TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወደ ሦስተኛ ደረጃ መድኃኒት የተሻገረው ኤችአይቪ ኤድስ!

በዓለም ከሚገኙ ጥቂት ወግ አጥባቂ አገሮች ተርታ ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች። የሕዝቦቿ ወግ አጥባቂነት አንዳንዴ ዘመናዊነትንየመጥላት፣ የመገዳደር ያህል የተጋነነ ሊመስል ሁሉ ይችላል፡፡ 

ብዙ አዳዲስ አስተሳሰቦችና ፈጠራዎች በአገሪቱ ተግባራዊ ከመደረጋቸውአስቀድሞ በባህልና ሃይማኖት መነጽር ማኅበረሰቡ እንዴት ሊመለከተውእንደሚችል በቅድሚያ በጥልቀት ይጤናል፡፡

ቁሳዊና ትውፊታዊ ባህሎቿ፣ ወጓ ሃይማኖታዊ መሠረት ያላቸው፣በትውልድ ቅብብሎሽ ዘመናትን የተሻገሩና በጊዜ መተካካት የበሰሉናቸው፡፡ ሐሳቡን በቀላሉ ለማስረዳት የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ፣ የቅዱስቁርዓን ሱራ ማጣቀስ የሚቀናው ሕዝቧ፣ አገሪቱ የጠኔ ምድር ብቻ ሳትሆንለፈጣሪ የተገዙ ፃድቃን መኖሪያም ሆና በዓለም ትታወቅ ዘን ረድቷታል፡፡

በሃይማኖት ላይ የፀናው የኢትዮጵያ የኋላ ታሪክ፣ የአሁን ህልውና ቅድስትአገር የሚል ቅጽል ታገኝ ዘንድም ምክንያት ሆኗል፡፡

በቀሪው ዓለም ብዙ ባህልና ልማድ ከጊዜው ጋር እንዲሄድ ተደርጎእየታደሰ፣ እየተከለሰና እየተቀነሰ የዘመናዊነት ቁንጮ የሆኑ አሁናዊባህሎች ተቀርዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-26-3
#update የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በሀገር ደረጃ በእምነት ተቋማት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ብጹአን ሊቃነጳጳሳት ተሳትፈዋል፡፡ አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእምነት ተቋማት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ተዋያይተዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ኢ/ር ታከለ ኡማ ከትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት አሰጣጥን ተመልክተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶስተኛው ዙር የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አሀድ የመጀመረያው ዓመት አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ተጀምሯል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ይገመገማሉ። መድረኩን በንግግር የከፈቱት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ታዜር ገ/እግዚያብሄር ሲሆኑ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹና በቂ የመሰረተ ልማት የተሟሉላቸው እንዲሆኑ ከተፈለገ የበላይ አመራሮችና የህብረተሰቡ የተቀናጀ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።

በቀጣይ ተግባራዊ የሚደረገው የከተሞች የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ከዚህ በፊት ከነበሩት በተጨማሪ አዳዲስ 73 ከተሞችን በመጨመር 117 ከተሞችን አካቷል። 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።ለዚህም ከዓለም ባንክና ከፈረንሳይ የልማት ድርጅት 611 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከክልሎችና ከተሞች 248 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በድምሩ 859 ሚሊዮን ነጥብ9 ሚሊዮን ዶላር የመቀናጆ በጀት ፀድቆለታል።

ይህ ፕሮግራም ከጊዜ ወደ ጊዜ አፈፃፀሙን በማሳደግ ላይ ሲሆን የፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርም በክልሎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከዚህ ፕሮግራም ጋር በማቀናጀት በከተማ ፕላን ዝግጅት፣ በመሬትና ቤቶች አቅርቦት፣ በከተሞች ገቢ አሰባሰብና በከተሞች የማስፈፀም አቅም እንዲሁም ከኮንስትራክሽንና መሰል ዘርፎች ጋር በማቀናጀት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ይበልጥ የሚያሳድገው መሆኑም ዛሬ በተከፈተው የሶስተኛው ዙር የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ ላይ ተመልክቷል። በዚሁ መድረክም የከተሞች አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቧል።

Via Negede
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢመደኤ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ወደ ሀገር ዉስጥ በሚገቡ እና ከሀገር በሚወጡ የቴክኖሎጂ እቃዎች ላይ ከአጋር አካላት ጋር የተቀናጀ የደህንነት ቁጥጥር በማድረግ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ሥራ መስራቱን ገለጸ፡፡ የኢመደኤ የሴኪዩሪቲ ክሊራንስ ማዕከል ሃላፊ አቶ መስፍን ሙሉነህ እንደገለጹት ኤጀንሲዉ በ2011 በጀት አመት የተለያዩ በገንዘብ የማይተመን ጥቃት ሊያደርሱ የሚችሉ መሳሪያዎች ወደ ሃገር ዉስጥ እንዳይገቡ ቅድመ ቁጥጥር በማድረግ በቴክኖሎጂዎቹ አማካኝነት የሚከሰቱ የተጋላጭነት ስጋት እና ጥቃት በመግታት ብሔራዊ ሠላምን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ስራ መሰራት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

Via #AMN
@tsegabwoldw @tikvahethiopia
#update የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቢኤ ኢትዮጲያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22/2012 ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#G7

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለሥልጣን በቡድን 7 ሃገራት ስብሰባ ላይ ድንገት በመገኘት ብዙዎችን አጀብ አሰኝተዋል።

ሞሐመድ ያቫድ ዛሪፍ ፈረንሳይ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 7 ውይይት ላይ ድንገት መገኘታቸውን የሚያሳብቅ አንድ ፎቶ ማሕበራዊ ድር አምባ ላይ ለቀዋል።

የሰባቱ ሃገራት መሪዎች ከሚያከናውነት ስብሰባ ጎን ለጎን የሚከናወኑ አነስተኛ ውይይቶች ላይ የተሳተፉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብዙዎችን ማስደነቃቸውን ምንጮች ዘግበዋል። በተለይ የአሜሪካ ልዑካን በከፍተኛ ባለሥልጣኑ 'ድንኳን ሰበራ' እጅግ መደነቃቸውን ከፈረንሳይ የሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ።

ሚኒስትር ዛሪፍ በትዊተር ገፃቸው ላይ 'ከፈረንሳይ ፕሬዝደንት እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ገንቢ የሆነ ውይይት አካሂደናል' ሲሉ ፅፈዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የቡድን 7 ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ከኢማኑዔል ማኽሮን ጋር መምከራቸው አይዘነጋም።

አሜሪካ እና ኢራን አሁን ላይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኙ መሆኑ የሰውየውን ድንገተኛ ጉብኝት 'ነገሩ ወዴት እና እንዴት ነው?' አድርጎታል።

ፈረንሳይ፤ ኢራን ከአሜሪካ እና ሌሎች አውሮጳ ሃገራት ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙት ለማለሳለስ ብትታርም ኢራን 'የበላችበትን ሳህን ሰባሪ' እየሆነች አስቸግራለች። በተለይ በቅርቡ ከነዳጅ ተሸካሚ መርከቦች ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ክስተት ኢራንን 'ነገር ተንኳሽ' አስብሏታል።

የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ሚኒስትር ዛሪፍ ከአሜሪካ ጋር ተስማምተን ነው እንዲጎበኙን ያደረግነው ቢሉም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ግን በጉብኝቱ እጅግ መደነቃቸውን አልደበቁም። የቡድን 7 ሃገራት - ብሪታኒያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጃፓን እና ዩናይትድ ስቴትስ፤ ቅዳሜ እና አሁድ 45ኛ ስብሰባቸውን አከናውነዋል።

Via #BBC
#update በሐዋሳ ከተማ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሞተር ቢስክሌቶች ከዛሬ ጀምሮ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ተፈቅዷ፡፡ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና የከተማዋ ፖሊስ  በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ኮማንደር ታደለ ዋሪዮ እንደገለጹት በከተማዋ ከአንድ ወር በፊት በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ላይ የታገደው እንቅስቃሴ ሕጋዊ ለሆኑት ተነስቷል። እንደ ኮማንደር ታደለ ገለፃ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የከተማዋ ፀጥታ እየተሻሻለ በመምጣቱና አንፃራዊ ሰላም በመስፈኑ ኮማንድ ፖስቱ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሞተር ቢስክሌቶች ብቻ በከተማዋ እንዲንቀሳቀሱ ወስኗል፡፡

የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ በበኩላቸው በከተማዋ መንቀሳቀስ የሚችሉት ሞተር ቢስክሌቶች የሰሌዳ ቁጥርና የሶስተኛ ወገን ያላቸው፣ ቦሎ የለጠፉ እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ መንጃ ፈቃድ ያላቸው ብቻ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ ለፀጥታ ሥራ ልዩ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሞተር ቢስክሌቶች ውጭ ሌሎች ሞተር ቢስክሌቶች ከንጋቱ 12፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉም አስታውቀዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-26-4
#update የቤኒሻንጉልና አማራ ክልል የጋራ ኮማድ ፖስት ባለፈው ሚያዚያ ከመተከል ዞን ተነስቶ ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተዛመተው ግጭት የተጠረጠሩ 169 ሰዎችንና ከ870 በላይ ቀስቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ የኮምንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የወረዳ አመራሮች እና የፀጥታ ኃይሎች ይገኙበታል።ኮማንድ ፖስቱ ፣በሁለቱ ክልሎች የጋራ ወሰኖች ላይ ባለፈው ሐምሌ ሥስት፣ የተከሰተውን ግጭት ለማብረድ፣የማረጋጋት ሥራ ከጀመረ ወዲህ  3ሺ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው ከመመለስ አንስቶ በርካታ የተዘረፉ ንብረቶችንም ማስመለሱን ገልጿል፡፡

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ሙገሳን እያገኙ ነዉ!

ካፍ በሚያዘጋጀው የዉስጥ ዉድድሮች አብዛኞቹ ጨዋታዎች የተመልካች ድርቅ እየመታቸዉ በዝግ በሚመስል መልኩ መካሄዳቸውን ቀጥሏል።

እንደሚታወቀው በክረምቱ በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ጥቂት ከሚባሉ ጨዋታዎች በስተቀር አብዛኞቹ በባዶ መካሄዳቸው ይታወቃል ይህም የካፍ አመራሮች ላይ ጥያቄ አስነስቶ ነበር።

ይህ ጉዳይ እየቀጠለ በመሄድ ክለቦች ላይ የራሱን የሆነ ተፅዕኖ አሳድሯል። በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የሻምፒዮንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን የማጣሪያ ጨዋታዎች ይህ ነገር ተስተዉሏል።

አፍሪካን ሶከር በድህረ ገፁ እንደዘገበው የኢትዮጵያን ክለቦች መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ በተጫወቱበት ጨዋታዎች ላይ የኢትዮጵያን እግርኳስ ደጋፊዎች አርአያ መሆን እንደሚችሉ አስፍሯል።

የካኖ ስፖርት አሰልጣኝ በበኩላቸው ክለቡ በእንዲህ አይነት የድጋፍ ድባብ እና ብዙ ቁጥር ባለው ተመልካች ዉስጥ ሲጫወቱ የመጀመሪያቸው መሆኑን ገልፀዋል።

አፍሪካን ሶከር በድህረ ገፁ ብዙ የእግርኳስ አፍቃሪያን በስታዲየም በመገኘት የተመለከቱትን ጨዋታዎች ሲጠቅስ የኢትዮጵያን ክለቦች ግምባር ቀደም ቦታዉን ሲይዙ ታሪካዊዉን የጋና ክለብ አሻንቲ ኮቶኮን ደጋፊዎችንም አካቷል።

Via African Soccer

ስፖርታዊ ጉዳዮችን ይከታተሉ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethsport
"የጥላቻ ንግግሮች የገነኑት መደበኛ መገናኛ ብዙሃን ስራቸውን ስላልሰሩ ነው —"ምሁራን

መደበኛ መገናኛ ብዙሃን የጥላቻ ንግግሮችን የመቀልበስና ለህዝብ ትክክለኛውን መረጃ የማድረስ ሚና ቢኖራቸውም ይህን ማድረግ እንዳልቻሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህራን ተናገሩ።

መምህራኑ ከአገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ ማግስት ጀምሮ እየመጣ ያለውን የመፃፍና የመናገር ነፃነት ተከትሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ ክብርን የሚነኩ የጥላቻ ንግግርች እየገነኑ መምጣታቸውን ይናገራሉ።

በተቋማትና በግለሰቦች ላይ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች በተለያዩ አካባቢዎች የግጭትና የግንኙነት መሻከር መንስኤ እየሆኑ መምጣታቸውንም ጠቁመዋል።

የጋዜጠኝነት መምህሩ አማኑኤል አብዲሳ እንደሚሉት በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎች የተአማኒነት ችግር ያለባቸውና በሂስና በጥላቻ ንግግር መካከል ያሉ በመሆናቸው ጉዳታቸው ያመዝናል።

ይህም የሆነው ማህበራዊ ሚዲያው የሚመራበት አሰራር ባለመኖሩና መደበኛ የመገናኛ ብዙሃኑ የስራ ውስንነት ስላለባቸው ነው ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአሸንዳ በዓል አከባበር #ማጠቃለያ በመጭው እሁድ በአዲስ አበባ በሚሌኒየም አዳራሽ ይደረጋል። #ETHIOPIA
ህዝቡ በመንገድ እጦት እየተሰቃየ ነው!

"የምትመለከቱት መንገድ #የወሊሶ_ከተማን ከተለያዩ አጎራባች ቀበሌዎች (ወራንን ዋ፣መኛንቆ፣ ኮኖ ፣ቂሌ፣ ጀሊሰ ጬካ፣ቆርኬ ፣ገርቦ እና ሌሎችንም የማያገናኝ ነው። ሕዝቡንም አሽከርካሪዎችንም እያሰቃየ ያለ መንገድ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በባሌ ዞን መዳ ወላቡ ወረዳ በሕገ ወጥ መልኩ ሲንቀሳቀስ የነበረ 340 ኩንታል ስኳር መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ ስኳሩ በኅብረተሰቡ ጥቆማና በጸጥታ ኃይሎች ክትትል የተያዘው ከወረዳው ወደ ጉጂ ዞን ሲጓጓዝ መሆኑን በመምሪያው የኮሙኒኬሽን ጉዳይ ዲቪዥን ባለሙያ ኮማንደር ናስር ኡመር ገልጸዋል። ኮድ 3 የሠሌዳ ቁጥር 79665 አዲስ አበባና ኮድ 3 የሠሌዳ ቁጥር 24685 ኢትዮጵያ በሆኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች ስኳሩን ሲያጓጉዙ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ተናግረዋል። አሽከርካሪዎቹ ለጊዜው መሰወራቸውንና የተያዘው ከ800ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ስኳር ለመንግሥት ገቢ መሆኑን ባለሙያው አመልክተዋል፡፡

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳምሰንግ በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋዩን እንዲያፈስ ግብዣ ቀረበለት!

ከሳምሰንግ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዎን ክዮንግ ኪም የተወያዩት ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ትልቁ አለም አቀፍ ኩባንያ በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ በሀገሪቱና በቀጣናው በጎ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጋብዘዋል። በአሁኑ ወቅት እየተካሄዱ ያሉ የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያከብሩ የገለፁት ኪም በኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚመረምሩ ገልፀዋል።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሁለት የተከፈሉት የሲአን አመራሮች ውዝግብ!

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) "ህጋዊ አመራሮች ነን" በሚሉ ሁለት ወገኖች መካከል አለመግባባት መከሰቱ ተሰማ። በዶክተር ሚሊዮን ቱማቶ የሚመራው ቡድን የሲአን ህጋዊ አመራር መሆኑን በመግለጽ የንቅናቄውን የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ማካሄዱን አስታውቋል። በአቶ ዱካሌ ላሚሶ የሚመራው ሲአን በበኩሉ፣ ሌላኛውን ቡድን "የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ በከባድ የስነ ምግባር ጉድለት ያሰናበታቸው ግለሰቦች ስብስብ ነው" ሲል ወንጅሏቸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ከሁለቱም ወገኖች የአቤቱታ ማመልከቻ እንደደረሰው በማረጋገጥ በቅርቡ ጉዳዩን በመመርመር ውሳኔውን እንደሚገልፅ አስታውቋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፖሊስ አንድን ወጣት #ሲደበድብ የሚታይበት የዛሬው ቪዲዮ በበርካቶች ዘንድ #መነጋገሪያ ሆኗል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏷BBC የአማርኛው አገልግሎት የዛሬውን ቪድዮ የቀረፀውን ወጣት አነጋግሮታል! #ADDISABEBA #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ሲሰራጭ በነበረው ቪድዮ ዙርያ ነገ መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የማምረቱ ስራ እዚህ ደርሷል!

በትምህርት ሚኒስቴር ሲሰራ የቆየው በ2011 በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ ተማሪዎች መጪውን የትምህርት ዘመን በመልካም ስነ-ልቦና እንዲጀምሩ እየተሰራ ካለው ስራ ጎን ለጎን በትምህርት ቁሳቁስ ለመደገፍ እየተመረተ ያለው ደብተር ወደ መጠናቀቁ ደርሷል፡፡ በቀሪው የአንድ ሳምንት መርኃግብር የማሸግና የማከፋፈል ስራዎች ይሰራሉ፡፡ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም እስካሁን ላሳያችሁት ቅን ትብብራችሁ ምስጋና ይገባችኃል፡፡ አሁንም በቀረው ጊዜ በዚህ መልካም ተግባር በመሳተፍ አሻራችሁን አሳርፉ፡፡
ተመዝገቡ 📞 0911485705

መልካምነት ለራስ ነው መልካም ሰርተን መልካምነትን ለትውልድ እናውርስ፡፡
@tsegabwolde @tikvahwthiopia