TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወጣቷን #በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ #ሞት ተፈረደበት‼️
.
.
አንዲት ወጣት ላይ አሰቃቂ ግድያ ፈፅሟል ያለውን ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ፍርድ ቤቱ ቅጣቱ የወሰነው በሐረማያ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ በሆነው #ጫላ አህመድ ሙመድ የተባለው ግለሰብ ላይ ነው።

የፍርድ ቤቱ ዳኛ አቶ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በግለሰቡ ላይ ቅጣቱን የወሰነው በቤት ሠራተኝነት ሕይወቷን ትመራ የነበረች ወጣትን በግፍ መግደሉ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት ነው።

ሟች በአወዳይ ከተማ ከባለቤቷ ጋር ተጋጭታ በሐረር ከተማ በቤት ሠራተኛነት ስትሰራም ነበር።

“ግለሰቡ ወጣቷን ለትዳር እንደሚፈልጋት በመግለፅ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት በመውሰድ ከአቅም በላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከፈፀመባት በኋላ ጆሮዋ አካባቢ እንደመታትና አንቆ እንደገደላት ታውቋል” ብለዋል።

“ወጣቷ ላይ ግድያ ከፈፀመ በኋላ ቤቱ ቆልፎባት ጠፍቷል” ያሉት ዳኛው፣የቤቱ ባለቤቶች ግለሰቡ በመጥፋቱ መጋቢት 24 ቀን 2010 ቤቱን ለሌላ ግለሰብ ለማከራየት ፈልገው በሩን ሲከፍቱ አስከሬኑን እንዳገኙት አስረድተዋል።

“የተዘጋውን በር ሲከፍቱ ያልጠበቁት መጥፎ ጠረን ያጋጠማቸው አከራዮች ዘልቀው ሲገቡ በቤቱ ወለል ላይ የፈረሰ የወጣቷን አስከሬን አግኝተነዋል” ሲሉም አብራርተዋል።

የሐረማያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ወንጀሉ ወደ ተፈፀመበት ቤት በማምራት አስከሬኑን ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሆስፒታል ተልኮ ምርመራ ከተደረገለት በኋላ መቀበሩን ተናግረዋል።

“ግለሰቡ በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የወሲብ ጥቃት ይፈጽሟል በሚል ጥርጣሬ በመኖሪያ ቤቱ በተደረገ ፍተሻ የሟች አልባሳት፣ የተለያዩ ሴቶች ፎቶግራፎች፣ ማሰቃያ ሰንሰለትና ሌሎች ወንጀል መፈፀሚያ ቁሶች ተገኝተዋል” ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ የቀረቡለትን የሕክምናና የሰው ማስረጃዎች በመመልከት ቅጣቱን መበየኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዱዓ እና ምህላ እየተደርገ ነው!

የሰዎች ህይዎት ላይ እየደረሰ ያለው በደል #እንዲቆም ምህላ እና ዱዓ እየተደረገ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች አስታወቁ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው #ግጭት ምክንያት በሰዎች ህይዎት እየደረሰ ያለው ጉዳት #ምህረት እንዲያገኝ ነው #ምህላ እና #ዱዓ እየተደረገ የሚገኘው። በሁለቱ ዞኖች እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች #ሞት#መፈናቀል እና #መሰደድ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶች አውግዘዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥንቃቄ አድርጉ‼️ #ከኢትዮጵያ ወደ #ቻይና የምትሄዱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዎች ይህን እቃ እዛ ላለ ሰው አድርስልኝ/አድርሺልኝ ሲሏችሁ በደንብ የሚላከውን ነገር ፈትሹ። ቻይና ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለመረዳት እንደቻልነው አንዳንዶች በሚላከው እቃ ውስጥ አደንዛዥ እፆችን በመጨመር እንደሚልኩ ጠቁመዋል። በተለይ ምግብ ነክ ነገሮች ውስጥ የአደንዛዥ እፆችን በመክተት ይልካሉ።…
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️

በህገ ወጥ ደላሎች #ነፃ የትምህርት አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ #ነብያት_ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት በሚገኙ ህገ ወጥ ደላሎች ነጻ የትምህርት እድል አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶቹ አግኝታችሁታል የተባለው ነፃ የትምህርት እድል #ሀሰተኛ በመሆኑ ቻይና ሲደርሱ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ባለፈም በቻይና አደገኛ እፅ #በማዘዋወር እና #ጫትን ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና በማስገባት በህገ ወጥ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ቃል አቀባዩ አብራርተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በቻይና በዚህ አይነት ወንጀል መሳተፍ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ #ሞት ቅጣት በሚደረስ ፍርድ የሚያስቀጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 47 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በፍርድ ቤት #ጥፋተኛ ተብለው የእርምት ጊዜያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን የቀሪዎቹ ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዜጎች ከተመሳሳይ ችግር ለመውጣት የትምህርት እድል አግኝታችኋል ሲባሉ ከተቋማቱ በቂ መረጃ መሰብሰብ እንደሚገባቸውም ቃል አቀባዩ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ወደ ቻይና ለተለያዩ ጉዳዮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የታሸጉ ነገሮችን ወደ ቻይና አድርሱልን ተብለው ሲጠየቁ ስለእቃዎቹ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

እነዚህ ወንጀሎች የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት እንዳያበላሹም መንግስታቱ እርስ በርስ የተሳሰሩ ደላሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት የሄዱ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ቃለ አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በተያዘው ሳምንት 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና 1 ሺህ 15 ኢትዮጵያውያን ከፑንትላንድ መመለሳቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ 500 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እንዲሁም ከፑንትላንድ 517 ዜጎች እንደሚመለሱ አውስተዋል።

እነዚህን ዜጎች ከሀገራት ለማስመለስ ከአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ዓመት ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ #ገድለዋል በተባሉ 3 ወታደሮች ላይ #ሞት ሲፈርድ በአንድ ወታደር ላይ ደግሞ የ10 ዓመት እሥራት በየነ። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ባለፈው ዓመት የተፈጸመው የዚህ ግድያ ዓላማ #ዘረፋ ነበር። ትናንት ያስቻለው ፍርድቤቱ ከወታደሮቹ ጋር ተባብረዋል ከተባሉ ሁለት ሲብሎች አንዱ እድሜ ይፍታህ ሌላኛው ደግሞ የ8 ዓመት እሥራት ተፈርዶበታል። አራቱም ወታደሮች ማዕረጋቸው ተገፎ ከጦር ኃይሉም መሰናበታቸው ተዘግቧል።

Via ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ እና ኢራን ወዴት እያመሩ ነው

ኢራን ለሲአይኤ እየሠሩ ነበር ያለቻቸውን 17 ሰላዮች በቁጥጥር ሥር ማዋሏን ይፋ አደረገች። ከነዚህ ገሚሱ #ሞት ተፈርዶባቸዋል ተብሏል። የኢራን የደህንነት ሚንስትር እንዳለው፤ ተጠርጣሪዎቹ ስለ ኒውክሌር፣ መከላከያ እና ሌሎችም ዘርፎች መረጃ እየሰበሰቡ ነበር። የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን ክስ "ሀሰት ነው" ሲሉ አጣጥለዋል። በኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ሳቢያ ሁለቱ አገራት እንደተፋጠጡ ነው። ትራምፕ ከዓለም አቀፉ የኒውክሌር ስምምነት ባለፈው ዓመት ወጥተው ኢራን ላይ የንግድ ማእቀብ መጣላቸው ይታወሳል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia