TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሜሴንጀር እና ዋትስአፕ በአብዛኛው የዓለም ክፍል በአግባቡ #እየሰሩ_አይደለም። ተጠቃሚዎች ፎቶ እና ቪዲዮ መመልከት እና መጫን አይችሉም። የፌስቡክ ቃል አቀባይ ችግሩ መፈጠሩን አምነው #መፍትሔ_ፍለጋ እየሰራን ነው ብለዋል። ባለፈው መጋቢት ፌስቡክ በሶስቱ መተግበሪያዎች ላይ ተመሳሳይ እክል ገጥሞት ነበር።

Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት የአቢዬ ግዛት የዘመቱ 860 ገደማ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ 30 ወታደራዊ ሰራተኞችና የተባበሩት መንግሥታት ፖሊሶች የግዛቲቱን ሰላም እና ፀጥታ ለመስጠበቅ ለነበራቸው ሚና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሜዳይ ተሸለሙ። በአቢዬ የተባበሩት መንግሥታት ጊዜያዊ የጸጥታ ጥበቃ ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴየር ጄኔራል ሙሉ ገብረሕይወት በሽልማቱ ወቅት በአቢዬ የደፈሩ ወታደሮችን አመስግነዋል። የኢትዮጵያ ሴት ወታደሮች የአካባቢው ሴቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ለተጫወቱት ሚና ተመስግነዋል።

Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia