TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አዲስ_አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከሌሎች ሴክተር ተቋማት ጋር በመሆን በቅርቡ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የንግድ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መስፍን አሰፋ እንደገለጹት ከነጋዴው የኅብረተሰብ ክፍል ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ውይይቶች ተደርገዋል፤ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ አካላት ላይም ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት መካከል የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ሱቆች፣ ዳቦ ቤቶች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ የእህል መነገጃ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች እንደሚገኙበት ኃላፊው መናገራውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

በተለይም ዋጋ የጨመሩ፣ ያለ ደረሰኝ ግብይት የፈጸሙ፣ ግራም ያጎደሉና በተለያዩ መንገዶች በኅብረተሰቡ ላይ ጫና ያደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ነው የተገለጸው፡፡

በተወሰደ እርምጃም መሻሻሎች እንደታዩና አልፎ አልፎም ከዚህ በፊት ከነበሩበት ዋጋ በታች የወረዱ ግብይቶች መኖራቸውን ጭምር ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

የቁጥጥር ሥራን ከማጠናከር በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ምርቱን በተሻለ ዋጋ የሚያገኝበትን አማራጮች በመፍጠር፣ በምርትና በሽያጭ ሂደት ውስጥ ምንም እሴት የማይጨምሩ ነገር ግን በሕገ ወጥ መልኩ በገበያ ስርዓት ውስጥ የተሰገሰጉ ደላሎችን በማስወገድ ኅብረተሰቡ በቀጥታ ከገበሬ ምርቱን ማግኘት እንዲችል ከተለያዩ ክልሎች በተለይም ከኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎች ጋር እየሠራ መሆኑንም አቶ መስፍን ገልጸዋል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢቢኤስ(EBS) ቴሌቪዥን ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 50ሺ ደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ አራት የመንግስት ት/ቤቶች እድሳት ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

Via @mayorofficezAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝን በአስር ዓመት ውስጥ ማጥፋት የሚያስችል ብሔራዊ ዕቅድ እያዘጋጀ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከዓለም የጤና ድርጅትና ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመሆን በብሔራዊ ዕቅዱ ዙሪያ ምክክር አድርጓል። በቅርቡ በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ 986 ሰዎች ተጠቂ መሆናቸውም ይታወቃል። አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባ በሽታው በስፋት የተገኘባቸው ሥፍራዎች ናቸው።

የጤና ሚኒስቴርም ይህንን ከግምት በማስገባት የበሽታውን ስርጭት በአስር ዓመት ውስጥ ለማስቆም የሚያስችል ስራ እንደሚሰራ አመልክቷል።

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሂጅራ_ባንክ

ሂጅራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ሂጅራ ባንክ አክሲዮን መሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሄራዊ ባንክ ካገኘ አንድ ወር እንደሞላው ነው የተገለጸው፡፡

የሂጅራ ባንክ አክስዮን አደራጆች ሰብሳቢ አቶ አህባብ አብድላ እንዳሉት ላለፉት ሁለት አመታት በሀገር ደረጃ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲፈጠር የተለያዩ ጥናቶችን ሲያከናውኑ እንደቆዩ ተናግረዋል፡፡ ባንኩ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ስርአትን በማበልጸግ ለዘመናት በሀገራችን ምጣኔ ሀብታዊ እንቅቃሴ ውስጥ ባለው ውስን ተሳትፎ የሚታወቀውን የህብረተሰብ ክፍል በሀገሪቱ እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲኖረው የማስቻል ስራ መስራቱንን ገልጿል።

የሂጅራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አነስተኛው የአክሲዮን ሽያጭ 30ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ሽያጭ ደግሞ 20 ሚሊየን ብር ነው ተብሏል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ አንድ ቢሊየን ብር የአክሲዮን ሽያጭ ለመሸጥ እንዳሰበም ተገለጿል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በህጻናት ልጆች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው አዛውንት በጽኑ እስራት ተቀጣ፦

የ81 አመት አዛውንት የሆነው ተከሳሽ ሰኢድ አብዱልከሪም አብዱልሃቢብ በታዳጊ ህጻናት ላይ የግብረ-ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል በመፈፀሙ በዓቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 627/1/ እና 627/3/ ሥር የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ተከሳሽ ሰኔ 27/2008 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 4፡30 ስዓት ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ከሊፋ ህንጻ አካባቢ በ12 አመቷ ህጻን ላይ የግብረ ስጋ ግንኙነት በመፈጸሙ እና በተመሳሳይ ቦታ ባልታወቀ ቀን ግንቦት 2009 ዓ.ም እና ጥር 2009 ዓ.ም 7 አመት በሆናቸው ሶስት ህጻናት ላይ የግብረ ስጋ ግንኙነት የመሰለ ድርጊት በመፈፀሙና ይህ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀሉም በማስረጃ በመረጋገጡ ዓቃቤ ህግ ክሱን መስርቶበታል፡፡

ተከሳሽ በአራቱም የግል ተበዳይ ህጻናት ላይ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል ሲል ዓቃቤ ህግ ባቀረባቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤት ያስደመጠ ሲሆን ጉዳዩን የተከታተለው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበውን የሰውና የህክምና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡

ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማየት ተከሳሽ ከእድሜያቸው አንጻር ድርጊቱን መፈጸማቸው ነውር በመሆኑ አንድ የቅጣት ማክበጃ እና ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና የተለያዩ በሽታዎች ያሉበት መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሶስት የቅጣት ማቅለያዎችን ይዞለት ሰኔ 02/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ10 አመት ጽኑ እስራት ይቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሶዴፓ 21ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በጅግጅጋ እየተከበረ ነው። የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 21ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በጅግጅጋ እየተከበረ ነው።

የምስረታ በዓሉ የፓርቲው ሊቀመንበርና ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፌ ኡመር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

ፓርቲው በዓሉን "የህግ የበላይነት ፣ዴሞክራሲና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለላቀ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል ነው እያከበረ የሚገኘው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የከተማ አስተዳደሩ የሚሰራቸውን የልማት ስራዎች እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የከተማውን ነዋሪ ችግር ለመቅረፍ በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች እያደረገ ላለው ድጋፍ ኢ/ር ታከለ ኡማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ይናገር ደሴ በበኩላቸው ባለፉት በርካታ ዓመታት በከተማዋ ውስጥ የተከማቹ ችግሮችን ለመፍታት እና ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡

በቀጣይነትም በከተማዋ ውስጥ ያሉ አንገብጋቢ ችግሮችን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ለጀመራቸው ፕሮጀክቶች ብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ አቅርቦት እንደሚያደርግም ዶ/ር ይናገር ደሴ ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደኢህዴን

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ከነገ ጀምሮ ከንቅናቄው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ምክክር ሊያካሂድ እንደሆነ ተሰማ። የጀርመን ራድዮ ታማኝ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል እንዳለው ነገ በሚጀምረው በስብሰባ ንቅናቄው በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄደው ልዩ ስብሰባ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ ምክክር ያደርጋል። ውይይቱ በተለይም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የራስ ገዝ ወይም በክልል የመደራጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ በተካሄደው ጥናት እና አፈጻጸም ዙሪያ ያተኩራል ተብሏል። ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ይኽው የምክክር መድረክ በሃዋሳ እና በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ምንጮቹ አመልክተዋል። በስብሰባው ላይ የዞኖች እና የወረዳዎች አመራሮች የካቢኔ አባላት በከፍተኛ እና በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የንቅናቄው ካድሬዎች እንደሚሳተፉ ራድዮ ጣቢያው ጨምሮ ግ0ልጿል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SMN የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራሮች በሀዋሳ ከተማ ከተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። አመራሮቹ ስላሉበት ሁኔታ ከቤተሰቦቻቸው መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርጊያለሁ። ከታሳሪ ቤተሰቦች አንድ ሰው በስልክ አነጋግሬ ያገኘሁትን መረጃ ወደበኃላ ወደናተ የማደርስ ይሆነል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት፦

* አፈፃፀሙ 43 በመቶ ብቻ ነው፤
* ግንባታውን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 30 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፤
* የፕሮጀክቱ እቃዎች በጸሐይና ዝናብ ከጥቅም ውጪ እየሆኑ ነው፤

የተራራው ግማሽ ጎን ተሰንጥቋል። በተሰነጠቀው ተራራ ስር ሰፊ ደልዳላ ሜዳ ተሰርቷል። በተሰራው ሜዳ ላይ እዚህም እዚያም ጅምር የፋብሪካ መትከያ ህንፃዎች፣ መጋዘኖች፣ ቢሮዎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ ጅምር የኤሌክትሪክ ማመንጫ ፋብሪካዎችና ሌሎች ህንፃዎች ጉች ጉች ብለው የአካባቢውን ተፈጥሮ በዙሪያቸው እየተመለከቱ ቆዝመዋል። ወደ ቤቶቹ ውስጥ ሲገባ በእርጥበት ወይበዋል። ፍየሎች ከዝናብ ስለሚጠለሉበት ከእነርሱ ጠረን ጋር ተዳምሮ ሰፋፊዎቹ ህንፃዎች ውስጣቸው በመጥፎ ጠረን ታውዷል። በአጠቃላይ የዋሻ ዘመንን ኑሮ ያስታውሳል።

ከአንደኛው ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ ለመድረስ የሚያታክተው ሰፊ ግቢ በአረምና በሳር ተወርሯል። ግቢው ከጫፍ እስከ ጫፍ በቁርጥራጭ ፣ ትላልቅና ወፋፍራም ብረቶች፣ በትናንሽና ትላልቅ ማሽኖች፣ ኮንቴይነሮች፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ተዘርዝረው በማያልቁ ቁሶች ተሞልቷል። ዝናብ፣ ቁሩና ጸሐይ የተፈራረቀባቸው ቁሶች በዝገት መልካቸው ጠፍቷል። ይህ የሀገር ሀብት ብክነትና ብልሽት ሲታይ ህሊናን በኀዘን ይሸነቁጣል።

የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ በዓመት 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል አውጥቶ በመጠቀም 90 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ፣ በዓመት 300ሺ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ፣ 60ሺ ቶን ሜታኖል፣ 5ሺ ቶን አሞኒያ፣ 4ሺ500 ቶን ሰልፈር እንዲሁም ኦክስጂን፣ ካርቦንዳዮክሳይድ፣ ናይትሮጂንና አርገን የሚባሉ ጋዞችን እንዲያመርት የታለመለት ግዙፍ ፕሮጀክት ነበር።

Via ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢራን ያገተችውን የብሪታኒያ መርከብ ከእገታ ነጻ እንደምትለቅ ፍንጭ ሰጠች። ፕሬዚዳንት ሀሰን ሮሃኒ “ብሪታኒያ በሃምሌ ወር መጀመሪያ ያገተችውን መርከባችንን ከለቀቀች ኢራንም ተመሳሳይ መልስ ትሰጣለች” ብለዋል። “ግሬስ-1” የተሰኘው ግዙፍ መርከብ የአውሮፓን ማዕቀብ በመጣስ ነዳጅ ጭኖ ወደ ሶሪያ ሲጓዝ በሃምሌ ወር መጀመሪያ የጂብራልተር የባህር ዳርቻ ላይ በብሪታኒያ መታገቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ የብሪታኒያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልብ ስቴና ኢምፔሮ የተሰኘ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሆርሙዝ ሰርጥ ሲያልፍ በኢራን ታግቷል። ኢራን መርከቡን ያገትኩት የአሳ ማጥመጃ መርከብን ስለገጨ እና ዓለም አቀፋዊ ህግን ስለጣሰ ነው ብላለች። ብሪታኒያና ኢራን በመርከብ እገታ እርስ በእርስ ወደ ውጥረት መግባታቸውን አልጄዚራ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
animation.gif
455 KB
40/60 የጋራ መኖሪየ ቤት...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ ዕግድ የተጣለባቸውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለይቶ እንዲያሳውቅ በፍርድ ቤት ታዘዘ፡፡

ትዕዛዙን የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነው፡፡ ኢንተርፕራይዙ ባለሦስት፣ ባለሁለትና ባለአንድ መኝታ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በየትኞቹ ሳይትና ብሎክ እንደሚገኙና የተሰጣቸውን የቤት ቁጥር ጭምር ለይቶ እንዲያሳውቅ ተነግሮታል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ትዕዛዙን ፈጽሞ የሚቀርበው ሐሙስ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕግድ የተጣለባቸው በምዝገባ ወቅት መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙ በርካታ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ የዕድሉ ባለቤቶች እንደሚሆኑ ተነግሯቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ውል ከፈጸሙ በኋላ፣ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. የከተማ አስተዳደሩ ከ18 ሺሕ በላይ የሚሆኑ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን፣ ከ40 በመቶ በላይ የቆጠቡ ሁሉ በዕጣው በማካተቱና በማውጣቱ ምክንያት ክስ በመመሥረቱ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ መጀመርያ ክስ ባቀረቡት 98 ሰዎች አቤቱታ መሠረት ሁሉንም ዕጣ የወጣባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችና በቀጣይ የሚወጡትም ጭምር ዕግድ የጣለ ቢሆንም፣ ቆይቶ ክስ ባቀረቡት ልክ ብቻ በማገድ የሌሎችን ቤቶች ዕግድ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ መቶ በመቶ መክፈላቸውን በመግለጽ ለፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 700 መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእነ አብዲ መሀመድ ዑመር የክስ መዝገብ 12 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡ በእነ አብዲ መሀመድ ዑመር የክስ መዝገብ የቀረቡ ተከሳሾች ‹‹ወንጀሉን አልፈፀምንም፤ ጥፋተኛም አይደለንም›› አሉ፡፡ በእነ አብዲ መሀመድ ዑመር የክስ መዝገብ ላይ 14 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን መቃወሚያ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ ብይን ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/A-07-24
የጥናት ውጤቱ ይፋ ተደረገ!

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ በደቡብ ክልል የሚነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምላሽ ለመስጠት ያስጠናው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ ሆነ።

ላለፉት ሰባት ወራት በምሁራን የተካሄደው የደቡብ ክልል አዲስ አከላለልን የተመለከተው ጥናት ውጤትን በተመለከተ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/A-07-24-2
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጀርመን ኤርትራዊ ወጣት ላይ በደረሰበት ጥቃት በርካቶች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን ገለፁ። ከቆዳው ቀለም ጋር ተያይዞ በጥይት በተመታው ኤርትራዊ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጀርመን ዋችተርስባች ከተማ ለተቃውሞ መውጣቸው ተገለፀ፡፡
የጀርመን የአገር ውስጥ ሚድያ እንደገለፀው የ26 አመቱ ኤርትራዊ ወጣት በጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳት ቢያጋጥመውም አሁን ላይ እየተሻለው መሆኑ ተገልፅዋል፡፡

የፍራንክፈርት ግዛት አቃቤ ህግ ቃል አቀባይ አሌክሳንደር ባድል እንዳሉት የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከውጪ ሃገር ዜጎች ጥላቻ የመነጨ ሊሆን ይችላል ያሉትን ጥቃት እየመረመሩ ይገኛሉ፡፡

ቃል አቀባዩ ጨምረውም ጥቃት አድራሹ በዘፈቀደ እንደተኮሰ ገልጸው እራሱን ማጥፋቱን አመልክተዋል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኛው አጎራባች ከተማ መኪና ውስጥ ህይወት አልባ ሆኖ መገኘቱን ገልፆ በሆስፒታል መሞቱ ተረጋግጧል ብሏል፡፡

የተጠርጣሪው ቤትና መኪና ሲፈተሸም ሁለት በከፊል አውቶማቲክ የሆኑ ህጋዊ ሽጉጦች መገኘታቸውንና ተጠርጣሪው የዘረኝነት ጥቃት የመፈፀም ዝንባሌ እንዳለው ተረጋግጧል መባሉን ዶቼ ዌሌ ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

መርማሪዎች በበኩላቸው የ55 አመቱ ጥቃት አድራሽ ቀኝ አክራሪ ናሽናሊስት መሆኑን እስካሁን አላረጋገጥንም ብለው ምርመራው መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ/#ENA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቤኒሻልጉል ጉሙዝ ክልል እና የሱዳኑ ብሉናይል አስተዳደር ለሁለቱ ሕዝቦች ሠላም እና የልማት ተጠቃሚነት የጀመሯቸውን ሥራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሱዳን ሪፐብሊክ የብሉናይል አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት ምክክር በአሶሳ ከተማ ትናንት ተጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደቡብ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሚታዩ የክልል እንሁን ጥያቄዎችን በጥናት ለመፍታት የክልሉ ገዥ ፓርቲ ደኢህዴን ሲያስጠና ቆየው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ ሆነ።

የጥናት ቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት 20 አባላት ያሉት የጥናት ቡድን ተዋቅሮ ላለፉት ሰባት ወራት ሰፊ ጥናት ሲያካሂድ ቆየቷል። በዚህም መሰረት ሶስት አማራጮችን አስቀምጧል ብለዋል ምክትል ሰብሳቢዋ።

በጥናቱ የተለየው የመጀመሪያው አማራጭ አብዛኛው የክልሉ ህዝብ አሁን ያለው የክልሉ አደረጃጀት ቢቀጥል የህዝቦችን አብሮነትና ያጠናክራል፤ ጠነካራ የደቡብ ህዝቦች ክልልንና የኢትዮጵያን አንድነት ያጠናክራል የሚል ነው።

በጥናቱ የተለየው መጀመሪያ አማራጭ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሮ ተቀባይነት የሚያጣ ከሆነ በጥናቱ በሁለተኝነት የተለየው አማራጭ ደግሞ ክልሉን በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በመክፈል ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ የፍተሃዊነት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

በጥናቱ በሶስተኝነት የተቀመጠው ሃሳብ ደግሞ ሁለቱ አማራጮች ተግባራዊ የማይሆኑ ከሆነና ሁኔታው ከክልል አልፎ በአገሪቱ ሰላምና አንድነት ላይ ጫና የሚፈጥር ከሆነ ጉዳዩ ለጊዜው ቢቆይና በእርጋታ ቢታይ የሚል ነው። እንደጥናት ቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች በላይ ለጥናቱ በመረጃ ሰጪነት ተሳትፈዋል።

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመኖሪያ ቤት ችግር ይፈታ ይሆን

በመጪው አዲስ ዓመት በተለይ #ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግሥት ሰራተኞች በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ተናገሩ። ግንባታው የሚካሄደው እንደከዚህ ቀደሙ በመንግሥት ሳይሆን በግል ተቋማት ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው መንግሥት የመቆጣጠርና የማስተባበር ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግረዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SMN

ከቀናት በፊት ከሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሀዋሳ ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና እና ምክትል ስራ አስኪያጆችን ጨምሮ የተቋሙ የቦርድ አባላት መታሰራቸው ይታወቃል። ለመሆኑ ታሳሪዎቹ በምን አይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?? ብዬ ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች መካከል አንድ ሰው አናግሪያለሁ...የታሰሩት በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንደሆነ የገለፁልኝ እኚህ ሰው ተከታዩን ብለዋል፦

"አሁንም ቢሆን #እየተሳቀቅን ነው ሄደን የምንጠይቃቸው፤ በር ላይ ያሉት የፀጥታ ኃይሎች ያሸማቅቁናል፣ ይሰድቡናል። በር ላይ ያሉት ሰዎች ለቤተሰቦች ተገቢውን ክብር እየሰጡ አይደለም፤ በስንት ልመና ነው ምግብ እንኳን የምናስገባላቸው። ከትላንት በስቲያ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ፣ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስና የክልሉ ፖሊስ አነጋግረዋቸው ነበር ምርመራ እያደረግን ነው በ14 ቀን ውስጥ ዝርዝር ጉዳዩን እና በምን ምክንያት እንደታሰሩ እናሳውቃችኃለን ብለዋቸው የነበረ ሲሆን ቀኑ መብዛቱን ቅሬታ ያሰሙት የSMN አመራሮቹ ከ14 ቀን በፊት ዝርዝሩ እንዲነገራቸው ጠይቀው ተፈቅዶላቸዋል። ለምን እንደታሰሩ ምን እየተፈፀመ እንዳለ አያውቁም፤ ፖሊስም ካሰራቸው በኃላ ነው መረጃ እያፈላለገ የሚገኘው ይህ ፍፁም ተገቢ አይደለም። ምን አይነት ስራ እየተሰራ እንዳለ አናውቅም፤ ቤተሰብ ብዙ ጊዜ እንዲያገኛቸው አይፈቀድም ነገር ግን ባገኘናቸው ሰዓት የሚነግሩን አያያዛቸው ጥሩ እንዳልሆነ ነው።"

🏷በታሳሪዎቹ ላይ ድብደባ እና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው የሚል ወሬ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ አይቼ ነበር ምን ያህል እውነት ነው ብዬ ለጠየኳቸው ጥያቄ የሰጡኝ ምላሽ፦ "እኔ ይህን እርግጠኛ #አይደለሁም፤ እርግጠኛ የምሆንበትን ነገር ብቻ ደውዬ አሳውቅሃለሁ"

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ...

የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ታሪኩ ለማ ባለፉት ቀናት የሚገኙበት የጤና ሁኔታ ጥሩ እንዳልሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የምክትል ስራ አስኪያጁ የቅርብ ሰው ግልፀዋል። "በተደጋጋሚ ወደተሻለ የህክምና ተቋም እንዲወስድ ጠይቀናል የክልሉ ፕሬዝዳንት አማካሪም ጋር ጉዳዩ ደርሷል እስካሁን በቂ ምላሽ አላገኘንም በዚህም ሳቢያ ተጨንቀናል፤ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግልን" ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia