TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢንጂነር ታከለ ኡማ...

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ከሃላፊነት እንዳነሷቸው ነግረዋቸዋል፡፡ በምትካቸው አዳነች አቢቤን እንደሚተኩም ከ3 ቀናት በፊት ለታከለ ገልጸውላቸዋል- ብሏል አዲስ ስታንዳርድ በዘገባው፡፡ አዳነች የኦዴፓ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የፌደራሉ ገቢዎች ሚንስትር ናቸው፡፡ ኢንጂነር ታከለ ለምን ከሃላፊነት እንደተነሱ አልታወቀም፡፡

በሌላ ዜና...

ኢሕዴግን የማዋሃድ ሃሳብ የኦዴፓን ሥራ አስፈጻሚ ለሁለት ከፍሎታል- ብሏል ይኼው ዘገባ፡፡ ዛሬ የተሰበሰበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በዚሁ ጉዳይ ላይ ጭምር ይመክራል፡፡

Via Addis Standard/wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AFAR

በአፋር ክልል ነዋሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዙ ሰልፎች በስምንት ወረዳዎች ተካሄዱ። የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንደገለጸው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የነበረውን ጥቃት በማውገዝ ሰልፎቹ ትናንትና ዛሬ  በወረዳዎቹ ተደርገዋል። ሰልፎቹ ትናንት በአዋሽ፣ በገዋኔና ቡሪሙዳይቶና አፋምቦ ወረዳዎች ነበር። ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፎች በበራህሌ፣ አብአላ፣ በመጋሌና ኢረብቲ ወረዳዎች ዛሬ ተካሂደዋል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በዚሁ ወቅት ”የሽብር ጥቃቶችና የግፍ ግድያዎች በአስቸኳይ መንግሥት ያስቁምልን!”፣ ”ወንጀለኞች ለሕግ ይቅረቡ!”  የሚሉ መፈክሮችን በዋነኛነት ይዘው ነበር።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የክልሉ መንግስት አፋርና ኢሳ በሰላም የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል"— የአፋር ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
.
.
የአፋር ክልል መንግሥት አፋርና ኢሳ በሰላም የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። ክልሉ ሰሞኑን በአፋምቦ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አህመድ ሱልጣን እንደተናገሩት ክልሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረቱን ይቀጥላል። ክልሉ  ከኢሳ ጋር ብቻ ሳይሆን፤ ከአጎራባች አማራ፤ ኦሮሚያናትግራይ ክልሎች  ጋርም በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን የማህበረሰቡን መሪዎች በማሳትፍ  መፈታታቸውን አውስተዋል። ሰሞኑን በአፋምቦ የተከሰተው ድርጊት ግን ግጭት ግን፤ ‘’እንደ ትናንቱ የሳርና ውሃ አድርጎ መውሰድ እውነታውን አያሳይም‘’  ብለዋል። በአፋምቦ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ 18 ሰዎችና 36 ሰዎች ደግሞ የቆሰሉበት ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህወሓት መግለጫና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምላሽ፤ የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤትም ምላሽ ሰጥቷል፦

የሕወሓት/TPLF/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሰባት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ስብሰባ በማጠናቀቅ መግለጫ አውጥቷል። ህወሓት በመግለጫው “እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም ከተዋሃዱም ኢህአዴግ ከማፍረስ ባሻገር ሃገርን ያፈርሳል” ብልዋል።

የኢህአዴግ ፅሕፈት ቤት በበኩሉ “ውህደቱ ሃገራዊ አንድነት የሚፈጥር መሆኑን ያካሄድኩት ጥናት አሳይቷል” ብሏል። በሌላ በኩል የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ወይም የፕሬስ ሴክሬታሪ ንጉሡ ጥላሁን በሰጡት ምላሽ፤ “በህወሓት የወጣው መግለጫ ለውጡ ከመጣላት ሳይሆን ከመጣበት ሕዝብን የማይወክል አካል የወጣ ነው” ብለዋል፡፡

ለዚህም ምክንያቱም “መግለጫውን ያወጣው ቡድን በለውጡ ምክንያት የተቋረጠበት ጥቅምና መኖሩንና የነበረው ግፍ እንዲመለስ መመኘቱ ነው” ብለዋል፡፡ ህወሓት የኢህአዴግን የውህደት እንቅስቃሴ አስመልክቶ በመግለጫው ያሰፈረውም ለዓመታት ሲያንፀባርቀው ከነበረው አቋም የተለየ እንደሆነ አቶ ንጉሡ ተናግረዋል፡፡

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የአማራ ክልል ደኅንነትና የጸጥታ ካውንስል የጋራ መግለጫና ውሳኔዎች!

በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ማንነትን ሽፋን በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የዘለቀው የጸጥታ መደፍረስ ለሰው ህይዎትና ለንብረት ጥፋት ምክንያት ሆኖ መቀጠሉ የሚታወስ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት ህግና ሥርዓትን በተከተለ አኳኋን ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎች የቅማንት ብሔረሰብን ጨምሮ ምላሽ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ ለተነሱ የማንነት ጥያቄዎችና መልሶች ቅሬታ ያቀረበ ኃይል፣ ቡድንና ማኅበረሰብ ህግና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ሀሳባቸውን፣ ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን አቅረበው መስተናገድ እየተቻለና ለዚህም በርካታ ዕድሎች ብሎም ጊዜያት ተሰጥተው እያለ በሃይል ፍላጎትን ለማሳካት መሞከር ጸረ ህገ መንግስትና የለዬለት ጸረ ሰላም ተግባር መሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-16-4

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Tayyip Erdogan | ቱርክ ሶሪያ ውስጥ ከከፈተችው ወታደራዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቱርኩ አቻቸው ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኃንን ሩስያ መጥተው እንዲያነጋግሯቸው ጋበዙ። የክሬምሊን ምንጮች እንደገለጡት፦ የቱርኩ ፕሬዚደንት የተጋበዙት በቱርክ እና ሶሪያ ጦር ሠራዊት መካከል መፋጠጥን ለማስወገድ ነው። ቱርክ ባለፉት ሳምንታት ሰሜን ሶሪያ ውስጥ በሚገኙ የኩርድ ሚሊሺያዎች ላይ ወታደራዊ ጥቃት መክፈቷ ተዘግቧል። ከዚያን ጊዜ አንስቶም ኩርዶች የሶሪያ መንግሥት እና አጋሩ ሩስያ እንዲታደጓቸው የተማጸኑ ሲኾን፤ የሶሪያ ጦር ሠራዊት ኩርዶችን በመደገፍ ላይ ይገኛል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከጎንደር-መተማ ፣ ከጎንደር-ሁመራ፣ ከጎንደር-ባሕር ዳር፣ ከጎንደር- ደባርቅ የሚወስዱ መንገዶች እንዲሁም በጎንደር ከተማና ዙሪያው ብሎም ሁሉም መጋቢና ዋና ዋና መንገዶች በማንኛውም ጊዜ ነፃ ይሆናሉ፡፡ የሕዝብ እንቅስቃሴም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ነፃ ይሆናል፡፡ ይህንን ለማደናቀፍ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።" የአማራ ክልል ደኅንነትና የጸጥታ ካውንስል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🔖እናስተዋዉቅዎ!

ውድ የNዋM የቻናላችን ቤተሰቦች አዳዲስ እና ኦሪጅናል የእግር ኳስ ማሊያዎችን ማስመጣት መጀመራችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
☞ የህፃናት እና የአዋቂዎች በፈለጉት Size
☞ በራስዎ ስም አልያም በተጫዋቾች ስም ወይም በባዶ።
☞ የሚፈልጉትን ክለብ ማሊያ Home Kit, away Kit, 3rd Kit.
☞ የሁሉም ክለብ የቀጣይ አመት ማሊያዎች፣ ቱታዎች፣የትሬኒግ ልብሶች፣የሻምፒዬንስ ሊግ እና ሊግ ኩዋሳች፣ታኬታዎች፣የበረኛ ጉዋንቶዎች እንዲህም ሌሎዎች

…ያናግሩን፣ @bilu14 @mammi_adda ላይ ይዘዙን!

Join our Channel https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEs6MglfzKeDMQQQZw

☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ! #ETHIOPIA☀️
የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 205ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው 205ኛ መደበኛ ስብሰባው የመንግስት አስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ ጥናት፤ የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት እና ከሲዳማ ብሔር ህዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዞ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ለማስፈጸም የሚያስችል የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ /ሞሽን/ እና ተጨማሪ በጀት ላይ በመወያየት ለክልሉ ምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ አሳተላልፏል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-17

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ እያሉ ከወለዱ እናቶች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር ተወያዩ!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ2011 ዓመት የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመውሰድ ላይ እያሉ ከወለዱ እናቶች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመፈተን ላይ እያሉ የወለዱ እናቶችን ትላንት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አበረታተዋል። ፕሬዚዳንቷ አራት ከሚሆኑ እናቶችና ቤተሰቦቻቸው ጋር የተወያዩ ሲሆን በውይይታቸው እናቶቹ የትምህርት ጥቅምን ተገንዝበው መውለዳቸው ሳይገድባቸው ፈተናቸውን መጨረሳቸው ለበርካታ ሴቶች አርዓያ እንደሆኑ ተናግረዋል።

”እነዚህ እናቶች በፈተና ላይ እያሉ መውለዳቸው ከትምህርታቸው ሳያስቆማቸው ፈተናቸውን በመቀጠል ትምህርት ለህይወታቸው መሰረት መሆኑን በማሳየታቸው ሊበረታቱ ይገባል” ብለዋል። በዚህ ምክንያትም እናቶቹ ለበርካታ ኢትዮጵያዊን እናቶች እርዓያ ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ በመሆኑ ለማበረታት አግኝተው እንዳነጋገሯቸው ተናግረዋል።

ከፕሬዚዳንቷ ጋር ውይይት ያደረጉት እናቶች መብራት ጋሌ ና ሊዲያ ሽብሩ በበኩላቸው፤ ፕሬዚዳንቷ እነሱን አግኝተው ማነጋገራቸው ደስታ እንደፈጠረላቸው ተናግረው ሴቶች ምንም ነገር ሳይገድባቸው ትምህርታቸውን በመከታተል ለውጤት መብቃት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በትምህርት ተቋማት የሚስተዋል ዘረኝነት ተነቅሎ መጣል ይገባዋል"- ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ
.
.
በየዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉ የጥላቻና የዘረኝነት አካሄዶች ህብረተሰቡን ያልሆነ መንገድ እንዲከተል እየደረጉት ስለሆነ ተነቅለው መጣል አለባቸው ተባለ፡፡ ይህ የተባለው በደብረብርሃን ከተማ ለ32ተኛ ጊዜ በተከበረው የመምህራን ማህበር ዓመታዊ ስብሰባ ወቅት ነው፡፡

የአመራርና የመሪ ሚና በሚል መነሻ ሀሳብ ላይ የአነቃቂ ንግግር ያደረጉት ረዳት ፕሮፌሰር ምህረት ሻንቆ እንዳሉት ትውልድ የመቅረፅ ስራ በዋንኝነት የሚወድቀው በመምህራን ላይ ነው። ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትምህርት ቤቶች እንኳን ለሌላው ሊተርፉ ቀርተው ራሳቸው የፀብና የቁርሾ መፍለቂያ እየሆኑ ነው ብለዋል ረዳት ፕሮፌሰሩ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-17-2

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#TPLF #PMOEthiopia #EPRDF

Via VOA AMHARIC
#TPLF #PMOEthiopia #EPRDF

የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫና በፌደራል መንግስቱ የተሰጠው ምላሽ የቀጠሉ ልዩነቶች የተደፋፈኑ እውነታዎች ዳግም አደባባይ የወጡበት ነው። ህወሓት ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግስቱን በከፍተኛ ሁኔታ ተችቷል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተበራከቱ፤ ጥፋት በጥፋት ላይ እየተደራረበ መጥቷል ይላል መግለጫው። የጥፋቱ መጠንና ስፋት በየቀኑ እየጨመረ ወደከፍተኛ ሀገር የመበተን ደረጃ እየደረሰ ነው ብሏል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በመግለጫው ላይ የተንፀባረቁ ሃሳቦችን አጣጥለዋል። ከለውጡ በፊት በነበሩ አመታት ኢትዮጵያ በመፍረስ አፋፍ ላይ እንደነበረች አቶ ንጉሱ አስታውሰዋል። አሁን ያለው የኢትዮጵያ አመራር የተረከበውም ችግር ነው በማለት የነበሩትን ሁኔታዎች አብራርተዋል።

በዚህ የለውጥ ሂደት ከፍተኛ ስኬቶች መመዝገባቸውን፤ ችግሮችም መኖራቸውን አስታውሰዋል። ከነዚህ ችግሮች አንዳንዶቹ ደግሞ ካለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የቀጠሉ በሽታዎች መሆናቸውን ነው የገለፁት። ያለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውጤቶች የሆኑት የጥላቻ፣ የቂም በቀል፣ የቁርሾ፣ የመለያየት፣ የመከፋፈልና የሴራ ጠባሳዎች በቀላሉ የሚለቁ አይደሉም በማለት ነው አቶ ንጉሱ ያብራሩት። እናም ለውጡ በአንድ በኩል እነዚህን የማስተካከል በሌላ በኩል ደግሞ ህብረተሰቡ የሚጠይቃቸው የመልካም አስተዳደር የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች የመመለስ ስራ መሸከሙን አንስተዋል። የህውሓት መግለጫ ግን ከዚህ የለውጥ ሂደት በተፃራሪ የቆሙ ወገኖችን አቋምን ያንፀባረቀ ነው ብለዋል።

Via VOA/ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፋር ክልል ሰመራና ሎጊያ ከተሞች በአሁን ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። የክልሉ ነዋሪዎች በንፁሃን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት አውግዘዋል። በመከላከያ ሰራዊት ከቀናት በፊት የተሰጠው ምላሽም ተገቢ እንዳልሆነ እየገለፁ ይገኛል።

PHOTO: Abu Jaefar Dalol & Twsfaye/ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰመራና ሎጊያ ቤተሰቦች/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEMERA

"Yes For Peace No for Terrorism!"

PHOTO: Abu Jaefar Dalol/TIKVAH FAMILY/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ5 ወራት 30 ትራንስፎርመሮች ተሰርቀዋል!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅት በ2011 ዓ.ም 10 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ይፋ ቢያደርግም ከግንቦት ወር ወዲህ ከ30 በላይ ትራንስፎርመሮች ተሰርቀዋል። ድርጅቱ ከመጪው ታህሳስ ወር ጀምሮ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚያደርግ የአገልግሎቱ ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አስታውቀዋል። ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ታዬ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2011 አፈጻጸምና በ2012 ዕቅድ ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከውዝፍ ሂሳብ እና ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ 21 ነጥብ 868 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 10 ነጥብ 123 ቢሊየን ብር ሰብስቧል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia