TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት⬆️

አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ሰራተኛ የእቴጌ ጣይቱን ሀውልት በተመለከተ በሶሻል ሚድያ እየተባለ ያለው ነገር "#ሀሰት ነው" ሲል ለENF የተናገረ ሲሆን "ትናንትና እኮ ም/ከንቲባው አቶ ታከለ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያለው መረጃ ሁሉ እንደ #እውነት ከተወሰደ #አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጥራል ያለው እሱን ለመግለፅ ነው" ሲል አብራርቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በምእራብ ወለጋ #የኦነግ ማሰልጠኛ ካምፕ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ቦታዎች ላይ ዛሬ ጥዋት #የአየር_ጥቃት መፈፀም መጀመሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። . . የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ... Ethiopia Defense Force begins #airstrike in western Oromia; says targets are OLF military training #camps. Ethiopian…
ኦነግ ላይ #ተሰነዘረ ስለተባለው የአየር ጥቃት!

#ጋዜጠኛ_ኤልያስ_መሰረት(AP)

ሰሞኑን አንዳንድ የሀገር ውስጥ ሚድያዎች በኦነግ ማሰልጠኛ ካምፖች ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን ሲዘግቡ ሰንብተዋል። አንድ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ትናንት ምሽት anonymously የነገሩኝ ግን ፈፅሞ የተለየ ነበር፦

"ያው እንደምታውቀው መከላከያ የራሱ ስርአት ስላለው እና እኔም ወታደር ስላልሆንኩ ዝም ብዬ በነሱ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት አልችልም። ልነግርህ የምችለው ግን ምንም አይነት የአየር ጥቃት አየር ሀይል አልሰነዘረም። የአየር ቅኝት ሊኖር ይችላል። በሂሊኮፕተር ተደብድበው ቢሆን የኦነግ አመራሮች እስካሁን ዝም ይሉ ነበር ወይ ብለህ ራስህን ጠይቀው እስቲ። እኔ አሁን ያለሁት አሶሳ ቢሆንም ባለኝ መረጃ በጄት እና ሂሊኮፕተር #ድብደባ ደረሰ የተባለው ፍፁም #ሀሰት ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News‼️

"በጅግጅጋ ከ59 ሰዎች በላይ ተገደሉ። 7 ከፍተኛ ባለስልጣት በቁጥጥር ስር ዋሉ።" በሚል በፌ ቡክ እና በዩትዩብ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰት ነው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወ/ሮ ሰናይት...‼️

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ፅ/ቤት በቅርቡ ሸገር ሬድዮ ላይ ቀርባ ስለ #መታወቂያ አሰጣጥ አስተያየቷን የሰጠችው ወ/ሮ ሰናይት ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በነበራት ቆይታ ይህን ብላለች፦

"ብዙ ተወርቶ እንደነበረው አስተያየቱን ለሸገር ሬድዮ ከሰጠሁ በሁዋላ ወደ ስራ አልተመለስኩም ነበር። ትናንት ግን #ወደስራ_ተመለሺ የሚል ደብዳቤ ተፅፏል። አሁን ወደ ቢሮ እየሄድኩ ነው። ውጤቱን በሁዋላ እነግርሀለው። ሰዎች #እያስፈሯሯት ነው ተብሎ በሶሻል ሚድያ የተወራው ግን #ሀሰት ነው። እዛ ደረጃ ነገሮች ከሄዱ ወደ መንግስት አካላት እና ሚድያዎች እሄዳለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ

ዛሬ በሀዋሳ በመንግስት ሀላፊዎች ላይ የተፈፀመው #ድብደባ!

ከደቂቃዎች በፊት አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከደቡብ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ከሆኑት ከዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው ጋር በስልክ ቆይታ አድርጎ ነበር ስለጉዳዩ ይህ ብለዋል፦

"በመጀመርያ በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው። ጠዋት እኔ ስመራው የነበረው ስብሰባ ሌላ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ወጣቶች መጥተው ስብሰባው ይቁም ሲሉ confront ሳናረጋቸው አመራሮችን ወዲያው #በትነናል። የወላይታ ዞን ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋ ስምዖን ላይ ግን #ጥቃት ተፈፅሟል። ይህ ስብሰባ ይካሄድበት የነበረው አዳራሽ ውስጥ ከመጡት ወጣቶች ጋር #ግጭት ነበር። ዝርዝሩን አላውቅም። አሁን ሰላም ነው። አቶ ፀጋ ለህክምና ሶዶ ደርሷል። ከትንሽ ደቂቃ በፊትም አናግሬዋለሁ።"

ማነው ድብደባውን የፈፀመው ተብለው በጋዜጠኛው ለቀረበላቸው ጥያቄ፦

"እከሌ ኤጄቶ ነው እከሌ አይደለም ለማለት አልችልም። ግን ሶሻል ሚድያ ላይ ኤጄቶ ስብሰባው እንዲበተን ይፈልጋል የሚል መልእክት ጠዋት ስብሰባ ከመግባቴ በፊት አንብቤ ነበር።"

የሶሻል ሚድያ ምስል: አቶ ፀጋ ስምኦን

Via Elias Mesret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የደቡብ ክልል #ምክትል_ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶክተር #ጌታሁን_ጋረደው በወጣቶች #ታግተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና #ሀሰት ነው

ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው: "...በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች #እንደታገትኩ የተገለፀው #ሀሰት ነው።"

Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በነበረው ግጭት ‹‹የሦስት ተማሪዎች ሕይወት ነው ያለፈው›› እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው ሲሉ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር #ኪሮስ_ጎሹ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀሰተኛ_መረጃ:ኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ ከኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ራሱን #አገለለ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው። ክለቡ እስካሁን ራሴን ከሊጉ #አላገለልኩም ብሏል።

Via #ቴዎድሮስ_ታከለ/ሶከር ኢትዮጵያ/
@tikvahethsport
#FakeNews የአማራ ክልል ልዩ ኃይል #ሊፈርስ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ/በተለይም በfacebook/ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews ሌተናል ጄነራል #ሃሰን_ኢብራሂም ታሰሩ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰት ነው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeBot

"የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር ልናንበሸብሽዎት በ ቴሌግራም መጥተናል። ይህ bot ቁጭ ብለው ገንዘብ የሚያፍሱበት ነው። በዚህ ቦት 1 ሰዉ ሲጋብዙ 1 ብር ያገኛሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን።"

#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ ስምን እየተጠቀሙ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መልዕክቶችን በርካታ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ሲቀባበሉት ተመልክተናል ይህ ፍፁም #ሀሰት ነው። መልዕክቱም የሚሰራጨው በሀሰተኛ ገፅ ነው!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia