TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ረቂቅ በጀቱ ነገ ይፀድቃል! ዛሬ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ በጀቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ይፀድቃል።

*ዛሬ ጥዋት ኦነግ፣ኦብነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ በይፋ ተሰርዘዋል።

#ነገ ዓርብ ዶክተር አብይ ምክር ቤት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ📌ዛሬ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ በጀቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ይፀድቃል።

*ዛሬ ጥዋት ኦነግ፣ኦብነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ በይፋ ተሰርዘዋል።

#ነገ ዓርብ ዶክተር አብይ ምክር ቤት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ የሚገኙት 10 ክፍለ ከተሞች ምክር ቤቶች #ነገ አስቸኳይ ጉባኤዎቻቸውን ያካሂዳሉ። ምክር ቤቶቹ በአስቸካይ ጉባኤዎቻቸው የክፍለ ከተሞቹን ዋና #አመራር ሹም ሽር እንደሚያደርጉ የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ነገ ስናድግ በሰላም እንድንኖር #ዘረኝነትን አታውርሱን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ-ኤርትራ⬇️

ወደ ጦርነት ገብተው ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ግንኙነታቸውን አቋርጠው የኖሩት እና በቅርቡ ግኑኝነታቸውን ያደሱት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ #ነገ በሳዑዲ አረቢያ በሚካሄድ ስነ ስርዓት በቅርቡ የገቧቸውን #የሰላም ስምምነቶች የሚያጠናክር ስምምነት ይፈራረማሉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይን ጠቅሰው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡትም በሪያድ በሚካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የተመድ ዋና ፀሃፊ #አንቶኒዮ_ጉተሬዝ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ እንዲሁም የሳዑዲ አረቢያው ንጉስ #ሳልማን ይገኛሉ ተብሏል።

📌የስምምነቱ ዝርዝር ይዘት ይፋ አልተደረገም።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ⬇️

በአዲስ አበባ ነገ እውቅና የተሰጠው #ሰልፍ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በከተማው ሕገ ወጥ ሰልፍ የሚደረግ ከሆነ በሕግ አግባብ #እርምጃ እንደሚወሰድም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

አንዳንድ ግለሰቦች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ #መሟለት ያለባቸውን መስፈርቶች ማለትም የሰልፉ አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ፣ እንዲሁም ሰልፉ ላይ የሚገኝ የሰው ብዛት ሳያሳውቁ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ለህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት ሲባል አብዛኛው የጸጥታ ኃይል በሌላ የጸጥታ ስራ ላይ በተሰማረበት በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ አለመኖሩን ኮሚሽኑ አስታውቆ፣ #ነገ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መሟለት ያለባቸውን
መስፈርቶች ሳያሟሉ ሰልፍ ለማድረግ የተዘጋጁ አካላት ከሕገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባና ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፈው በሚወጡ አካላት ላይ ኮሚሽኑ በሕግ አግባብ #እርምጃ ለመውሰድ እንሚገደድ አስታውቋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) #ነገ ድርጅታዊ ስብሰባውን ይጀምራል። ድርጅቱ የፖለቲካ ፕሮግራሙንና ስያሜውን ይቀይራል ተብሎ ይጠበቃል። በርከት ያሉ ነባር የአመራር አባላቱንም #ያሰናብታል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት #ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ ሰብሳቢን #ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

Via-ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሁሉም የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በሙሉ፦

▪️ጥር 1 እስከ ጥር 21-TIKVAH-ETH▪️

የሰላም፣ የፍቅር እና አንድነት ሳምንታትን በመላው ሀገሪቱ አውጀን የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረግን እንገኛለን። በፌስቡክ ላይ ተፅእኖ እንዲፈጠር እያደረጋችሁት ላለው ትልቅ ስራ ምስጋና ይገባችኃል።

#ነገ_ሰኞ ሁሉም የቤተሰባችን አባል ተከታዮቹን ስራዎች እንዲሰራ በታላቅ ትህትና እንለምናለን፦

•ሰራተኞች ወደስራ ከመግባታችሁ በፊት አንዳች መልካም ስራ እንድትሰሩ፦ በጎዳና ላይ ካሉ አቅም ከሌላቸ ወገኖች አንዱን እንኳን ቁርስ ብታበሉ። አልያም እናተ ለአእምሯቹ ደስታን የሚሰጣችሁን መልካም ስራ ብትሰሩ። ስራ ቦታ በሚኖራችሁ የእረፍት ጊዜ በሀገራችን ሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ ከጓደኞቻችሁ ጋር ውይይት ብታደርጉ።

•የታክሲ ሹፌሮች በስራ እንቅስቃሴያችሁ ሰላም እና አንድነትን የሚያጎለብቱ ሙዚቃዎችን ለተሳፋሪዎች በመክፈት ተፅእኖ እድትፈጥሩ። ተሰብስባችሁ ምሳ በምትመግቡበት ወቅት ስለሰላም እና አንድነት እንድትመክሩ።

•ተማሪዎች በእረፍት ጊዚያችሁ ስለሰላም እንድትነጋገሩ። በቀጣይ ሳምንታት በተለያዩ መልካም ስራዎች ላይ ስለመሳተፍ ብትመክሩ። (በቡድን ሆናችሁ ደም ልገሳ፣ ህሙማንን መጠየቅ፣ የተቸገሩትን መርዳት...)

🔹ሁላችንም በፌስቡክ ብሄር ተኮር የጥላቻ መልዕክቶችን እና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ገለሰቦችን #Block ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላልን!!

🙏መልዕክቱ ተፈፃሚ እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነን!! በቤተሰባችን አፍረን አናውቅም!!🙏
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ #ነገ የካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባለፈው እሁድ መጋቢት 1 ቀን፤ 2011 ዓ.ም ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የመረጃ ማከማቻ ሳጥኖች ላይ የሚካሄደው ምርመራ #ነገ እንደሚጀመር የፈረንሳይ የበረራ ደኅንነት ምርመራ ባለሥልጣን (Bureau d'Enquêtes & d'Analyses) ዐስታወቀ። ባለሥልጣኑ በትዊተር ገጹ እንዳሳወቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ምርመራ ቡድን አደጋ የደረሰበትን አውሮፕላን የበረራ መረጃ መመዝገቢያ እና የአብራሪዎች ክፍል የድምጽ መቅጃ መሳሪያዎችን ይዞ ዛሬ ባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ደርሷል። በአሁኑ ጊዜም እንዴት ተቀናጅተው መሥራት እንዳለባቸው እየመከሩ ነው። የምርመራው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ላይ ለመድረስ ቀናት ሊወስድ እንደሚችል ባለሥልጣኑ ዐስታውቋል።

Via ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ለባለሀብቶች ሊሰጥ ነው፡፡ ከሆንግ ኮንግ የመጡ የባለሀብቶች ቡድን አባላት የኢንዱስትሪ ፓርኩን #ነገ እንደሚረከቡ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶችን እየተቀበለች ነው። #የኦሮሚያ እና #የሶማሌ ክልል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ #ነገ ይካሄዳል።

ፎቶ፦ Mame/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ወጣቶች ፌደሬሽን አስተባባሪነት #ነገ መስከረም 24 በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረውን የእሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ ከከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች የተሰባሰቡ ወጣቶች መስቀል አደባባይ እና አካባቢውን አፅድተዋል፡፡

ከ3 ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን በነገው ዕለትም በዓሉ ከተከበረ በኋላ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የፅዳት ዘመቻው ይካሄዳል ተብሏል፡፡

የፅዳት ዘመቻው ከ10ሩም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የወጣት ፌደሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌደሬሽን እያስተባበረው ይገኛል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia