የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች መካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በመመዘኛነት የማያገለግሉ ውጤቶች፦
በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦
•ባዮሎጂ፣
•ኬሚስትሪ እና ስነ-ዜጋ (Civics) ፈተናዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመቀላቀል በመመዘኛነት #አያገለግሉም።
በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦
•የታሪክ (History)፤
•ኤኮኖሚክስ እና ስነ-ዜጋ ፈተናዎች ውጤቶች #ውድቅ ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዘሪሁን ዱሬሳ (ዶ/ር) እንዳሉት ባለፈው ሰኔ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመቀጠል በእንግሊዘኛ፣ ሒሳብ እና አፕቲቲዩድ ውጤቶቻቸው ይለካሉ።
ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ፊዚክስ፣ ከማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ የጂኦግራፊ ፈተናዎች ለመመዘኛነት ተመርጠዋል።
ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ «ተማሪዎችንም ፍትኃዊ በሆነ መልክ ሊያወዳድር እና ከእነሱ ችሎታ ባሻገር ምንም መበላለጥን ሊያስከትል የማይችል ሆኖ ስላገኘንው እነዚህን ተጠቅመን ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ መመደብ እና የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት ወስነናል» ብለዋል።
ከ322 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከሰኔ 6 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የተቀመጡበት ይኸው ፈተና ችግር እንደነበረበት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚዓብሔር «ሰኔ 6 እና 7 የተፈተኑት ፈተና ትክክለኛ ይዘት አለው። ሰኔ 10 እና 12 [የተፈተኑት ፈተናዎች ውጤት] ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ሲታይ የመጨመር ባሕሪ ሲያሳይ የተወሰነ ቦታ ላይ ግን ከሚጠበቀው በላይ ጋሽቦ ሔዷል» ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ «መቁረጫ ነጥቡ የት ይሆናል የሚለውን ኤጀንሲው ለተማሪዎች እና ለወላጆች፤ ለዩኒቨርሲቲዎች ግልፅ የሚያደርግ ይሆናል» ብለዋል።
የመንግሥት ባለስልጣናቱ ውሳኔ ቀድሞም ቀውስ ውስጥ በገባው የትምህርት ዘርፍ ተጨማሪ የውዝግብ መነሾ ሆኗል። ለመመዘኛነት አያገለግሉም ተብለው ውድቅ የተደረጉት የፈተና ውጤቶች ችግሮች ምንድናቸው? በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምን አይነት ችግሮች ተፈጠሩ? #ተጠያቂውስ ማነው ለሚሉ ጥያቄዎች ባለሥልጣናቱ በግልፅ የሰጡት ማብራሪያ ባይኖርም ጉዳዩ ጠቅላይ ምኒስትሩ በሚመሩት አጣሪ ኮሚቴ ጉዳዩ ይመረመራል ተብሏል።
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች መካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በመመዘኛነት የማያገለግሉ ውጤቶች፦ በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦ •ባዮሎጂ፣ •ኬሚስትሪ እና ስነ-ዜጋ (Civics) ፈተናዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመቀላቀል በመመዘኛነት #አያገለግሉም። በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦ •የታሪክ (History)፤ •ኤኮኖሚክስ እና ስነ-ዜጋ ፈተናዎች ውጤቶች…
ግልፅ መሆን ያለባቸው ጥያቄዎች!
የ12ኛ ክፍል ፈተና!
ችግሩ እነዴትና በማን ተፈጠረ? በሌሎች የትምህርት አይነቶች በራሳቸው ሰርተው የተሻለ ውጤት ላመጡ ተማሪዎችስ ችግር አይፈጥርም ወይ? የሚሉና ሌሎችም ግልጽ መሆን ያባቸው ጥያቄዎች አሁንም ምላሽ ይሻሉ፡፡
Via #AMMA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA

#FAKE የ2012 ዓ/ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ/የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ እየተባለ የሚሠራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
#የአምቦ_ህብረት -- ደብተር ለመግዛት አቅም ለሌላቸው ቤተሰብ ልጆች የደብተር ማሠባሰብ ሥራ እየተሠራ ነው። በአምቦ የምትገኙ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በዚህ ሥራ ላይ እንድትሣተፉ ጥሪ እናቀርባለን።
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
📌በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ማስታወቂያ ተመሳሥሎ የተሠራ ነው!
"ሰላም ፀጋ የUnity University ማስታወቂያ ተመሳስሎ የተሰራጨው ማስታወቂያ #በphotoshop ተቀነባብሮ የተሰራ መሆኑን የግቢው አስተዳደር አረጋግጦልኛል" #YABU
ተመሳስሎ የተሰራበትን ማስታወቂያ👇

#Photoshop የተሰራበት ትክክለኛው ማስታወቂያ ይህ ሲሆን ለማረጋገጥ ቀኑን, ቁጥሩን እንዲሁም የተሰኩበትን መርፌዎች ቀለም ተመሳሳይነት መመልከት ይቻላል።
Via #YABU/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #YABU/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የተላለፈላችሁ መልዕክት!
ለዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፦
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ሆኖም በቴሌግራም የተሣሣተ መልዕክት የተላለፈ መሆኑን ደርሠንበታል። ስለሆነም የተሳሳተ መረጃ መሆኑን ተገንዝባችሁ ለአላስፈላጊ ቅጣትና መጉላላት እንዳትዳረጉ እያሳሰብን ዩኒቨርሲቲው ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት #ክፍያችሁን እንድታከናውና እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናስታውቃለን።
#ሼር

👆ይህን መልዕክት በTIKVAH-ETH ተመልክታችሁ አስፈላጊውን ማጣራት አድርጋችሁ ላሳወቃችሁን አካላት ከልብ እያመሰገንን የትኛውም ድርጅት ስለተቋሙ እንዲሁም ግለሠቦች በማህበራዊ ሚዲዎች የሚናፈሱ መረጃችን ለማክሰም እና ህብረተሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ በዚህ መልዕክት መላክ ይቻላል @tsegabtikvah
#update የፌደራል ፖሊስ ባለፈው አንድ አመት ሰላምን ለማስከበር ላበረከተው አስተወጽኦ የምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ የሰለም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፌደራል ፖሊስ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ በማድረግ ሂደት ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ሀሰት ነው!
በኢትዮ ቴሌኮም ስም በተከፈተ ቻናል ሀሰተኛ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ በመሆናቸው ጥንቃቄ አድርጉ። ኢትዮ ቴሌኮም ነፃ የኢንተርኔት እና የድምፅ አገልግሎት ይሰጣል ይህን ተቀላቀሉ ለሌሎችም አጋሩ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትዮ ቴሌኮም ስም በተከፈተ ቻናል ሀሰተኛ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ በመሆናቸው ጥንቃቄ አድርጉ። ኢትዮ ቴሌኮም ነፃ የኢንተርኔት እና የድምፅ አገልግሎት ይሰጣል ይህን ተቀላቀሉ ለሌሎችም አጋሩ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ከተለያየ የዓለም ክፍል የተወጣጡ እና በተባበሩት መንግሥታት መሪነት አዲስ አበባ ላይ ውይይት እያደረጉ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ የአፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence) ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።
Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ሁለት ሠዎች ተገደሉ!
በጋምቤላ ክልል በዛሬው ዕለት ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የአይን እማኞች እና የክልሉ መንግሥት ሰራተኛ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በጋምቤላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰራተኛ የሆኑ አንድ የአይን እማኝ እንዳሉት ሰራተኞቹ የተገደሉት “ዊኜል” ከተባለ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ነው።
ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉት የተ.መ.ድ. ሰራተኛ «ዛሬ በኢታንግ መስመር ዊኜል ወደተባለ [መጠለያ] ሲሔዱ፤ ሁለት ግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ተገድለዋል። እኛው ጋ የሚሰሩ የሌላ ተቋም ሰራተኞች ማለት ነው» ሲሉ ተናግረዋል።
አክሽን አጌይንስት ኸንገር (Action Against Hunger) የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም ተቀጣሪ ናቸው የተባሉት ሁለት ሰዎች «ወደ ኢታንግ ከሚወስደው መንገድ ተገንጥለው ወደ ስደተኞች መጠለያለው ለመግባት ወደ ስድስት ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው» በታጣቂዎች መገደላቸውን የአይን እማኙ አብራርተዋል።
የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪ ባለሙያ በበኩላቸው በአካባቢው አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ንብረት የሆነ ተሽከርካሪ ጥቃት እንደተፈጸመበት አረጋግጠዋል። «የሆነ መኪና መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መኪና ተመቷል። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የሚባል አለ። ሁለት ሰው ሞቷል» ያሉት የጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪ ባልደረባ አንድ አሽከርካሪ እና የመስክ ሰራተኛ መገደላቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

#update በእስልመና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበረው የአሹራ በዓል የፊታችን ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ.ም በአልነጃሺ መስጊድ በድምቀት ይከበራል። በዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮችና ሃይማኖት መሪዎች በተገኙበት የሚከበር መሆኑ ተገልጿል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አንድ ሐገር-ቢያ ቶኮ"
በተለይ ኤቶዮጵ በተሰኘው መፅሐፉ ብዙ አንባቢዎችን ያስደመመው ደራሲና ሐኪም ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ አዲስ መፅሐፍ "አንድ ሐገር-ቢያ ቶኮ" ነገ ለአንባቢያን ይቀርባል። መፅሐፉ ነገ ጷግሜ 1 ከ11 ሰኣት ጀምሮ በሐገር ፍቅር ቲያትር ቤት የሚመረቅ ሲሆን ዋጋው 100 ብር ብቻ ነው። ከቅዳሜ ጀምሮ በሁሉም የአዲስ አበባ መፅሐፍት ቤቶችና አዟሪዎች እጅ ላይ ያገኙታል። ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ አንባብያን ከእሁድ ጀምሮ እንደሚሰራጭና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እንደሚዳረስ ደራሲው አሳውቆናል።
#TIKVAH_ETHIOPIA

