TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ👆የዕለተ እሁዱ የማጠቃለያ ዝግጅት እጅግ ደማቅ እና በርካታ ቁም ነገሮች የተነሱበት ብዙ ሀሳቦች የተንሸራሸሩበት በተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ስለጥላቻ ንግግር የማስገንዘብ ስራ የተሰራበት ነበር። እንደተለመደው በወጣት ነብያት አማካኝነት የውይይት ሀሳብ ተነስቶ ተሳታፊዎች ሀሳብ ሰንዝረዋል። የዚህ ሳምንት የመወያያ ጉዳይ የነበረው የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነበር። የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት #StopHateSpeech በሚል ወደተቋሙ ለመጡት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የክብር ሰርተፊኬት አበርክቷል።

የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ሀሳቡን በመደገፍ እስከመጨረሻው ከTIKVAH-ETH #ጎን እንደሚቆም ገልጿል!

#ሀዋሳ_ዩኒቨርስቲ #StopHateSpeech
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ 6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ #ጎን የሚገኘው የእቴጌ መነን አዳሪ ትምህርት ቤት ለ2012 የትምህርት ዘመን በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያላቸው 500 ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የእቴጌ መነን ትምህርት ቤት እያደረገ ያለውን ዝግጅት ተመልክተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia