TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን⬇️

በቡራዩና በመዲናዋ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የተከሰቱ #ግጭቶች ላይ የደረሱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ቡድን #ከዛሬ ጀምሮ መሰማራቱን የኢትዮጰያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ይህንን ያለው በዛሬው ዕለት ግጭቱን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኀን በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።

በመግለጫው ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር እንደተናገሩት በደረሰው ግጭት በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን አንስተዋል።

ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለ #ለከፋ ጉዳት ያደርሳል ያሉት ኮሚሽነሩ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም እና ተዘዋውሮ የመስራት እንዲሁም በሰላም የመኖር መብቶችን ለማስከበር ጠንከር ብሎ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ እስከ አሁን የደረሰውን ጉዳት መንስዔ፣ ጉዳት እና ስፋት አጣርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሪፖርት በማድረግ ያጠፉ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋልም ተብሏል።

በተለያዩ ቦታዎችም የተከሰተውን ግጭት እንዲረጋጋ ከመንግስት ጋር እየሰራ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በመግለጫው የፌደራል እና የክልል #ጸጥታ አካላትም ሚናቸውን #በአግባቡ እንዲወጡ አሳስቧል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት🔝

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር #ከዛሬ ጀምሮ እንደሚሠማራም ተገልጧል፡፡

በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የተከሰተውን ግጭት ለማርገብ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በተመለከተ የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጎንደር ላይ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል #አለምነው_አየነ እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘላለም_ልጃለም ናቸው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር ከዛሬ የካቲት10/2011 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሠማራም በመግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

በፀጥታ ኃይሉ አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ የተከለከለከሉ ተግባራትም በመግለጫው ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከጎንደር-መተማ መስመር ከመንገድ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም፤ በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ #ክልከላ ተደርጓል፡፡ በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሣሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ እንደማይችልም ታውቋል፡፡

ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል እርምጃ እንደሚወሰድበትና ‹‹ሰላም ለማስከበር›› በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፈቃድ ውጭ መሣሪያ ይዞ #እንዳይንቀሳቀስ እገዳ ተላልፏል፡፡

በመግለጫው የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ኃይሉ ጋር እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሞተር እገዳ~በሀዋሳ ከተማ!

በሐዋሳ ከተማና በዙሪያዋ አጋጥሞ ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሲባል በከተማዋ ውስጥ ሞተር ሳይክሎች እንዳይቀሳቀሱ እገዳ መጣሉን ቢቢሲ ያናገራቸው የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች አረጋግጡ።

እርማጃው የተወሰደው ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው ብለው የሚያምኑት የከተማዋ ነዋሪዎች እገዳ መጣሉ በክልሉ መገናኛ ብዙሃን በኩል እንደተገለጸ ጠቅሰዋል። አሽከርካሪዎች ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት በሐዋሳ ከተማ በብዛት ይተዩ የነበሩት ሞተር ሳይክሎች #ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ እንደሌሉ የገለጹት አንድ ነዋሪ ትራፊክ ፖሊሶችም መንገድ ላይ ያገኟቸውን ሲያስቆሙ መመልከታቸውንና መኪኖችና ባጃጆች ግን በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ እንደሚታዩ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia