የካራ ማራ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምግባ መርሃ ግብር ተቋረጠ!
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የሚገኘው ካራ ማራ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር መቋረጡ ተገለጸ። በዚህ ትምህርት ቤት የምገባ መርሃ ግብር ሊቋረጥ የቻለው በማህበራቱ የቅድመ ዝግጅት ማነስ መሆኑን የክፍለ ከተማው የትምህርት ጽህፈት ቤት ገልጿል።
ባለፉት ሁለት ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አካባቢ በሚገኘው የካራ ማራ ትምህርት ቤት በመንግስት በኩል የተመቻቸው የቁርስና የምሳ ምገባ በአግባቡ አልተካሄደም።
የካራ ማራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የአደራጃጀት ርእስ መምህር አቶ ዮናስ ሽኩር እንደገለጹት፤ ምገባው የተቋረጠው ምግቡን እንዲያቀርቡ በማህበር የተደራጁ እናቶች የንግድ ፈቃድ የላቸውም። በመሆኑም ከክፍያ አፈጻጸም ጋር ችግር በማጋጠሙ የተነሳ ምግብ አቅራቢ እናቶች የገንዘብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የእንጨት ስራ የሚሰራው ወጣት የ2,500,000 ብር እድለኛ ሆኖ ሽማቱን ተረከበ!
በደቡብ ክልላዊ ሲዳማ ዞን ይርጋለም ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ አበበ ጌታቸው በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 3ኛ ዕጣ 2,500,000 ብር እድለኛ ሆኖ ሽልማቱን ተረከበ፡፡ እድለኛው ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን የእንጨት ሥራ በማስራት ቤተሰቦቹን ያስተዳድር ነበር፡፡ በደረሰው ገንዘብም “ያላሟላኋቸው የእንጨት ማሽኖች ለመግዛትና አሁን የምንኖረው በኪራይ ቤት ስለሆነ የራሴን ቤት ለመስራት እጠቀምበታለሁ'' ብሏል፡፡
ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ

#AddisAbeba
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ እንደሚገኝ ተገለፀ። ጋዜጠኛው በፖሊስ ኮሚሽኑ ውስጥ ለመገኘቱ እንደ ምክንያት የተባለው ደግሞ በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ስብሰባ አድርጎ ሲወጣ የተሰባሰቡ ቡድኖች ጉዳት ሊያደርሱበት ሲሞክሩ ፖሊስ ደርሶ ወደ ኮሚሽኑ ግቢ እንዳስገባው ነው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ የገለፀው። የሪፖርተሩ ጋዜጠኛ ታምሩ ፅጌ ስለጉዳዩ የማጣራት ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ጋር ደውሎ ያገኘው ምላሽ፦ "አሁን ማናገር ስለማልችል መልሼ እደውልልሀለሁ" የሚል ነው።

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን አራት ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከ1ሺህ 100ሄክታር በላይ የነበረ ሰብል ማውደሙን የዞኑ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ገለጸ። መንጋውን ለመከላከል ከአጎራባች ክልልች ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ተመልክቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሲአይኤ(CIA) መፈንቅለ መንግሥት አሲሮብኝ ነበር" የኤርትራ መንግስት
.
.
የኤርትራ መንግሥት ትላንት አርብ ባወጣው ያልተለመደ መግለጫ ሲአይኤን በመፈንቅለ መንግሥት ሽረባ ይከሳል። የእስራኤል የስለለ መረብ ሞሳድንም ስም በማጥፋት ተባብሯል ይላል።
የኤርትራ መንግሥት ይህን ስኢረ መንግሥት ተሸርቦብኝ ነበር የሚለው በፈረንጆች 2011 ላይ ነው። ይህንኑ የተመለከተ ሁነኛ ምሥጢራዊ መረጃ እጄ ገብቷል ብሏል።
ምስጢራዊው የመፈንቅለ መንግሥት ሴራው በኤርትራ ውስጥ ልክ እንደ "አረቡ ጸደይ" ዓይነት ሕዝባዊ ተቃውሞና አመጽ የማስነሳት ጥንስስ ነበረበትም ብሏል።
ይህ በትግርኛ ቋንቋ ትላንት አርብ የተሰራጨው የኤርትራ መንግሥት መግለጫ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራውን ለመጎንጎን በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተሰብስበው ነበር ያላቸውን ተቋማትና ግለሰቦች በስም ሳይቀር ይዘረዝራል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ኤርትራዊያንን በገፍ እንዲሰደዱ የማሳለጥ ሥራ እንዲሰራ በሲአይኤ ይታዘዝ ነበር ይላል።
'ሴረኞቹ' የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላትም አገራቸውን ጥለው እንዲኮበልሉ ያባብሏቸው ነበር ሲልም ይከሳል። በ2009 በኬንያ ተሳትፎ ያደረገው የኤርትራ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከፊል አባላት ወደ አገር ቤት ለመመለስ አሻፈረኝ ማለታቸው ይታወሳል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-02-2

የዛሬው "የማስቻል" መርኃግብር በኢንዶኔዢያ አንባሳደር H.E Mr Al Busyra Basnur እንኳን ደና መጣችሁ መልዕክት የተከፈተ ሲሆን አንባሳደሩ በንግግራቸው እንደገለጹት የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዢያ ግንኙነት ከ1961 ጀምሮ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት የነበራቸው እንደሆነ ጠቅሰው አሁን ላይም በተለያዩ ዘርፎች አብረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ለተሳታፊዎች አብራርተዋል፡፡ ወጣቱ ትልቅ አቅም አለው ያሉት አምባሳደሩ ሀገራቸውም ለኢትዮጵያ ወጣቶች የትምህርት ዕድል በመስጠትና የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት እየደገፈች ትገኛለች ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንዶኔዢያ የወጣቶች ህብረት ተመስርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የተናገሩት አምባሳደሩ ዛሬ ላይ ለተገኙት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦችም የዚህ ህብረት አባል እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡ በንግግራቸው መጨረሻም ኢትዮጵያና ኢንዶኔዢያ በወጣቶቻቸው ጥንካሬ ትልቅ ሀገር ይሆናሉ ብለዋል፡፡
@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!
@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!
#ማስቻል
ሁለተኛው ክፍል የነበረው የ Google digital skill ሥልጠና በ Africa 118 የተሰጠ ሲሆን በሥልጠናው አሁን ላይ ስላለው የዲጂታል ዓለም እና እንዴት ክህሎታችንን በማዳበር መጠቀም እንደሚቻል እንዲሁም ስለ መሰረታዊ digital marketing መግቢያ የሚሆን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን በ Africa 118 አማካኝነት ተሰጥቷል፡፡

በሦስተኛው ክፍል አቶ ክብረት አበበ የጠብታ አንቡላንስ ባለቤት ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደው ያለፉበትን መንገድ ከተሞክሯቸው ጋር በማዛመድ ስለ ማህበራዊ ሥራ ፈጠራ ገለጻ አድርገዋል፡፡
አቶ ክብረት ሲናገሩ አሁን ላለው ስኬታቸው ቤትና ንብረታቸውን መሸጣቸውን አስታውሰው አሁን ላይ ግን ጠብታ ከድርጅት አልፎ ፍልስፍና ለመሆን በቅቷል ያሉት አቶ ክብረት ይህም በሀገር ደረጃ ሲገለጽ የሁላችንም ጠብታ ለዚህች ሀገር ያስፈልጋታል በማለት አብራርተውታል፡፡
ወጣቱን አንቀው የሚይዙ በርካታ ውስብስብ ነገሮች አሁን ላይ ቢኖሩም አገልጋይነትን ከትርፋማነት ጋር ያዋሀደ ሥራ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ብቸኛው ችግሮቻችንና ድህነትን የምናሸንፍበት መሳሪያችን ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ወጣት ቃለወንጌል ተስፋዬ ወጣቱ መጠቀም የሚገባቸውን ዕድሎች እንዴት ማግኘት አለበት የሚለውን እሱ ያገኛቸውንና የተሳተፈባቸውን እድሎች በማንሳት ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን የዩዝ ቱዩዝ አላማውንና በቀጣይ ሊሰራ ስላሰባቸው ነገሮች ገለጻ አድርጓል፡፡

TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስቻል #enabling በዚህ ፕሮግራም 50 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሚሳተፉ ሲሆን በሀገራዊና አለማቀፍ ዕድሎች፣ በማህበራዊ ሥራ ፈጠራና ክህሎትን በማሳደግ ላይ ምክክር ይደረጋል። በፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የGoogle Digital Skill ሥልጠናና ሰርተፊኬት ይሰጣል። ፕሮግራሙን TIKVAH-ETH እና ዩዝ ቱዩዝ ከተባባሪ አጋሮች…
#ማስቻል #enabling
በአጠቃላይ የመጀመሪያው የማስቻል ፕሮግራም እጅግ የተሳካ መሆኑን ዕድሉን አግኝተው የተሳተፉ ቤተሰቦቻችን ገልጸዋል፡፡ ለዚህ መርኃግብር መሳካት ኢንዶኔዢያ ኤምባሲ፣ ዩዝ ቱዩዝ ፣ Africa 118ና አቶ ክብረት አበበን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ስም ልናመሰግን እንወዳለን፡፡ በቀጣይም #ማስቻል ተጠናክሮ ለበርካታ ቤተሰቦቻችን የምንደርስበትን ዕድል ለማመቻቸት እንሰራለን፡፡ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ለወጣቶች የሚመጡ እድሎች ሲኖሩም እናሳውቃለን።
@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአጠቃላይ የመጀመሪያው የማስቻል ፕሮግራም እጅግ የተሳካ መሆኑን ዕድሉን አግኝተው የተሳተፉ ቤተሰቦቻችን ገልጸዋል፡፡ ለዚህ መርኃግብር መሳካት ኢንዶኔዢያ ኤምባሲ፣ ዩዝ ቱዩዝ ፣ Africa 118ና አቶ ክብረት አበበን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ስም ልናመሰግን እንወዳለን፡፡ በቀጣይም #ማስቻል ተጠናክሮ ለበርካታ ቤተሰቦቻችን የምንደርስበትን ዕድል ለማመቻቸት እንሰራለን፡፡ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ለወጣቶች የሚመጡ እድሎች ሲኖሩም እናሳውቃለን።
@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbeba ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ እንደሚገኝ ተገለፀ። ጋዜጠኛው በፖሊስ ኮሚሽኑ ውስጥ ለመገኘቱ እንደ ምክንያት የተባለው ደግሞ በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ስብሰባ አድርጎ ሲወጣ የተሰባሰቡ ቡድኖች ጉዳት ሊያደርሱበት ሲሞክሩ ፖሊስ ደርሶ ወደ ኮሚሽኑ ግቢ እንዳስገባው ነው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ የገለፀው። የሪፖርተሩ ጋዜጠኛ ታምሩ ፅጌ ስለጉዳዩ የማጣራት…
#UPDATE ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ባልደረቦቹ ቃላቸውን ሰጥተው ከፖሊስ ጣቢያ በሰላም መውጣታቸውን፤ በተጨማሪም የሚያስመዘግቡት ቃል ካላቸውም ነገ ጠዋት መመለስ እንደሚችሉ እንደተገለፀላቸው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ገልጿል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ የተያዘው ተጠርጣሪ ግለሰብ ጋዜጠኛ እስክንድርና ባልደረቦቹ ከፖሊስ ጣቢያው እስከወጡበት ጊዜ ድረስ እዛው ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ጋዜጠኛ በላይ ጨምሮ ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሻሻያ እየተደረገባቸው የሚገኙ በርካታ የህግ ማዕቀፎች በቅርቡ ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል!
ማሻሻያ እየተደረገባቸው የሚገኙ በርካታ የህግ ማዕቀፎች በቅርቡ ይጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ገለጸ። ዘንድሮ ማሻሻያ ከሚደረግባቸው የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን፣ የጥላቻ ንግግር፣ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና የማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ማዕቀፍ ይገኙበታል። የሕግ ማሻሻያው ሕብረተሰቡ በፍትሕ ስርዓቱ አመኔታ እንዲኖረው ከማድረግ ባሻገር በዘርፉ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ ሕዝቦችን አንድነት ለችግር እያጋለጡ ያሉ ጉዳዮች ትኩረት የተሰጣቸው ሲሆን የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ የሚያስችሉና ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ የህግ ማዕቀፎች በበጀት ዓመቱ ይጸድቃሉ ተብለው ከሚገመቱት መካከል እንደሚገኙበት ተገልጿል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-6
Via SRTA

#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ
"ከ6 ወር በላይ በመዲናዋ መሬት አጥሮ የሚያስቀምጥ ማንኛውም አካል መሬት ይወረሳል" - ኢንጂነር ታከለ ኡማ
በአዲስ አበባ ከተማ ከስድስት ወር በላይ መሬት አጥረው የሚያስቀምጡ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግስታት መሬት እንደሚወረስ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።
ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ በዘጠኝ ክፍለ ከተማዎች የሚገነቡ ከ20 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረዋል። በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር ከስድስት ወር በላይ በከተማዋ ያለምን ግንባታ መሬት አጥሮ የሚያስቀምጥ ማንኛውም አካል መሬቱ እንደሚወረስበት ማረጋገጥ አፈልጋሉ ብለዋል።
ሀብት የሚባክንበት ወቅት አልፏል ያሉት ምክትል ከንቲባው፥ በእያንዳንዱ ቦታ በመንግስት እና በባለህብቶች ግንባታ ሳይካሄድባቸው ታጥረው የተቀመጡ መሬቶች በጥናት ተለይተዋል ብለዋል። በመሆኑም ግንባታ ሳይካሄድባቸው የሚገኘት እነዚህ መሬቶች በቅርቡ ወደ መሬት ባንክ ይመለሳሉ ብለዋል።
Via ኤፍ ቢ ሲ

እንዳታስቡ የሚከለክሏችሁን አታዳምጡ!
"ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ማህበራዊ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህ ማህበራዊ ችግሮች ግን በራሳቸው ችግር ብቻ አይደሉም፤ ለታያቸውና ማህበራዊ ሥራ ፈጠራ ለገባቸው ችግሮቹ ትልልቅ ዕድሎች ናቸው፡፡ ችግር ካለ መፍትሔ እናስባለን፤ መፍትሔው ሲገኝ ደግሞ ማህበረሰቡን ይጠቅማል፤ ሀገርን ይጠቅማል እኛም እንጠቀማለን፡፡ ስለዚህ መፍትሔ አስቡ፤ እንዳታስቡ የሚከለክሏችሁን አታዳምጡ!" አቶ ክብረት አበበ (CEO of Tebita Ambulance)
#ማስቻል #enabling #IndonesiaEmbassy #YouthtoYouth #ቲክቫህኢትዮጵያ

በጎንደር የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ!
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል፡፡ ሩጫው የተዘጋጀው ለቅዱስ ሩፋኤል የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት ድጋፍ ለማሰባሰብ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
መነሻውን ማራኪ አድርጎ በአዘዞ አየር ማረፊያ (ማይልኮ ሎጂ) መድረሻውን ያደረገ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ነው የተካሄደው፡፡ ለሩጫው 1 ሺህ 800 የሚሆን የመሮጫ ‹ቲሸርት› መሸጡ ተገልጿል፤ በሩጫ ውድድር የውጭ ሀገር ዜጎችም ተሳትፈዋል፡፡
የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩን ያዘጋጀው ማይልኮ ሎጂ ነው፤ የሯጮችን መለያ ቲሸርት በማሳተምና ለአሸናፊዎች ሽልማት በማዘጋጀት ጭምር ነው ውድድሩን ያዘጋጀው፡፡
በውድድሩ 1ኛ እና 2ኛ የሚወጡት ብስክሌት፣ ሦስተኛ የሚወጣው ደግሞ ሙሉ የስፖርት ትጥቅ እንደሚሸለሙ ታውቋል፤ በተጨማሪም 1ኛ የሚወጣው ለ6 ቀን፣ 2ኛ የሚወጣው ለ4 ቀን እና 3ኛ ለሚወጣው ለ2 ቀን በማይልኮ ሎጂ ሙሉ ወጭ ተሸፍኖ መስተንግዶ እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ደግሞ ‹‹እኛን ለመርዳ ስለሮጣችሁ እናመሰግናል›› እያሉ ነው፡፡
ትምህርት ቤቱ ከለጋሽ አካላት የሚያገኘው ገቢ በመቀነሱና የተማሪዎችን መሠረታዊ የትምህርት ግብዓቶች ለማሟላት የበጀት እጥረቱን ለመቅረፍ የሩጫ ውድድሩን እንዳዘጋጀ ታውቋል፡፡ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅች፣ የመንግሥት ተቋማትና ግለሰቦች ድጋፍ እንዲያደርጉለት ጥሪ ማቅረቡን አብመድ ዘግቧል፡፡
Via AMMA

የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በዶሃ በነበራቸው የሥራ ቆይታ ወቅት በሚሲዮኑ ተገኝተው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዉን እና የአገልግሎት አሰጣጡን ተመልክተዋል። በኮሚዩኒቲው ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያንንም አነጋግረዋል።
ምንጭ፦የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዶሃ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዶሃ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ይታወቁ የነበረው በአካል ላይ ጥቃት በማድረስ፣ አሰቃቂ የማሰቃየት ተግባር በመፈጸም ጭምር ነበረ" - ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር
.
.
• ኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድ ዓመት በፊት አዲስ የፖለቲከ ምዕራፍ ተከፍቷል። የተፈጠረውን መልካም ዕድል በመጠቀም በአገር ውስጥ የዴሞክራሲ ተቋማትን በአዲስ መልክ ለማደራጀትና ለማጠናከር ለሚደረገው ስራ የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት የቀረበልኝን ጥሪ በበጎ መልክ ለመቀበል ወስኛለሁ።
• አሁን የደረስንበት ምዕራፍ በብዙ ትግል የተገኘ ነው። ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን፣ ደህንነታቸውን፣ አካላቸውን፣ ንብረታቸውን ያጡበት ሂደት ነው።
• በመሆኑም በእዚህ ወቅት ያለን ሰዎች ደግሞ ይህንን ጊዜ በኃላፊነት ስሜት ተረክበን የምንችለውን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን። ወደእዚህ ተመልሼ በእዚህ ስራ ላይ ለመሰማራት የወሰንኩትም በእዚሁ ስሜት ነው።
• የዴሞክራሲ ተቋማት ተብለው የሚታሰቡት እንደምርጫ ቦርድ፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የመሳሰሉት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ስር ሆነው የመንግስት መጠቀሚያ መሳሪያ ወይንም የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ እየሆኑ ሲያገለግሉ እንደነበሩ ይታወቃል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-03-2
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ

#ATAYE
በአጣዬ ከተማ አንድ ኮንቲነር ልባሽ ጨርቅና ሺሻ በሐሰተኛ ሰነድ በተሽከርካሪ ጭኖ ሲያጓጉዙ የነበረ ግለሰብ በተጠርጣሪነት መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታወቀ።
በቅርንጫፉ የህግ ተገዥነት ተወካይ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ እንድሪስ መሃመድ እንደገለጹት ግለሰቡ የተያዘው ጥቅምት 21/2012ዓ.ም. ነው።
የተያዘው ተጠርጣሪው ግለሰብ ኮድ 3-25275 ኢት የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ህገ ወጥ የሆነው እቃ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲያጓጉዝ ነበር ሾፌር መሆኑን አመልክተዋል።
የአካባቢው ህብረተሰብ በሰጠው ጥቆማ ተሽከርካሪ ሲፈተሽ ኮንቲነሩ ሙሉውን ልባሽ ጨርቅና የሚጨሰው ሺሻ ጭኖ መገኘቱን አስረድተዋል።
ሾፌሩ በፖሊስ ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ያመለከቱት አቶ እንድሪስ “በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ስም የተዘጋጀ ሐሰተኛ የይለፍ ሰነድም ይዞ ተገኝቷል “ብለዋል፡፡
የእቃው ብዛትና ግምት ቆጠራው ሲጠናቀቅ እንደሚገጽና ህብረተሰቡ ህገ ወጦችን ለመከላከል የሚያደርገው ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ከሳምንት በፊትም 340 ሺህ ብር ግምት ያለው ህገ ወጥ የግንባታ እቃ መያዙም ተመልክቷል፡፡

Forwarded from TIKVAH-SPORT
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ፕሮግራም . . . . . .
የኢትዮጵያ ብሔራ ቡድን ከፊታችን ላለበት የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ የምድቡ ሁለት ከባድ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ልምምዳቸውን በመቀሌ የሚያካሂዱ ይሆናል ፡፡
በዚህም መሰረት በኢንስትራከተር አብርሀም መብርሀቱ የሚሰለጥኑት ዋልያዎቹ ፕሮግራማቸው የሚከተለውን ይመስላል ፡፡
ጥቅምት 24 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ መቀሌ በማቅናት በዚሁ ዕለት ልምምዳቸውን ማምሻውን የሚያደርጉ ይሆናል ፡፡
ህዳር 1 - ልምምዳቸውን በማድረግ ከቆዩ በኋላ ዋልያዎቹ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ ይሆናል ፡፡
ህዳር 2 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዕለተ ማክሰኞ የመጀመሪያ ተጋጣሚው ወደ ሆነው ማዳጋስካር አንታናናሪቮ የሚጓዝ ይሆናል ፡፡
ህዳር 6 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ከማዳጋስጋር ጋር የሚያደርግ ይሆናል ፡፡
ህዳር 7 - ዋልያዎቹ የመክፈቻ ጨዋታቸውን ባደረጉ ማግስት በዕለተ እሁድ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ ይሆናል ፡፡
ህዳር 8 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛውን ወሳኝ ጨዋታ ለማድረግ ወደ መቀሌ ለዝግጅት በረራውን ያደርጋል ፡፡
ህዳር 9 - ዋልያዎቹ የምእራብ አፍሪካዋን ከባዷን ኮትዲቯር የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል ፡፡
Via #FirewAsrat
@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH

ጋዜጠኛ እና የአዲስ አበባ ባለደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆነው እስክንድር ነጋ ትላንት በበርካታ ወጣቶች ተከቦ እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጧል!
"ትናንት ቅዳሜ ምሽት 1፡00 አካባቢ፤ ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው ቢሯችን ስብሰባ ጨርሰን ስንወጣ ነው የተወሰኑ ወጣቶች ናቸው የከበቡን" ይላል እስክንድር። እስክንድር ቁጥራቸው ከ10 በላይ ይሆናል ያላቸው ሰብሰብ ያሉ ወጣቶች ከቢሮው ውጪ ደጃፍ ላይ ጠብቀው እርሱንና አራት የባልደራስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን እንደከበቧቸው ያስረዳል። «አልፈናቸው ስንሄድ በከበባ መልክ ተከትለውናል። እንቅስቃሴያቸው አስጊ ስለነበር ወደ ኋላ ተመልሰን ፖሊስ ይዞ እንዲጠይቅልን ሙከራ አድርገናል። ቢሆንም አንዱ ብቻ ነው በፖሊስ ቁጥጥር ሥራ መዋል የቻለው።
More👇
https://telegra.ph/BBC-11-03-2
Via BBC አማርኛው አገልግሎት

በአዲስ አበባ የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር 12ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኮንፈረንስ መካሄድ የጀመረው ሰሞኑን በተከሰተው የጸጥታ መጓደል ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት አብርሀም ፍቃዱ እንደገለጸው ማህበሩ በከተማዋ ለሚገኙ የደቡብ ተወላጆች ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያችሉ ተግባራትን ሲየከናውን ቆይቷል፡፡ ለአብነትም በጌዲኦና ጎፋ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት ከ500 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የወጣት ማዕከላትን በቁሳቁስ ለማደራጀት ግምቱ ከ700 ሺህ ብር በላይ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-03-3