#Congratulations የዲላ ዩኒቨርስቲ በክረምት ወራት ያሰለጠናቸውን 2ሽህ 286 ተማሪዎች ዛሬ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ አስመረቀ። ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 504 ሴቶች ይገኙበታል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት እንዲቋቋም አንፈቅድም ብሏል መባሉን አስተባበሉ!
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጉዳዩን አስመልክተው ለኦ ኤም ኤን በሰጡት አስተያየት፤ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት እንዲቋቋም አንፈቅድም ብሏል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መሰረተቢስ ወሬ ነው ብለዋል፡፡አቶ ሽመልስ ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን በዉይይት እንዲፈቱ ነው የተናገርኩት ነው ያሉት፡፡
"የኦሮምያ ቤተ ክህነት የሚባለው የማይታሰብ ጉዳይ ነውና እኛም አንፈቅድም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ እንደመንግስት መቸውኑ ተቀባይነት አይኖረውም በማለት ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መንግሥትን ወክለው እየተሳተፉ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል” ሲል የEOTC TV ጋዜጠኛው ዲ/ን ኃይሉ ዘግቧል የተባለውን ምክትል ፕሬዝዳንቱ የማደናገሪያ ወሬ ነውም ብለዋል፡፡
መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ገብቶ በስብሰባ ላይ ተሳተፉ ተብለው ለተጠየቁ ጥያቄም መልስ ሲሰጡ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘው እንደሆነ ገልፀው፤ ምክረሀሳብ ከማቅረብ የዘለለ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ያሉት፤ ምእመናን በቋንቋቸው እንዲያመልኩ ላመስቻል ነው በማለት ይሞግታሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የቤተክህነቱ መቋቋም በቤተክርስትያኗ ውስጥ ስር የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል ይላሉ፡፡አላማችን ሌላ ስኖዶስ ማቋቋም አይደለምም በማለት በተደጋጋም ተናግረዋል፡፡ይሁንና የቤተክህነቱን መቋቋም በአዎንታዊነት ያልተቀበሉ አካላት እርምጃውን ተቀውመዋል፡፡
Via #OMN

የኤጀንሲው 5 የስራ ሃላፊዎች ክስ ተመሰረተባቸው!
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴን ጨምሮ አምስት የሥራ ኃላፊዎች ክስ ተመሰረተባቸው።
የስራ ኃላፊዎቹ ክስ የተመሰረተባቸው ኤ ቢ ኤች ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል አማካሪ ድርጅት ደረሰብኝ ባለው የስም ማጥፋት ተግባር እንደሆነ የክስ መዝገቡ ያስረዳል።
እንዲሁም አማካሪ ድርጅቱ ከ174 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሶብኛል ሲል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትሐ ብሔር ስድስተኛ ምድብ ችሎት ክስ መስርቷል።
ከስድስት ዓመት በፊት የጅማ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ኤ ቢ ኤች ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል አማካሪ ድርጅት የመማሪያ ክፍሎች፣ የቢሮዎችና የቤተ መፃሕፍት አገልግሎት ለማቅረብ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል መፈጸሙን በክስ መዝገቡ ላይ ተጠቅሷል።
አማካሪ ድርጅቱ ”በህጋዊ ውል እየሰራሁ ባለሁበት ወቅት ኤጀንሲውና የስራ ኃላፊዎቹ ትምህርታቸውን የሚከታተሉትን ተማሪዎች መንግስት እንደማያውቃቸው፣ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋርም ያለው ግንኙነት ህገ-ወጥ ነው በማለት ለመገናኛ ብዙሃን በሚሰጡት መግለጫ የስም ማጥፋት ደስርሶብኛል” ሲል ክስ መስርቷል።
ኤጀንሲውና የስራ ኃላፊዎች በአማካሪ ድርጅቱ ላይ ያደረጉት የስም ማጥፋት ተግባር ከ174 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰበት ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል። ኤጀንሲውና የስራ ኃላፊዎቹ ለተመሰረተባቸው ክስ እስከ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የክስ መልስ እንዲያመጡ የታዘዘ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ክሱን ለመስማት ለጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via #ENA

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴን ጨምሮ አምስት የሥራ ኃላፊዎች ክስ ተመሰረተባቸው። የስራ ኃላፊዎቹ ክስ የተመሰረተባቸው ኤ ቢ ኤች ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል አማካሪ ድርጅት ደረሰብኝ ባለው የስም ማጥፋት ተግባር እንደሆነ የክስ መዝገቡ አስረድቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከቱ⬆️ዛምቢያ ውስጥ የሚገኙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል። #TIKVAH_ETHIOPIA