TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባለ_2_መኝታ🔝

የመከላከያ ሰራዊት አባል ለሆናችሁ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በሙሉ፦

የመከ/ሰራዊት ፋውንዴሽን #የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች እጣ የወጣላቸው እና የቤት እድለኞች ቼክሊስት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባለ_3_መኝታ🔝

የመከላከያ ሰራዊት አባል ለሆናችሁ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በሙሉ፦

የመከ/ሰራዊት ፋውንዴሽን #የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች እጣ የወጣላቸው እና የቤት እድለኞች ቼክሊስት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባለ_4_መኝታ🔝

የመከላከያ ሰራዊት አባል ለሆናችሁ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በሙሉ፦

የመከ/ሰራዊት ፋውንዴሽን #የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች እጣ የወጣላቸው እና የቤት እድለኞች ቼክሊስት!

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking_News Loading...
#ሰበር_ዜና በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በሚገኙ #ሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ልዩ ወረዳዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ #ታውጇል#ETHIOPIA

#State_of_emergency

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ከዛሬ ጀምሮ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተወስኗል። #state_of_emergency #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Breaking

"...በክልሉ ባሉ ሁሉም ዞኖች፤ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ልዩ ወረዳዎች በፌደራል የፀጥታ ኃይል ቁጥጥር ስር ሆኖ በጊዚያዊ ኮማንድ ፖስት እንዲመራ የክልሉ መንግስት በጠየቀው መሰረት የፌደራል ፀጥታ ምክር ቤት ከሐምሌ 15/2011 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ንግድን ለማሳለጥ ከተቋቋመው ኮሚቴ አባላት ጋር እየተወያዩ ነው።
በውይይታቸውም ባለፉት ጥቂት ወራት በሀገሪቱ የተከናወኑ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎችን በመገምገም ላይ መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የሀገሪቱን የቢዝነስ ዘርፍ እንቅስቃሴ ለማሳደግ እየተከናወኑ ባሉ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ግቦች ላይ ሊካሄዱ በሚገባቸው ማሻሻያዎች ዙሪያ እየመከሩ ይገኛሉ።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ እና የአፋር ክልል መንግስታት ለአማራ ክልል መንግስት አጋርነታቸውን ገለጹ፡፡ የክልል መንግስታት ርዕሰ መስተዳድሮች ትላንት ባህር ዳር በነበረው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በዓለ ሲመት ላይ ታድመዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባስተላለፉት የአጋርነት መልዕክት ‹‹ኢትዮጵያውያን የሚያዋጣን ለጋራ አንድነታችንና ለልማታችን በጋራ መትጋት ነው፤ ፈተናወች የጋራ ቤትን የሚያፈርሱ ከሆነ ማንም አይጠቀምበትም፤ የጋራ ቤት የሆነችውን ኢትዮጵያ በአንድነት ልማቷን እና ሰላሟን አስጠብቆ ለማሻገር መትጋት ይገባል›› ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አንድነትና ቀጣይነት የማረጋገጥ ትልቅ ኃላፊነት መወጣት ተገቢ መሆኑንም አቶ ሽመልስ አሳስበዋል፡፡

የጥፋት መንገድ እንዳይደገም፣ ኢትዮጵያን ለዘመናት በአዙሪት ውስጥ ያኖራት በውይይትና በዴሞክራሲያዊ መንግድ ችግሮችን የመፍታት ችግር እንዲያበቃ ሁሉም በጋራ መታገል እንደሚገባውም ነው ያሳሰቡት፡፡ የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ እና መንግስትም ከአማራ ክልል መንግስት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/BDR-07-23-2
#update አሜሪካ ስደተኞችን ፍርድ ቤት ሳታቀርብ ወደመጡበት ሀገር ልትመልስ ነው፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ያለፍርድ ቤት ውሳኔ ስደተኞችን ወደ መጡበት አገር መመለስ የሚያስችል መመሪያ አወጣ፡፡

በአዲሱ ደንብ መሰረት ማንኛውም ማስረጃ የሌለው ስደተኛና በተከታታይ ለሁለት ዓመት አሜሪካ ውስጥ እንደነበር ማረጋገጥ ያልቻለ ግለሰብ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ይደረጋል። ፖሊሲው ዛሬ ይፋ ተደርጎ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች በአፋጣኝ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ተብሏል።

አሜሪካን ሲቪል ሊበርቲስ ዩኒየን የተባለ የመብት ተሟጋች ቡድን ፖሊሲውን በመቃወም ፍርድ ቤት ወስዶ ለመሟገት ማሰቡን ተናግሯል። የአሜሪካ የስደተኞች ፖሊሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥብቅ እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል፡፡

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ደጋማው ክፍል በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የደረሰውን ውድመት ለማካካስ ከ38 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች መተከላቸውን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አበባው አዛናው እንደገለፁት የችግኝ ተከላው በተያዘው ዓመት መጋቢትና ሚያዚያ ወር በፓርኩ ውስጥ በተነሳው የእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመተካት ነው፡፡

ችግኞቹ የተተከሉትም ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ሁለት ሺህ የሚደርሱ ወጣቶችና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላትን በማሳተፍ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በፓርኩ ውስጥ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተተከሉ ያሉ ችግኞች በፍጥነት የሚያድጉና ለአካባቢው ስነ-ምህዳር ተስማሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከ60 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን እስካሁን በተካሄደ እንቅስቃሴ አብዛኛውን ማሳካት እንደተቻለ ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡-ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮምቦልቻ

"እኛ የኢትዮጵያ መንገዶችን ባለስልጣን የኮምቦልቻ መንገድ አውታርና ደህንነት ማኔጅመንት ሰራተኞች በዶ/ር አብይ የተጀመረውን የችግኝ ተከላ ፕሮጀክት ጀምረናል።" ሀይሉወሰን በቀለ ከኮምቦልቻ

@tsegabwolde @tikvahethiopia