TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ጦማሪያን ፎረም⬆️

#በዩኔስኮ አዘጋጅነት በስካይ ላይት ሆቴል እየተዘጋጀ በሚገኘው በዚህ መድረክ ላይ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ እንዴት ሀሰተኛ መረጃዎችን ልናጣራ እንችላለን በሚል በ Cayley Clifford(ከአፍሪካ ቼክ) አቅራቢነት መነሻ ኃሳብ ተነስቶ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በከሰዓቱ መርኃግብር ደግሞ በኢትዮጵያ የጦማርያን አሶሴሽን በማቋቋም ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትያጵያ የጦማሪያን ማህበር ቢቋቋም ጠቀሜታው ምን ይሆን?

#በዩኔስኮ አዘጋጅነት የአንድ ቀን #የጦማሪያን ፎረም ትላንት ተካሂዷል፡፡ ፎረሙ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኡጋንዳና ከኬኒያ የመጡ እንግዶች ያላቸውን ልምድም ያካፈሉበት መድረክ ሆኖ አልፏል፡፡ በተለይ በኬኒያ ያለው የጦማሪያን ማህበር በኢትዮጵያ ማህበሩ ቢቋቋም ከተጠያቂነት፣ መብትን ከማስከበር፣ ሀገራዊ ጉዳዮችን እንደ ዓላማ ይዞ ከመንቀሳቀስና በኬኒያ ካጋጠማቸው የመንግስት ጫና ጋር በማጣቀስ ለተሳታፊዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25-2
#ጊፋታ

የወላይታን የዘመን መለዋጫ የጊፋታ በዓል #በዩኔስኮ የማስመዝገብ ጥረት መጀመሩ ተገልጿል፡፡ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንደገለጹት፤ የጊፋታን በዓል በዩኔስኮ የማስመዝገብ እንቅስቃሴ በመካሄድ ላይ ነው ብለዋል፡፡ ከመስከረም 14 እስከ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረው የወላይታ ዘመን መለዋጫ ትርጓሜ ታላቅና የመጀመሪያ ማለት እንደመሆኑ በበዓሉ ያለውን እውነታ በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚደረውን ጥረት ከፍ እንደሚያደርገው አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia