TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ /የትምህርት ሚኒስትር/፦

•አዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ የፌደራል የስራ ቋንቋን ማስተማር የሚለው ምክረ ሀሳብ እንጂ #አስገዳጅ ህግ አይደለም።

•ፍኖተ ካርታው ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ #የሚፈቅድ ነው።

•የፌደራል የስራ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሰጥ በፍኖተ ካርታው የተመለከተው ምክረ ሀሳብ ነው። ይሁን እንጂ ይህ #በክልሎች ስልጣን የሚወሰን እንጂ ፍኖተ ካርታው ለትግበራዉ #አያስገድድም

•አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ምክረ ሀሳብ መሰረት ቋንቋንዎችን ይበልጥ #የሚያሳድግ እና የዜጎችን ተግባቦት ይበልጥ የሚያሳልጥ ነው።
 
•የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ኢትዮጵያ የምትመራበትን የፌደራሊዝም ስርአት በምንም መንገድ አያፈርስም፤ ይህንን የማድረግ አቅመም የለውም።

•በሁሉም ትምህርት ቤቶች ቢያንስ ለ1 ዓመት የቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲሰጥ #አስገዳጅ መሆኑ ፍኖተ ካርታውን ከዚህ ቀደሙ ልዩ ያደርገዋል።
 
•አዲሱ ፍኖተ ካርታ የተሟላ የትምህርት ስርአትን ይከተላል፥ እንደ ጆኦግራፊ እና ታሪክ ያሉ የትምህርት አይነቶች በሀገር በቀል እውቀት እንዲቃኙ ያደርጋል።

•የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ሊተገበር የሚችለው የኢትዮጵያ ህዝቦች ሲያምኑበት ብቻ ነው።

#FBC #TIKVAH
@tsegabwolde @tikvahethiopia