TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጥብቅ ማሳሰቢያ ~ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፖሊስ ነን ባዮቹ ጥቃት አድራሾች ክስ ሳይመሰርቱም፣ ሳይመሰረትባቸውም ለምን ተለቀቁ?

እሁድ ጥቅምት 23 ምሽት፣ መነን አካባቢ የፖሊስ ደንብ ልብስ ሳይለብሱ ነገር ግን ፖሊስ ስለመሆናቸው የተናገሩ ግለሰቦች አንዱ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተሰምቷል፡፡
ግለሰቦቹ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢወሰዱም ፖሊስ ነን ባዮቹ ክስ ሳይመሰርቱም፣ ሳይመሰረትባቸውም ተለቅቀዋል፡፡ ጉዳዩን አይቶታል የተባለው የመነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የደረሰኝ መረጃ የለም፣ አጣራለሁም ብሏል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ(ቦጌ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ! ከከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ፦ . . ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ (ቦጌ) ሴትነትን ከፍ ለማድረግ በሠሯቸው ሥራዎች፥ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቀረት ባከናወኗቸው ተግባራት፥ በአካባቢ ጥበቃ እና በአረንጓዴ ልማት መስክ ባኖሯቸው ዘመን ተሻጋሪ አሻራዎች፥ የእናቶችን እና ሕፃናትን ሞት ለማስቀረት ዕውን ባደረጓቸው የጤና ተቋማት እና…
ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ...

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፥ የልማት አምባሳደር፥ የሴቶች እናት እና የተመራማሪ ዶ/ር ቦጋለች ገብሬን የቀብር ሥነ ሥርዐት የሚያስፈፅም ኮሚቴ አቋቁሞ እየሠራ መሆኑን የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። የዞኑ አስተዳደር እንደገለፀው የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አስክሬን ሀገር ውስጥ ሲገባ የጀግና አቀባበል ለማድረግ እና ብሔራዊ የአስክሬን ሽኝት ፕሮግራም ለማዘጋጀት የተቋቋመው ኮሚቴ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Prof. Kindeya G/Hiwot:

"It is now under control according to the park authorities & local people! They suspected another area & checking it."

Photo C. Tigray Communication Bureau and Goitom Negash

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA -- የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር የብሄርና የሃይማኖት ብዝሃነትን በአግባቡ ለማስተዳደር የሃይማኖት አባቶችና የህብረተሰቡ ሚና በሚል ርዕስ ያዘጋጀዉ ክልል አቀፍ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነዉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIGJIGA

በሶማሌ ክልል ህጋዊ እውቅና ይዘው የሚንቀሳቀሱ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ውይይት አደረጉ። ድርጅቶቹ ትናንት በሶማሌ ክልል ር/መስተዳደር ጽህፈት ቤት ባደረጉት ውይይት በቀጣይ በጋራ የሚሰሩባቸው ጉዳዮች በጹሁፍ የሚያዘጋጁ አምስት አባላት መሰየማቸውን የሶማሌ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ መሀመድ ኡመር ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመረጡ አምስቱ አባላት የሚያዘጋጁትን ሰነድ በጋራ ውይይት ዳብሮ ሁሉም ከተቀበሉት በኋላ ወደ ቀጣዩ የስምምነት ምእራፍ ይሸጋገራሉ ተብሏል።

(ኢዜአ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመርሳ ከተማ ወጣቶች...

የመርሳ ከተማ ወጣቶች በጊራናና አካባቢዋ የተከሰተዉን የአንበጣ መንጋ በመከላከልና ከህዝባቸዉ ጎን ለመቆም በአሁን ሰዓት ወደ ጊራና እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ በጥቅምት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል!

የጥቅምት ወር የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ። የጥቅም ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 18 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡንም አስታውቋል። ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዚህ ወር የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በዜሮ ነጥብ ሁለት ከመቶ ቅናሽ ታይቷል።

በወሩ ቲማቲም፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ጎመን፣ ካሮት፣ ምስር፣ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት እና ወተት አይብና ዕንቁላል መጠነኛ ቅናሽ አሳይተዋል። ባለፉት ተከታታይ ወራት ምግብ ነክ በሆኑ ምርቶች ላይ የማያቋርጥ ጭማሪ መስተዋሉ ይታወቃል።

በጥቅምት ወር ደግሞ ምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ መጠነኛ ጭማሪ መስተዋሉን ኤጀንሲው አመልክቷል። በሌላ በኩል ዋና ዋና የእህል አይነቶች በተለይ ጤፍ፣ ገብስ፣ ማሽላ፣ በቆሎና የስንዴ ዱቄት እንዲሁም የበሬ ስጋ የተጋነነ ባይሆንም በተያዘውም ወር የዋጋ ጭማሪው እንደቀጠለ ነው።

ምክንያቱ ደግሞ የልብስና መጫሚያ፣ የቤት ኪራይ፣ ማገዶና ከሰል፣ የቤት ዕቃዎችና ማስጌጫዎች፣ የቤት መስሪያ እቃዎች፣ ሕክምናና ትራንስፖርት ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ መሆኑን ኤጀንሲው ጠቅሷል።
አጠቃላይ የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጻር ተመሳሳይ መሆኑን አስታውቋል።

(ENA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሞት ፍርደኛ ኢትዮጵያዊያን በሳውዲ!

በሳዑዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው 2 ኢትዮጵያዊያን እና ሌሎችም እስረኞች ምሕረት እንዲደረግላቸው የሳዑዲን መንግሥት እየጎተጎተ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገለፀ፡፡

ከሰሞኑ የሞት ፍርድ የተበየነባቸውን ሁለት ኢትዮጵያዊያን እና ሌሎች ፍርድ የተቀበሉ ኢትዮጵያዊያንን መጎብኘቱን ያሳወቀው በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለፍርደኞቹ ጠበቃ አቁሞ እንደሚከረራከር ገልጿል፡፡

በሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥረው የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊያን አቅም ስለሌላቸው ጠበቃ ባለማቆማቸው ያለጥፋታቸው ፍርድ እንደተላለፈባቸው በመጠቆም መንግሥት ጠበቃ አቁሞ ይግባኝ እንዲልላቸው ተማፅነዋል፡፡

ኤምባሲውም የፍርድ ውሳኔውን ቅጂ ያገኘ ሲሆን፣ ጠበቃ አቁሞ ዜጎቹ እንዲከራከሩ ለማድረግ እንደሚጥር ገልጿል፡፡

ፍርደኞቹ ለሶስት አመት ማረሚያ ቤት እንደቆዩ፣ ለ16 ጊዜ ያህል ፍርድ ቤት ሲቀርቡም ሶስት ጊዜ ብቻ ቃላቸውን እንደሰጡ ለኤምባሲው ተወካይ አስረድተዋል፡፡

(አሐዱ ቴሌቪዥን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀይማኖት መሪዎች የህዝቦችን መስተጋብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለፁ። የህዝቦች የእስር በርስ መስተጋብር እንዲጠናከርና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ፡፡ በዛሬው እለት ከኦሮሚያ ክልል ሁሉም አካባቢዎች የተወጣጡ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካች የተገኙበት የሰላም ኮንፍረንስ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡

(ዋልታ ቴሌቪዥን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

በመርሳ ከተማ የአንበጣ መንጋ እየተዛመተ ሲሆን ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ የአንበጣውን ጉዳት ለመከላከል የአካባቢው ህብረተሰብ፣ ተማሪዎች እና የክልሉ ልዩ ሀይሎች እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡

@tsegawolde @tikvahethiopia
ወሎ ዩኒቨርሲቲ👌

ከ900 በላይ የሚሆኑ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአማራ ክልል ቃሉ ወረዳ የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰብ እና በአካባቢ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በመከላከል ተሳትፎ አደረጉ። የአንበጣ መንጋውን በመከላከሉ እና የደረሱ ሰብሎችን በመሰብሰቡ ተግባር የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳን ዶ/ር አባተ ጌታሁን ጨምሮ፤ ምክትል ፕሬዝዳንቱና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው የስራ ሃላፊዎችም ተሳትፎ አድርገዋል።

(ወሎ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አመራሮች በዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ!

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ4ኛው የወንጀል ችሎት በአበርገሌ ወረዳ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን ከፍተኛ አመራሮች በዋስ እንዲለቀቁ ወስኗል።

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ4ኛው የወንጀል ችሎት በአበርገሌ ወረዳ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ከፍተኛ አመራሮች በዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ።

ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ እንዲፈቱ የወሰነው መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ወድቅ በማድረግ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ከኢትዮ ቴሌኮም የስልክ ልውውጥ መረጃ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አልደረሰልኝም የሚልና በወረዳው የአራት ተቋማት የኦዲት ምርመራ ውጤት አለመድረሱን በመጥቀስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ነበር።

ተጠርጣሪዎችም የእጅ ስልካቸውን ከሰጡ ከ30 ቀናት በላይ መሆኑንና ኦዲት የሚደረጉ ተቋማትም በዋና እና ምክትል ሃላፊ የሚመሩ በመሆናቸው የዋስትና መብት እንደማያስከለክል ጠቅሰው ተከራክረዋል።

ችሎቱ ግራ ቀኙን ከመረመረ በኋላ ተጠርጣሪዎች በዋስ ቢወጡ በኦዲት ስራውም ሆነ የስልክ ቅብብሎሹን ለማጣራት የሚያሳድሩት ተጽእኖ ሊኖር አይችልም በማለት በ15 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወስኗል።

የዋስትና መብት የተሰጣቸውም የአበርገሌ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፣ የአዴፓ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ በአዴፓ ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት አደረጃጀትና የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከመስከረም 25/2012 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

https://telegra.ph/ETH-11-06-2

(ENA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መከላከያ እና የትግራይ ልዩ ኃይል ገብተዋል! (ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም) "ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እሳትና ሰው ሲታገሉ አድረዋል። የዱር ሕይወት ጀግኖች ዋጋ ከፍለው ስለ ቃፍታ መዳን ተስፋ ሰጥቸውኛል። መከላከያና የትግራይ ልዩ ኃይል ገብተዋል።" (ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም) @tsegabwolde @tikvahethiopia
የቃፍታ ሽራሮ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጠፍቷል!

ከኢትዮጵያ ዱር እንሰሳትና ጥበቃ ባለስልጣን በተገኘው መረጃ በቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከአንድ ቀን ተኩል በኋላ በመከላከያ ሰራዊት እና በትግራይ ክልል ርብርብ መጥፋቱን ለማወቅ ተችሏል። 2,170 ኪሎ ሜትር ስኴር ያረፈው ፓርክ በቃጠሎው ምክንያት 1,500 ሄክታር ላይ ያለ ሳር ወድሞበታል። በፓርኩ ውስጥ የንብ ማር ለመቁረጥ በተደጋጋሚ እሳት ሰለሚለኮስ ፓርኩን ለእሳት ቃጠሎው አየተጋለጠ ይገኛል። በፓርኩ ውስጥ በርከት ያሉ ዝሆኖች ይገኛሉ።

(ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት-ካፒታል ጋዜጣ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሦስቱ ሀገሮች በዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ መንገዶች ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ተቀናጅተዋል!" - SSNA

ግብጽ ከኡጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ለማሰናከል እየሠራች መሆኗን የደቡብ ሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ የሰነድ ማስረጃውን ከአንድ ታማኝ የኡጋንዳ የቀድሞ ደኅንነት ባልደረባ ማግኘቱንም ገልጧል፡፡ ሦስቱ ሀገሮች በዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ መንገዶች ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ተቀናጅተዋል፡፡ ግብጽ ግድቡን ካጠቃች ሁለቱ ሀገሮች ወታደራዊ ጦር ሠፈር ይፈቅዳሉ፡፡ ግብጽ በምላሹ የኡጋንዳው ወዳጅ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በሥልጣን እንዲቆዩ ወታደራዊ ድጋፍ ታደርጋለች፡፡ ዘገባው ከገለልተኛ ምንጭ አልተጣራም፡፡

https://southsudannewsagency.org/index.php/2019/11/05/leaked-document-cairo-kampala-juba-conspiring-against-addis-ababa/

(WazemaRadio,SSNA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍሬው አስራት በ @tikvahethsport

ዓለም አቀፉ የስፖርት ጋዜጠኛ እና የረጅም ጊዜ የቤተሰባችን አባል ፍሬው አስራት ከመጪው አርብ ጀምሮ ለስፖርት ወዳድጆች የቤተሰባችን አባላት የተመረጡ መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

ይህ የስፖርት ገፃችን ነው👉 @tikvahethsport
ጠቃሚ መረጃ!

ስለ አንበጣ መንጋ ምን ያህል ያውቃሉ?


(ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን)

• አንድ ጎልማሳ የበረኃ አንበጣ በየቀኑ የራሱን ክብደት ያህል ማለትም ሁለት ግራም ምግብ የሚበላ ሲሆን፣ አንድ አማካይ ብዛት ያለው የበረኃ አንበጣ መንጋ የ10 ዝሆኖች ወይም የ25 ግመሎች ወይም የ25ሺህ ሰዎች በቀን ውስጥ የሚመገቡትን ምግብ ይጨርሳል።

• በወረርሽኝ ወቅት የበረኃ አንበጣ መንጋ እሰከ 29 ሚሊየን ካሬ ኪ.ሜ የሚሸፍን ሰፊ መሬት በመያዝ ወደ 60 አገራት ውስጥ የመሰራጨት አቅም አለው። ይህም የዓለማችን 20 በመቶ መሬት ማለት ሲሆን፣ የዓለማችንን 10 በመቶ ሕዝብ ኑሮ ያስተጓጉላሉ ማለት ነው።

• ሴት የበረኃ አንበጣ ከ95-158 እንቅሏል ትጥላለች።

• የበረኃ አንበጣ መንጋ በነፋስ እየታገዘ በሰዓት ከ16-19 ኪ.ሜ ሊጓዝ የሚችል ሲሆን፣ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ5-130 ኪ.ሜ መጓዝ ይችላል።

• በአንድ ካሬ ኪ.ሜ ስፋት ባለው መሬት ላይ የበረኃ አንበጣ መንጋ ውስጥ ከ40-80 ሚሊዮን የሚገመቱ አንበጣዎች ይገኛሉ።

• የበረኃ አንበጣ መንጋ በአየር ሁኔታ እና ሥነ ምኅዳር ላይ መሠረት በማድረግ ከሦስት እስከ አምስት ወራት በሕይወት መቆየት ይችላል።

• እ.አ.አ እስከ 1921 ድረስ ሁለት ዓይነት የበረኃ አንበጣ መንጋ ዝርያዎች ብቻ ነበሩ። ሆኖም የአፍሪካ፣ የሩቅ ምሥራቅ፣ ቀይ የምሥራቅ አፍሪካ፣ ቡናማ የደቡብ አፍሪካ፣ የሞሮኮ፣ የቦምቤይ፣ የአውስትራሊያ እና የዛፍ የሚባሉ ክፍፍሎች አላቸው።

• የበረኃ አንበጣ መንጋ አጭር ቀንድ መሰል ነገር የያዙ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ዝርያዎች አሉት።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-06-3

ምንጭ:-የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ተደጋጋሚ የሆነ የአውሮፕላን ብልሽት የበረሃ አንበጣን ለመከላከል እንቅፋት እንደሆነበት የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የግብርና ሚኒስቴር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2012 ዓ.ም በጀት አመት የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡ በዚህ ወቅት ተደጋጋሚ የሆነ የአውሮፕላን ብልሽት የበረሃ አንበጣን ለመከላከል እንቅፋት መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ በትግራይ ክልል ሰባት ወረዳዎች ፣ በአማራ ክልል አስር ወረዳዎች ፣ በኦሮሚያ ክልል ዘጠኝ ወረዳዎች ፣ በሶማሌ ክልል 12 ወረዳዎች ፣ በአፋር ክልል 21 ወረዳዎችና በድሬዳዋ መስተዳደር አንድ ወረዳ ላይ ከባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የበረሃ አንበጣው ያረፈባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡

(FBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

መንግስት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚያቀርበውን ፈሳሽ ዘይት ከውጪ ሊያስገባ ነው፡፡ ዘይቱ ወደ አገር እየተጓጓዘ መሆኑንና እስከ 15 ቀን ድረስ ገብቶ እንደሚከፋፈልም ይጠበቃል፡፡ በየወሩ 33 ሚሊየን ሊትር ፈሳሽ ዘይት እንዲያስገባና እንዲያከፋፍል የተፈቀደለት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ዘይቱ ቀደም ብሎ ሲሰራጭ የነበረው እና የረጋው ዘይት በሚከፋፈልበት ዋጋ ለህብረተሰቡ እንደሚቀርብ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል፡፡

በድርጅቱ የሽያጭ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ደጀኑ ተክለ ማርያም እንደተናገሩት 1 455 ኮንቴነር ፈሳሽ ዘይት ከኢንዶኔዢያ ተገንዘቶ ወደ አገር እየተጓጓዘ ነው፡፡ 30 ሚሊየን ሊትሩ ከሚረጋው ዘይት በደረጃ ከፍ ያለና ፈሳሽ ሲሆን 3 ሚሊዮን ሊትሩ ደግሞ የተጣራ የሱፍ ዘይት መሆኑን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡ ዘይቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እንደሚከፋፈልም ተሰምቷል፡፡

መንግስት በወሰነው መሰረት በየወሩ 40 ሚሊየን ሊትር ዘይት ከውጪ ተገዝቶ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ይከፋፈላል፡፡ በቅርቡ 67 በመቶውን እንዲያስመጣና እንዲያከፋፍል የተፈቀደለት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ፈሳሽ ዘይት ብቻ እንደሚያስገባ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ዜና!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች በ12 ወረዳዎች በ128 ቀበሌዎች ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መነጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ገለጸ። በቢሮው የችግኝ ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ሂርጳ እንዳሉት የአንበጣ መንጋው ከጎረቤት ሶማሊያ የመጣ ሲሆን በሁለቱ ዞኖች ውስጥ በ23 ሺህ 323 ሄክታር ሰብል ላይ ቢታይም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tsegawolde @tikvahethiopia