TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ከተሰጣቸዉ እዉቅናና ፍቃድ ዉጪ የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ የግልና የመንግስት ኮሌጆችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡ ኤጀንሲዉ ከእዉቅናዉ ዉጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡

በአዲስ አበባና አካባቢዋ 18 የግል ኮሌጆችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶችን መዝጋቱን አስተዉቋል፡፡ እንዲሁም 4 የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከእዉቅናዉ ዉጪ ከግል የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር ሲሰጡ የነበረዉን አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን የኤንጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ሞታ ተናግረዋል፡።

በተለይም በግል ዘርፍ የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አብዛኞቹ ደረጃቸዉን ባለጠበቁ የትምህረት ቅጥር ግቢ ዉስጥ እንደነበር ጠቁመው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ኤጀንሲዉ ቁርጠኛ አቋም መያዙንም ምክትል ዳሬክተሩ አስታዉቀዋል።

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያጣላን ታሪክ ሳይሆን ተረክ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ተረኮች ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡ አንድ ግለሰብ በምግብ ቢመረዝ ቢበዛ እራሱን ነው የሚገለው፤ ሃሳቡ ቢመረዝ ግን እራሱን ብቻ ሳይሆን አካባቢን ያጠፋል፡፡” ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ

#AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ጽዳት ከውጭ አይመጣም፤ጽዳት የሚመጣው ከውስጥ ነው፡፡ የውስጥ ማንነት ከጸዳ ውጪ የምናየው ነገርም ንጹህ ይሆናል፡፡” ቤተልሄም ለገሰ/የፍልስፍና ባለሙያ/

#AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ልቦና የሚቆሽሸው እውቀት ላይ ያልተመሰረተ ተግባር ሲኖር ነው፡፡ የግለሰብ ልቦና የማህበረሰብ ልቦናን ይገነባል፡፡ የማህበረሰብ ልቦና ደግሞ በዕድር፤በእቁብ በመሳሰሉት ይገነባል፡፡” ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ/ገጣሚ እና ደራሲ/

#AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“አዕምሮ ሶስት ትልልቅ ነገሮች አሉት፡- እሳቤ፤ትውስታ እና እይታ፡፡ የእነዚህ ነገሮች መመረዝ አዕምሮን ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋላጭ ያደርጋል፡፡” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ/የስነልቦና ባለሙያ እና መምህር/

#AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሞራልን ወደ ቁስ ለማውረድ ሃሳብ ያስፈልጋል፤ቁሱ አለም በሃሳብ አለም ይገዛል፡፡ የሃሳቡ አለም በሞራል አለም ይገዛል፡፡ሃሳብ በሞራል ካልተገዛ አደገኛ እና አጥፊ ሊሆን ይችላል፡፡ ቁስም በሃሳብ ካልተገዛ ትክክል አይሆንም፡፡” ዶ/ር ምህረት ደበበ/የአዕምሮ ሃኪም/

#AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#uodate በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ለንባብ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጽሐፍትን በማሰባሰብ ለአማኑኤል የአእምሮ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለገሱ፡፡ ወጣቶቹ ከአዲስ አበባ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር በመተባበር በሆስፒታሉ ኑ! መደርደሪያዉን እንሙላ በሚል መሪቃል መጽሐፍ የማሰባሰብ ፕሮግራም አከናውነዋል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢመደኤ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ወደ ሀገር ዉስጥ በሚገቡ እና ከሀገር በሚወጡ የቴክኖሎጂ እቃዎች ላይ ከአጋር አካላት ጋር የተቀናጀ የደህንነት ቁጥጥር በማድረግ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ሥራ መስራቱን ገለጸ፡፡ የኢመደኤ የሴኪዩሪቲ ክሊራንስ ማዕከል ሃላፊ አቶ መስፍን ሙሉነህ እንደገለጹት ኤጀንሲዉ በ2011 በጀት አመት የተለያዩ በገንዘብ የማይተመን ጥቃት ሊያደርሱ የሚችሉ መሳሪያዎች ወደ ሃገር ዉስጥ እንዳይገቡ ቅድመ ቁጥጥር በማድረግ በቴክኖሎጂዎቹ አማካኝነት የሚከሰቱ የተጋላጭነት ስጋት እና ጥቃት በመግታት ብሔራዊ ሠላምን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ስራ መሰራት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

Via #AMN
@tsegabwoldw @tikvahethiopia
#update የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቢኤ ኢትዮጲያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22/2012 ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia