TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አርሲ_ሮቤ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ሮቤ ከተማ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በተከሰተው የሰላም ችግር ዙሪያ ከሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ጋር ውይይት ተካሂዷል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም የተፈጠረው የሰላም ችግር የሃይማኖት አይደለም ብለዋል።

ከዚህ በፊትም ከአሁንም፤ ከዚህ በኃላም እኛ አንድላይ ነው የምንኖረው፤ ስለዚህ እምነትን ምክንያት በማድረግ የፖለቲካ አመለካከትን ሲያንፀባርቁ የነበሩ አካላት በህግ ይጠየቁልን ሲሉ ተናግረዋል።

በስብሰባው ላይ የተገኙት የODP ሃላፊ እንደተናገሩት ከትላንት በስቲያ የተካሄደውና የተፈፀመው ነገር ሆን ተብሎ እንደሆነና፤ በዓሉን የሚያከብሩ ሰዎች ህጋዊ ባንዲራዎችን በመጠቀም በዓሉን ማክበር እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ውጪ ግን ሌሎች ያልተፈቀዱ እና እውቅና የሌላቸው ባንዲራዎችን መጠቀም ተገቢ አይደለም የተከለከለም ነው ሲሉ አሳስበዋል። እምነትን ተገን አድርገው የማህበረሰቡን ሰላም የሚበጠብጡ አካላትን ለህግ እናቀርባለን ብለዋል የODP ተወካዩ። የኦሮሞ ህዝብም ከብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለውን ሰላም እንዲጠብቅም መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ እምነት ተከታዮች ጋር በመሆን መስቀል አደባባይን አፀዱ። በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የሚከበረውን የደመራ በዓልን አስመልክቶ የከተማ ነዋሪዎች በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ እንዲያፀዱ ምክትል ከንቲባው ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል አንዳንድ ከተሞች በህገ ወጥ የመሬት ወረራ ያለአግባብ የተያዙ መሬቶችን በመያዝ ማስመለስ መቻሉን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡ በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችንና መሬቶችን ማስመለሱን ቢሮው ገልጿል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዘርፉ በህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሳትፎ የነበነራቸውን አመራሮችና ሠራተኞች ላይም እርምጃ መውሰዱን ቢሮው በ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2012 የስራ ዘመን የዕቅድ ዝግጅት የግምገማ መድረክ ላይ ገልጿል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ የሚዘጉ መንገዶች!

በአዲስ አበባ ለደመራ በዓል አከባበር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች፦ ዛሬ በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከረፋዱ 4 ሰአት ጀምሮ ተከታዮቹ መንገዶች ዝግ ይሆናሉ፦

• ከኦሎፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
• ከለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከብሄራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአምባሳደር ቲያትር ቤት ወደ መስቀል አደባባይ

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ፣ 6727 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚስን አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#JIMMA በጅማ ከተማና አካባቢው የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሰከረም 17 የመስቀል ክብረ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ ዛሬ በማፅዳት ዝግጁ አደረጉ። በከተማው በዓሉ በሚከበርበት “ሚኒ ሁለገብ ስታዲየም” በተካሄደው የጽዳት ሥራ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላትና የወጣት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ለጊፋታ እሮጣለሁ " በሚል የተዘጋጀ እሩጫ በወላይታ ከተማ ተካሄደ!

የወላይተ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለጊፋታ እሮጣለሁ በሚል የተዘገጀ የ3ኪሎ ሚትር እሩጫ ውድድር ተካሄዷል። ሩጫውን ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩንቤ እና የዞኑ ባህል ቱሪዝምና እስፖርት መምሪያ ኅላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን ሲሆኑ፤ በሩጫውም በርካታ የወላይታ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ

የወላይታን የዘመን መለዋጫ የጊፋታ በዓል #በዩኔስኮ የማስመዝገብ ጥረት መጀመሩ ተገልጿል፡፡ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንደገለጹት፤ የጊፋታን በዓል በዩኔስኮ የማስመዝገብ እንቅስቃሴ በመካሄድ ላይ ነው ብለዋል፡፡ ከመስከረም 14 እስከ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረው የወላይታ ዘመን መለዋጫ ትርጓሜ ታላቅና የመጀመሪያ ማለት እንደመሆኑ በበዓሉ ያለውን እውነታ በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚደረውን ጥረት ከፍ እንደሚያደርገው አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#AAWSA

አዲስ አባባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን “ውኃ በተሽከርካሪ እናቀርባለን“ የሚሉ ግለሰቦችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ፡፡ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንፁህ የመጠጥ ውኃ አምርቶ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት የአገልግሎት ክፍያ እንደሚሰበስብ አስታውቋል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ስልጣን ያልተሰጣቸው ግለሰቦች “ውኃ እናቀርባለን” በሚል ጥራቱ ያልተጠበቀ እና ከየት እንደተቀዳ የማይታወቅ የውኃ ሽያጭ እያካሄዱ ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

ህብረተሰቡም ከባለስልጣኑ ዕውቅና ውጭ የሆኑ ግለሰቦች ለሽያጭ የሚያቀርቡት ውኃ የጥራት ደረጃው ያልተረጋገጠ ከመሆኑም ባለፈ ለጤና ጠንቅ ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ ያለፍቃድ ውሃ በመሸጥ ላይ የተሰማሩ አካላትም ከዚህ ተግባር እንዲቆጠቡ ባለስልጣኑ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን ማሳሰቢያ በቸልታ ያለፈ እና በተግባሩ የቀጠለን ግለሰብ በህግ እንደሚጠይቅ አስታውቋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethioia
#HARAR የደመራና የመስቀል በዓል በደመቀና በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጉን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#update የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ተሰጠ። ማብራሪያውን የሰጡት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ናቸው፡፡

https://telegra.ph/TIKVAH-09-27

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethioia
#DEBRE_MARKOS

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበትን የንጉሥ ተክለሃይማኖት አደባባይ አካባቢን አፅድተዋል።

በበጎ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወጣቶች ለክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethioia
እስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና የሃይማኖት አባቶች የመስቀል በዓል የሚከበርትን አካባቢ አጸዱ!

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና የሃይማኖት አባቶች የመስቀል በዓል የሚከበርባቸውን አካባቢዎች ሲያጸዱ አርፍደዋል፡፡

በከተማዋ የቆየውንና ያለውን አብሮነት፣ መተሳሰብና አንድነት ለትውልድ ለማስተላለፍ በተግባር የአንደኛው ሃይማኖት ተከታይ ለሌላኛው ሃይማኖት ተከታይ አጋር መሆኑን ያሳዩበት ተግባር መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደምም #የደባርቅ_ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በዓል ለማክበር በሚዘጋጁበት ወቅት የመስጅድና ሌሎችም የሶላት መስገጃ አካባቢዎችን ማጽዳታቸውን የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethioia
#BONGA የካፊቾ ብሔር የዘመን መለወጫ ”ማሽቃሬ ባሮ” በዓል በቦንጋ ከተማ ተከብሯል። በዞኑ ከቀበሌ ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች ላለፉት ሶስት ቀናት ሲከበር የቆየው ይኸው በዓል ትናንት በዞኑ ዋና ከተማ ቦንጋ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተጠናቋል።

Photo: ZELALEM/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethioia
ከአንድ አካባቢ የሚመጡ ተማሪዎችን በአንድ «ዶርም» አይመደብም!

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች ቅበላ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለጸ። በተቋሙ ከአንድ አካባቢ የሚመጡ ተማሪዎች በአንድ ዶርም እንደማይመደቡ ተጠቁሟል፡፡ የተማሪዎች ማደሪያ ሕንፃም ቁጥጥር የሚደረገው በትምህርት ክፍሎች አማካኝነት መሆኑ ታውቋል፡፡

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ አንዳርጌ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርሲቲው ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የማደሪያ ሕንፃዎችን ለአገልግሎት ዝግጁ የሚሆኑበት ደረጃ ላይ የማድረስ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፤ በዚህም ባለፈው ዓመት ከነበረው ችግር የተነሳ የተጎዱ ማደሪያ ክፍሎችን የመጠገን ሥራው በመጠናቅ ላይ ይገኛል።

ከዚህም ባለፈ ምድረ ግቢውን ጽዱ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ጤፍና አትክልትን ጨምሮ ለተማሪዎች የምግብ ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶችን በማሟላት ላይም ነው ብለዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው መሠረታዊ ችግር ሊሆን የሚችለው የውሃ አቅርቦት መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ የውሃ እጥረትን ሊፈታ በሚችል መልኩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን፤ መምህራንን ከማሟላት አኳያም ቅጥር እየተካሄደ መሆኑንና በሚሰጡት የትምህርት ዓይነቶች ድልድል እየተካሄደ መሆኑን፤ የማስተማሪያ ግብዓቶችም በመሟላት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
•የአፋር ህዝብ ፓርቲ
•የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ
•የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ/ኦዲፒ/
•የጋምቤላ ህዝቦች ፍትህ ለሰላምና ዴሞክራሲ ንቅናቄ

https://telegra.ph/TIKVAH-09-27-2

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና እና የስም ቅየራ የተሰጣቸው ፓርቲዎችን ለህዝብ ማሳወቅ አለበት በሚለው የህግ ድንጋጌ መሰረት ከላይ የተጠቀሱት ፓርቲዎች የስም ቅየራ እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል።

ምንጭ፦ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ሕንፃ ቁጥጥር የሚደረገው በትምህርት ክፍሎች አማካኝነት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ #DEBRE_BERHAN_UNIVERSITY

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያዳምጡ⬆️

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በደመራ ስነ ስርዓት ወቅት በህገ መንግስቱ ከተፈቀደው ሰንደቅ ዓላማ ውጪ የተለያዩ አርማዎችን ይዞ መገኘት አይችልም ያለበትን ምክንያት ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አስረድቷል፤ ካላይ ያለውን ፋይል ከፍታችሁ ሙሉውን አድምጡ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ፦

"...በዓሉን ወደፖለቲካ ለመቀየር፤ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ የተዘጋጀ ኃይል አለ። ይሄንን ወደሌላ እንዳይሄድ ነው። ፖሊስ የህዝቡን ደህንነት ከመጠበቅ አንፃር ነው እየሰራ ያለው እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም የለውም። ፌደራል ፖሊስ ፓርቲም አይደግፍም፣ብሄርም አይደግም ሃይማኖትም አይደግፍም...የለውም! እኛ ውዥንብር እንዳይፈጠር ችግር እንዳይፈጠር ነው። አንድ ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ ይዞ ይሄ ሀገር አቀፍ በዓል ነው። በአለም አቀፍ ደረጃም ተቀባይነት ያለው በዓል ነው። በጥሩ ሁኔታ በድምቀት የለምንም ልዩነት በሰላም እንዲጠናቀቅ ነው፤ ረብሽ ሳይነሳ እንዲጠናቀቅ ነው።...እኛ ጥንቃቄ ከማድረግ አንፃር ነው። እንዴት እኛ ሃይማኖት ውስጥ ገብተን የሃይማኖት ጉዳይ እንከለክላለን? ፖሊስ ያውቃል የሃማኖት ነገር የቱ ነው፤ የሃይማኖት ያልሆነው የቱ ነው የሚለውን በደንብ ነው የሚያውቀው። ፖለቲካ እና ሃይማኖት መቀላቀል የለበትም። ለፖለቲካ አርማ የሚጠቀሙትን እዛው ፖለቲካ ቦታ ይውሰዱ ፤ ረብሽ ማስነሺያ ስለሆነ ነው። ማቀጣጠያ ነው። የቤተክርስቲያንን አርማ አልነካንም እኛ ቤተክርስቲያን የራሷ አርማ አላት እዛ ውስጥ አልገባንም። "

@tsegabwolde @tikvahethioia
ከጅማ⬆️

"ዛሬ በጅማ በሰማ አካባቢ ልጆች አስተባባሪነት የደም ልገሳ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው፤ በጣም ብዙ ሰው ደም ለግሷል። በተለይ የአካባቢው ወጣት፣ ሴት ወንድ ሳይል ብዙ ሰው ተሳትፏል። ለመላው የእርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የመስቀል ደመራ በዓል እንዲሆንም እንመኛለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DebreTabor

የደብረ ታቦር ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የመስቀል በዓል የሚከበርበትን የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ አደባባይን ዛሬ አጽድተዋል። ‹‹የእስልምና ሃይማኖት ከክርስትና ሃይማኖት ጋር አብሮ የኖረ እና የተዛመደ በመሆኑ አብሮነታችንን ለመግለፅ የጽዳት ሥራውን አከናውነናል›› ብለዋል። ‹‹አንዳንድ አካላት የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖትን በማጋጨት የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማስተላለፍ ቢጥሩም አብሮነታችንን ከጥንት ጀምሮ የቆየ በመሆኑ ሊነጣጥሉን አይችሉም›› የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል።

ባለፈው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በዓል በሚያከብሩበት ወቅት የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች መስጅድ እና የመስገጃ ቦታዎችን ማጽዳታቸው የሚታወስ ነው።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ምንም የተደበቀ ዓላማ የለውም!" የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
.
.
ትላንት መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም በሚዲያ አማካኝነት የተሰራጨው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ አርማና ሎጎ መያዝ አትችልም አላልንም እኛ ያልነው የኢትዮጵያ ህዝብ ያልተግባበት የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አርማ ይዞ መምጣት አይቻልም ነው ያልነው። ምክንያቱም በዓሉ የሀይማኖት መሆኑ ቀርቶ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተጠልፎ የፖለቲካ አጀንዳ መጠቀሚያ ሆኖ ወደ ግጭት እንዳያመራ ነው። ይህንን ታላቅ በዓል በርካታ የዓለም ሚዲያዎች የሚዘግቡት ስለሆነ መንገዱን ስቶ ገጽታችንን ማበላሸት የለበትም ፣ ወደ ግጭት የሚያመሩ ነገሮች ሁሉ ይወገዱ፤ ህዝበ ክርስቲያን ይህንን በዓል በድምቀት አክብሮ አምላኩን አመስግኖ በደስታ ያለምንም የፀጥታ ችግር ወደ ቤቱ እንዲመለስ ነው። ከዚህ ውጭ ምንም የተደበቀ ዓላማ የለውም።

ፖሊስ ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም!

ETHIOPIAN FEDERAL POLICE COMMISSION

@tsegabwolde @tikvahethiopia