TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሲራጅ አብደላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት!

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአፋር ክልል ፖሊስ አባል ለሆነው ሲራጅ አብደላ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከቱ። ዛሬ መስከርም 12 ቀን 2012 ከሰዓት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ሀገሬና ሕዝቤ ይበልጥብኛል በማለት የሕግ የበላይነትን በማስከበሩ ያላቸውን አድናቆት ገልፀውለታል። ወጣት እንደመሆኑ በጣም ብዙ ለሀገሩ መሥራት እንደሚችልና በመልካምነቱ እንዲቀጥል ማበረታታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እጅግ በጣም አሳዛኝ... ከደንበጫን ወደ ባህርዳር በሚወስደው መንገድ ሀይሩፍ እና ሀይሱዙ መኪና ተጋጭተው ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። በስፍራው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በአደጋው የሰው ህይወት ማለፉን ነግረውናል። ጉዳቱን አስከፊ ያደረገው ደግሞ አምቡላንስ በአካባቢው ቶሎ መድረስ ባለመቻሉ ነው ብለዋል ቤተሰቦቻችን። ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል! @tsegabwolde @tikvahethiopia
በዚህ አሳዛኝ አደጋ የሟቾች ቁጥር ስንት እንደሆነ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን እስካሁን 16 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በቦታው የነበሩት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ እንደነበረ ገልፀው ለሟች ቤተሰቦች መፅናናቱን ተመፅተዋል፤ የተጎዱትንም ፈጣሪ ይማራቸው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
⬆️ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላለፈ መልዕክት!
@tsehabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አንባቸው መኮንን መታሰቢያ⬆️

በቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶክተር) መታሰቢያነት የተሰየመዉ የጎብጎብ 2ኛ ደረጃ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡

በቀድሞው አማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) የትውልድ አካባቢ ለመታሰቢነት በስማቸዉ የተሰየመዉ የጎብጎብ ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤት ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የዶክተር አምባቸዉ መኮንን ቤተሰቦች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

ትምሀርት ቤቱ በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ጎብጎብ ከተማ ነው ትምህርት ቤቱ በዶክተር አባቸዉ መኮንን ስም ለመታሰቢያነት የተሰየመው በአካባቢዉ ኅብረተሰብና የላይ ጋይት ወረዳ ጥረት መሆኑም ታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ በተያዘው የትምህርት ዘመን ለማስተማር ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል የተዛወሩ 500 ተማሪዎችን መቀበሉም ታውቋል፡፡ የመማሪያ፣ የአይ ሲ፣ የቤተ ሙከራና የቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ሕንጻዎችን አካትቶ የተገነባ ነው፡፡

ምንጭ፡- የላይ ጋይንት ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬ እንዴት ዋለች?

"አሁንም እጅግ በጣም ስጋት አለ፤ ወጥተን መግባት አልቻልንም፤ ድሬዳዋ መኖር አቅቶናል" የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ጥዋት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር። ከሰዓት ግን ሁኔታዎች የተረጋጉ መስለው አልፈዋል። በከተማይቱ ብዙ ቦታ እንቅስቃሴ አልታየም። በአንዳንድ አከባቢዎች የንግድ ተቋማት ተዘግተው ነው የዋሉት። የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ተቀዛቅዞ ውሏል። አሁንም ውጥረቱ ሙሉ በሙሉ አልረገበም። ነዋሪውም ስጋት ላይ ነው።

ትራንስፖርትን በሚመለከት የተወሱኑ አካባቢዎች ነው የሚንቀሳቀሰው መንገድ የተዘጋባቸው ሰፈኖች ሙሉ በሙሉ ትራንስፖርት አልነበረም ለምሳሌ ኮኔል አካባቢ ታክሲ እስከ ድልድዩ ድረስ ነበር ሲሄድ የነበረው። ቀፊራ አካባቢም ትራንስፖርት አልነበረም፤ አዲስ ከተማ፣ ኮኔል፣ ደቻቱ፣ ቀፊራ አካባቢ መንገዶች በድንጋይ ተዘግተው ነበር የዋሉት።

በከተማው ከተፋጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ ብዙ ንብረት ወድሟል፤ ሰዎች ተጎድተዋል። የተደራጁ አካላት የሰዎች መኖሪያ ቤት አውድመዋል። አካባቢ እየተለየ ነው ረብሻ የሚነሳው፣ ምክንያቱም አይታወቅም፤ ነገር ግን ከጊዜ በኃላ ወደ ሃይማኖት፣ ወደ ብሄር ፀብ ይቀየራል። የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ችግሮች ብዙ በሚታዩባቸው አካባቢዎች በቡድን ሆነው ሰላም ለማስጠበቅ እየተንቀሳቀሱ ነበር።

አሁንም ድሬዳዋ ከስጋት ቀጠና ተላቃ እንደቀድሞ መጠሪያዋ የፍቅር ከተማ እንድትባል ሁሉም አካል ሊረባረብ ይገባል፤ በዚህ ከቀጠለ አስከፊ ችግሮች መድረሳቸው አይቀርም አሁንም የታዩት ምልክቶች የዚሁ ማሳያ ናቸው።

#TIKVAH_ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት⬆️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሄሰን የሰላም ሽልማት⬆️

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተበረከተው የሄሰን የሰላም ሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ተከናወነ። በሄሰን ፌደራዊ ግዛት ዋና ከተማ ቪስባደን በሚገኘው የፌደራል ግዛቱ ምክር ቤት በተከናወነው የሽልማት አስጣጥ ሥነ ሥርዓት የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ሽልማቱን ተቀብለዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሄሰን ፌደራዊ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር የሄሰን ፓርላማ አባላት የጀርመን መንግሥት ባለሥልጣናት የተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

Via #FBC
PHOTO: DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች እስከመቶ በመቶ የደምወዝ ጭማሪ እንዲፈጸም ተወስኗል!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሐምሌ 2011 ባካሔደው ስብሰባ የባንኩ ሠራተኞች ለሁለት ዓመት ሲያቀርቡ የነበረውን የደምወዝ ጥያቄ በማጽደቅ ከአዲሱ በጀት ዓመት ጀምሮ የሚታሰብ እስከመቶ በመቶ የደምወዝ ጭማሪ እንዲፈጸም ወስኗል።

በቦርዱ ውሳኔ መሠረትም የባንኩ የሰው ኃይል ክፍል ለሠራተኞቹ በላከው የውስጥ ማስታወሻ የደምወዝ ጭማሪውን ማፅደቁን የገለፀ ሲሆን፤ የጭማሪውን መጠንም በያዝነው ሳምንት በሚተላለፍ የውስጥ ማስታወሻ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ባንኩ ከ37 ሺሕ በላይ ከሚሆኑ ሠራተኞቹ ሲቀርብበት የነበረውን ይህንን የደምወዝ ጥያቄ ለመፍታት ባለፈው ዓመት የተለያዩ የጥቅማ ጥቅም ማሻሻያዎችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ የባንኩ ሠራተኞች ካለው የሥራ ጫና እና ከባንኩ አቅም ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ እንደሆነ ሲያማርሩ ቆይተዋል። ባሳለፍነው ዓመት አጋማሽ ላይ በከተማ ለሚገኙ ሠራተኞቹ 15 በመቶ የኑሮ ውድነት ጭማሪ ያደረገ ሲሆን ከከተማ ውጪ ለሚገኙት ደግሞ የበረሃ አበል ላይ ተመሳሳይ ጭማሪ ማድረጉ ይታወሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-23-7

Via አዲስ ማለዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሻሸመኔ⬆️

"እንዴት አመሻቹ? ዛሬ በሻሸመኔ ከተማ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ከምሽቱ 12 ሰአት አካባቢ ትልቅ ዋርካ ወድቆ በሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። 2 ባጃጅ እና 1 ሌላ መኪና ላይ ወድቆ ጉዳት አድርሷል። እስካሁን የአንዱ ባጃጅ ሹፌር ነው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ከአንድ ሰአት በኃላ ነው የወጣው አዲስ ነገር ካለ አሳውቃለሁ።" Seyaw/ከሻሸመኔ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ የወደቀው ዋርካ እስካሁን እንዳልተነሳ በቦታው ላይ የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ገልፀዋል። በመሆኑም በዚሁ መስመር እያሽከረከራችሁ የምትገኙ ጥንቃቄ እንድታደርጉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

አዲስ ነገር ካለ መልሰን እናሳውቃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የባጃጅ አሽከርካሪ ወደ ሀዋሳ ሪፈር ተደርጎለት እየሄደ ይገኛል።" Seyaw/TIKVAH-ETH/

አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ የወደቀው ዋርካ አልተነሳም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ የጥንቃቄ መልዕክት!

የወደቀውን ዋርካ ለማንሳት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ቢገኝም እስካሁን ማንሳት አልተቻለም፤ በመሆኑም ወደ ሀዋሳ መስመር እያሽከረከራችሁ የምትገኙ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። አደጋው በሰው ላይ እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

#ሻሸመኔ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኒውዮርክ

የተመድ ዐመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በኒውዮርክ ጀምሯል፡፡ መሪዎች ዛሬ ስለ አየር ንብረት ለውጥ ይመክራሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለተኛ ጊዜ በጉባዔው አልተገኙም፡፡ ለጉባዔው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴንና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸውን ነው የወከሉት፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢትዮጵያ መንግስት #ግድያውን አጣርቶ ሊያሳውቀን ይገባል፤ለህዝብ ይፋ ያድርግ" --ኮነሬል ፅጌ አለማየሁ
.
.
የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሐይሎች ኢታማጆር ሹም ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች በጀነራሉ ግድያ ዙርያ የፍትህ ጉዳይ የዘገየ ሆንዋል ሲሉ ቅሬታቸው አሰሙ፡፡ የጀነራሉ ሚስት ኮነሬል ፅጌ አለማየሁ "የኢትዮጵያ መንግስት ግድያው አጣርቶ ሊያሳውቀን ይገባል፣ ለህዝብ ይፋ ያድርግ" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር #እንደሻው_ጣሰው በበኩላቸው ምርመራው ሂደት ላይ መሆኑ ለጀርመን ራድዮ ጣቢያ/DW/ተናግረዋል፡፡ የጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ሰማንያኛ ቀን ዝክር ትላንት ሲካሄድ በተቀበሩበት ቦታ ለጀነራል ሰዓረ ሐወልት ቆሞላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጀማሪ የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጌታቸው ረዳም እንዲሁ የሰኔ 15ቱ ገድያ የምርመራ ሂደት ለህዝብ መገለፅ አለበት ብለዋል፡፡ 

Via DW/የጀርመን ራድዮ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ...በአማራ ክልል ሰኔ 15 2011 ዓ/ም ተሞክሮ ከሽፏል የተባለው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የምርመራ ውጤት "በቅርቡ ይፋ ይደረጋል" ከተባለ ወራት ተቆጥረዋል። ይህንን ብሎ የነበረው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው፤ ኮሚሽኑ በወቅቱ በነበረው የክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር ፤ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ስለምርመራ ውጤቱ ከምክርቤቱ አባላት ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበር ታስታውሳላችሁ። ከላይ ያለው ዜናም በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ይዞት የወጣው ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ለራሱ ያደረገው ነገር አልነበረም ሌላው ቀርቶ ቤት እንኳ የገዛው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነው!" ቤተሰቦቹ

ከካናዳ መጥቶ የሞተው የ 10 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ እድለኛው ሚካኤል ገብሩ ቀብር ተፈጸመ፡፡

• "ስለሚካኤል አሟሟት በቂ መረጃ አላገኘንም" ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ

ቤተሰቡ ነገሩ አስደንጋጭ ዱብእዳ እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡ የ 41 አመቱ ሚካኤል ገብሩ የዛሬ ሁለት አመት ነበር በሚኖርበት ካናዳ ቶሮንቶ የ 10.7 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ እድለኛ የሆነው፡፡ የካናዳ ዜግነት የነበረው ሚካኤል ህይወቱ በአንድ እድል ተለውጦ መልቲ ሚሊየነር ቢሆንም በማግኘቱ ጠባዩ ያልተቀየረ ሌሎችን ለመርዳት ደግ የነበረ ሰው ነበር ይላሉ ወዳጅ ዘመዶቹና የሚያውቁት ሁሉ፡፡

ለራሱ ያደረገው ነገር አልነበረም ሌላው ቀርቶ ቤት እንኳ የገዛው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነው ሲሉ የሚናገሩት ቤተሰቦቹ ላለፉት ሁለት አመታት ለሌሎች እንጂ ለራሱ አንድ ነገር ሳያደርግ ኖሮ የማይኖርበትን ቤት ገዝቶ ነው ይህን አለም የተሰናበተው ሲሉ በሀዘን ስሜት ለሲቢሲ ዜና አውታር ስለ ሚካኤል ተናግረዋል፡፡

ሎተሪ ባገኝ የተቸገሩ ሰዎችን ነው የምረዳበት ሲል የሚመኝ ደግ ሰው ነበር የሚሉት እና በቅርበት የሚያቃውቁት ሎተሪ ከወጣለት በኋላ እንኳን በአካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለቤተክርስቲያናት ብዙ ልገሳ አድርጓልም ይላሉ፡፡

ሲመኝ የኖረው ሎተሪ ወጥቶለት ቱጃር ከሆነ በኋላ ማንነቱንና ባህሪውን ሳይቀይር በወዳጅ ዘመዶቹና በሚያውቃቸው እንደተወደደ መኖሩን ብዙዎች መስክረውለታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-09-23-8
TIKVAH-ETHIOPIA
በዚህ አሳዛኝ አደጋ የሟቾች ቁጥር ስንት እንደሆነ ፖሊስ እያጣራ ሲሆን እስካሁን 16 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በቦታው የነበሩት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ እንደነበረ ገልፀው ለሟች ቤተሰቦች መፅናናቱን ተመፅተዋል፤ የተጎዱትንም ፈጣሪ ይማራቸው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር 23 ደርሷል!

በደምበጫ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 23 ደረሰ። በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 17 ወንዶችና 6 ሴቶች መሞታቸው ተሰምቷል። አንድ የጭነት ማመላለሻ አይሱዙ ሁለት መለስተኛ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አቡቶብሶችንና አንድ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ ገጭቶ ነው አደጋው የደረሰው። አደጋው የደረሰው ደምበጫ ዙሪ ወረዳ ከየጨረቃ ከተማ ወጣ ብሎ ነው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የአባይ ጉዳይ ለግብፅ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ነው”

"ግድቡ ወደግብፅ የሚወርደውን የውሃ ፍሰት ይቀንሰዋል ይህ ደግሞ በ100 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ ተፅኖ ያሳድራል"

“ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንም ግብፅ 95% በረሃማ መሆኗን መገንዘብ አለባቸው”

"...ያለን የናይል ውሃ ብቻ ነው”

የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #ሳሜህ_ሽኩሪ በተመድ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመካፈል በአሜሪካ ኒውዮርክ ይገኛሉ። ሚኒስትሩ ከአል ሞኒተር ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እና ስለ አባይ ወንዝ የተወሰኑ ነጥቦችን አንስተዋል ይህንን https://telegra.ph/TIKVAH-09-23 በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia