TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ📸የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሁለተኛ ዓመት⬆️

ፎቶ©TIKVAH-ETH ቤተሰቦች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ ምሽት በTIKVAH-ETH ስለነዚህ ጉዳዮች ቤተሰቦቻችን የሚሉት ነገር አላቸው!

√የ2010 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች የውጭ የትምህርት እድል ሳያገኙ አሁንም እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፣ በርከት ያሉትም የዚህ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ ስደረሰባቸው መንገላታት ቅሬታ አሰምተዋል።

√ከተለያዩ የሬድዮ ጣቢያዎች ነው የምንደውለው በማለት በርካቶች ካርድ እየተጠየቁ እንደሆነ ነግረውናል። አንዳዶቹ ልክዋል!! ደዋዮቹ ደውለው ምን ይላሉ ቀድተናቸዋል!

√የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ሰራተኞች ስራ አቁመው ውለዋል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወላይታ ሶዶ ከተማ 35 ኩንታል ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች ተያዙ። በድሬዳዋ አስተዳደርም ከ146 ኪሎ ግራም በላይ ካነቢስ አደንዛዥ እጽ እንዲቃጠል ተደርጓል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ህያውሁን ሞጋ እንዳሉት 35 ኩንታል ካናቢሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ባለፈው ነሀሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም ነው።

ዕጹን የሰሌዳ ቁጥሩ 3-03866 አ.አ በሆነ ኤፍ.ኤስ.አር አይሱዙ ተሽከርካሪ ሲያዘዋውሩ የነበሩት አሽከርካሪና ረዳቱ ከነ መኪናው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል፡፡

ምክትል ኢንስፔክተር ህያውሁን እንዳሉት ካናቢሱን ከኦሮሚያ ክልል ሻሸማኔ ከተማ በማምጣት እስከ አርባ ምንጭና ሞያሌ ከተማ ድረስ የማድረስ ዕቅድ ነበር።

https://telegra.ph/ETH-09-06-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
29 ሺህ ሰዎች በቺክቭ ተይዘዋል!

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ የጤና ቢሮ ሀላፊዎች ፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በበሽታው ተይዘው በጤና ተቋማት ህክምና እየተደረገላቸው ያሉትን ወገኖች እንድሁም በህብረተሰቡ ውስጥ በመኖሪያ ቤትና አከባቢው በሽታውን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ ተመልክተዋል:: የጤና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸው ውሃ የሚያቁሩ ጉድጓዶችን የመድፈን፣ ማፋሰስና ኬሚካል ርጭት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። በከተማው እስካሁን ሃያ ዘጠኝ ሺህ( 29,000) ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን የሞተ ያለመኖሩን ማረጋገጥ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ማዕከላዊ እስር ቤት⬆️

"ማዕከላዊ እስር ቤት ያገኘሁት ነው። የሚታየው ልጅ እዛው ተጎጂ የነበረ ነው።" #ABEBA/TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️በዛሬው ዕለት #ማዕከላዊ_እስር_ቤትን የጎበኙ የTIKVAH-ETHIOPIA የቤተሰብ አባላት ከላይ ያሉትን ፎቶዎች #አጋርተውናል!

እርሶስ ማዕከላዊን ጎብኝተው ነበር? ፎቶዎችን ያጋሩ!

ፎቶ©ABEBA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE በትምህርት ሚኒስቴር ስም እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው!
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. Walta TV -- ይህ የቴሌግራም ቻናል የዋልታ ቴሌቪዥን አይደለም። ዋልታ ሚዲያ እስካሁን በይፋ ያሳወቀው የቴሌግራም ቻናል የለም።

2. ትምህርት ሚኒስቴር --- የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርን ስም የሚጠቀመው ቻናል ሀሰተኛ ነው። ትምህርት ሚኒስቴር ቴሌግራም ቻናል የለውም።

3. NEAEA/የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ/ --- ኤጀንሲው ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል የለውም።

ፌስቡክ፦

1. አብን/የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ/--24,00 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አይደለም። በዚህ ገፅ የመሰራጩ መረጃዎችም የአብን አይደሉም። ትክክለኛው የፌስቡክ ገፅ 153,422 like ያለው ነው።

2. OBN አማርኛ -- 20,236 ሺህ Like ያለው OBN አማርኛ በሚል የተከፈተው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የዋናው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 111 ሺህ Like ያለው ነው። ይህን የፌስቡክ ገፅ ተጠንቀቁት!

#Bonus

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በፌስቡክ #verify የተደረገ የፌስቡክ ገፅ አላቸው። ገፁ 97,017 Like ያለው ነው!

#TIKVAH_ETHIOPIA

በየዕለቱ 5 ሀሰተኛና በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸውን ገፆች እናቀርባለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

ዛሬ በተካሂደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ 95 በመቶ መግባባት ላይ መደረሱን ሊቀ አእላፍ ቀሲስ #በላይ_መኮንን ገለፁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያ ተልኮ መመሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ሰላም ቀሲስ #ሰለሞን_ቶልቻ በበኩላቸው፤ ውይይቱ በጥሩ መንፈስ መጠናቀቁን ገለፀው በነገው ዕለት መቋጫ እንደሚበጅለትና መግለጫ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጠዋት መወያየታቸው ይታወቃል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Tikvah-eth
Tikvah-Eth 2
ደዋዮቹ እነማን ናቸው?

በተለያየ ሰው ስልክ ላይ እየደውሉ ከፋና ብሮድካስቲንግ ነው፤ እድለኛ ስለሆኑ ካርድ ይላኩልን የሚሉ አካላት እየበዙ መጥተዋል። እነዚህ አካላት ማንነታቸው #አይታወቅም። የሚደውሉትም በሞባይል መስመር ስልክ ነው። ስራቸውን በስልክ ነው የሚሰሩት በርካቶችን እያጭበረበረበሩ የሚገኙ አካላት ናቸው። በሚድሮክ ኢትዮጵያ ስም፣ በኢትዮ ቴሌኮም ስም፣ የማጭበርበር ስራ እየተሰራ ነው። ስልክ ከተደወለላቸው አካላት መካከል የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል። ለመሆኑ ፋና ብሮድካስቲንግ ይህን ጉዳይ ያውቀዋል?? ሚድሮክ ኢትዮጵያ ያውቀዋል?? ኢትዮ ቴሌኮምስ?? ምን እየተሰራ ነው ያለው??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይሄ ስልክ +251 97 397 0261 የሚድሮክ ነው? የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው?? የኢትዮ ቴሌኮም ነው?? በዚህ ቁጥር እና በሌሎችም ነው እየደወሉ እስከ 800 ብር ድረስ ካርድ ለማስሞላት የሚሞክሩት። የሚመለከተው አካል ይህን ድርጊት በአስቸኳይ ያጣራ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ በዚህ ቁጥር +251 97 397 0261 የተደወለለት የቻናላችን ቤተሰብ ይህን ብሏል፦

"እነዚህ ሰዎች ብዙ ሰው እያታለሉ ነው። መጀመሪያ ላይ እኔም አምኛቸው ነበር። በባህሪየ ተጠራጣሪ ነኝ ግን ለማሳመን የተጠቀሙበት መንገድ ከባድ ነው እንደሰማኸው በጣም ነው የሚያጣድፍህ ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚሰጡህ። የገንዘብ ሽልማቱን በተመለከተ ለኔ እንኳን የጠቀሰልኝ ብር 42 ሺ ብር ነው። ይሄን ሰማ ነው መጠራጠር የጀመርኩት። እንደሚታወቀው ለበአል ሽልማት በአብዛኛው ሲዘጋጅ የበግ መግዣ ወይም ሌላ የቤት ቁሳቁስ እንጂ በዚህ ደረጃ የገንዘብ ሽልማት ሰምቼ አላውቅም። ብቻ ሁሉም ሰው ይወቀው። በተለይ ራንደምሊ ስለሚደውሉ ብዙ የገጠር አካባቢ ሰዎችን እንደሚያታልሉ መገመት ይቻላል። አመሰግናለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ አበርክተዋል።

የዛሬን ውሎ የተመለከተ ዘገባ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-06-5