውስጥ እጃቸው አለበት ተብሎ የተጠረጠሩ ከ100 በላይ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው መባሉ ይታወሳል፡፡ ከዛሬ በኋላ ወደ መማር ማስተማር በማይመለሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በምዕራብ ወለጋ ዞን አንድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣን መንገድ ላይ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ተገደሉ!

ትናንት [ረቡዕ] በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ውስጥ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ቶላ ገዳ ለሥራ ጉዳይ ወደ ምዕራብ ወለጋ ቄለም ወለጋ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት፣ ላሎ አሳቢ ተብሎ በሚታወቀው ወረዳ ውስጥ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤሊያስ ኡመታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህ ግድያ የተፈጸመው ላሎ አሳቢ ወረዳ ውስጥ ጋራ ቶሬ በሚባል ቦታ ላይ ረቡዕ ዕለት ጠዋት አምስት ሰዓት አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

አስተዳዳሪው ጨምረው እንደተናገሩት አቶ ቶላን የገደሉት ታጣቂዎች እየተጓዙበት በነበረው መኪና ላይ ከግራና ከቀኝ ሆነው በከፈቱት ተኩስ በመኪናው ውስጥ እየተጓዙ የነበሩ መንገደኞችን ኢላማ አድርገው እንደሆነ አመልክተዋል።

በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት አቶ ቶላ ገዳ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ እንደሆኑ አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልጸዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-21

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
AAU 6 ኪሎ የተማሪዎች ረብሻ ተነስቷል🤔

(ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት)

ዛሬ ቀን 7:30 ስድስት ኪሎ ዪንቨርስቲ የተማሪ ጩኸት ይሰማል። ፌዴራል ፓሊሶች አሉ። ተማሪዎች ከዶርም እንዳይወጡ ተደርገዋክ። የጊቢው በሮች ዝግ ናቸው። አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል። ረብሻ ለማስነሳት ሙከራዎች ነበሩ ግን እውነተኛ ምክንያቱን አላውቅም ሲል አንድ ተማሪ ተናግሯል።

ይህ በጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት ፌስቡክ ገፅ ላይ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የቲክቫህ 6 ኪሎ ቤተሰቦች ገልፀዋል። በግቢው ውስጥ አለመረጋጋት ነበር ነገር ግን ተኩስ የሚባል ነገር አልነበረም፤ መረጃው ስህተት ነው ሊታረም ይገባዋል ብለዋል። @tikvahethiopiaBot
ጋሞ ዞን...

በጋሞ ዞን በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማይገባቸው ደረጃ ላይ ተቀምጠው በተገኙ 31 ግለሰቦች ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል መረጃ ማሰባሰቡን የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለፀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዳበሮ ዳልጬ እንደገለፁት ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በዞን ደረጃና በስሩ በሚገኙ ወረዳዎች የ3ሺህ 238 ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራ ተከናውኗል። ከእነዚህ ዉስጥ 31 የመንግስት ሠራተኞች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ለበርካታ ዓመታት የመንግስትን ገንዘብ ያለአግባብ ሲጠቀሙ መቆየታቸውን ተረጋግጧል፡፡

(ENA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AAU

ጋዜጠኛ ጌትነት ተስፋዬ - ተኩስ ነበረ የተባለው #ውሸት ነበር በሚል ዳግም በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ አስተካክሏል። በተማሪዎች ስም እኛም እናመሰግናለን!
-------
ጥቃቅ የሚመስሉ ነገር ግን ወላጆችን የሚያስጨንቁ መረጃዎች ስላሉ ጋዜጠኞችም ሚዲያዎችም ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መረጃ ቢያቀብሉ ይመረጣል!! ትላንት ፋና ብሮድካስቲንግ በፌስቡክ ገፁ ይዞት የወጣው የተሳሳተ መረጃ በርካታ ቤተሰቦቻችን ላይ ጭንቀት ፈጥሮ ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረው ግርግር በፍጥነት ተረጋግቷል አለ!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በዩኒቨርሲቲው ተፈጠረሮ የነበረውን ችግር በፍጥነት በመቆጣጠር አሁን የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል፡፡ ግርግሩ ተማሪዎች ባነሱት ጥያቄ የተፈጠረ ቢሆንም ጥያቄው ምን እንደሆነ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ ከደቂቃዎች በፊት በዩኒቨርሲቲው ግርግር ከተፈጠረ በኋላ የፀጥታ አካላት ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ከዩኒቨርሲቲው ይዘዉ ሲወጡ ታይተዋል፡፡

(Tamirayehu W. Seven)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ወ/ሮ ያለም ፀጋይ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ። በጉብኝታቸውም በሆስፒታሉ ግቢውስጥ በቅርቡ የጤና ሚኒስቴር ያስከፈተውን የመረጃ ማዕከል እንዲሁም ህሙማንን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በተጨማሪም የሆስፒታሉን የልብ ሀክምና ማዕከል፣ የቶክሲኮሎጂ (የተመረዙ ሰዎች ህክምና) የስልክ ጥሪ ማዕከል እና የቀዶ ህክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል። በዚህ ወቅትም በህክምና ክፍሉ የሚስተዋሉት የአቅርቦትና የግብዓት ችግሮች እንዲፈቱ የራሳቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

(ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬም ባለፉት ቀናት በተለያዩ ጥፋቶች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን የመያዙ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ገልጿል፡፡ የትላንት የዩኒቨርሲቲዎች አዳርም ሰላማዊ ነበር፤ ከተደረጉ ውይይቶች በኃላ ወደ ትምህርት የተመለሱ ተማሪዎች ቁጥርም በእጅጉ እየተሻሻለ ነው ብሏል፡፡

(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#InjibaraUniversity

የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠልና የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ለማስጠበቅ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመጡ ተማሪዎች መካከል ስምምነት ላይ ተደረሰ!
.
.
በተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረውን ስጋት ለመቅረፍ ከሰኞ ማለትም ከቀን 08/02/12 ጀምሮ ምክክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

በምክክሩ ላይ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከክልልና ከዞን የተወከሉ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር አካላት፣ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ሁሉም ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በውይይት ሂደቱም በዋናነት በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚከሰቱት አላስፈላጊ ግጭቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሊንፀባረቁ እንደማይገባና ተማሪ ጥያቄ ካለው በሰለጠነ መንገድ ማቅረብ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ከሁሉም አካባቢ የመጡ ተማሪዎች ተቻችለውና ተከባብረው ለዩኒቨርሲቲውና ለሀገር ሰላም በጋራ መቆም እንዳለባቸውም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በመጨረሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕ/ር ብርሃኑ በላይ እና የሀገር ሽማግሌዎች ለተማሪዎች ምክር ሰጥተው፤ ለተገኘው ሰላምና በጋራ የመቆም መንፈስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ከነገ ማለትም ከ12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

(Injibara University)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በእንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ከነገ ዓርብ 12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከAAU ቲክቫህ ቤተሰቦች...

"አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ (AAU 6 ኪሎ) ተማሪዎችን ሰብስበው ካናገሩን በኃላ ሁሉም ነገር ተረጋግቶ ወደ ዶርም ተመልሰናል። የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከዛ ውጪ እንደሚባለው #የተጋነነ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም። ፕሬዝዳንቱም የሚያረጋጋ ንግግር አድርገዋል። ለተፈጠረውም ነገር ተማሪዎችን ይቅርታ ጠይቀዋል። በአሁን ሰዓት ተዘግተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው በሮች በሙሉት ተክፍተዋል። L(Tikvah Family-AAU)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia