TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር...

ቆቦ አካባቢ መንገድ ተዘግቶ #መቆማቸውን መንገደኞች ገልፀዋል። ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቁ የተናገሩት መንገደኞቹ ለረጅም ደቂቃ መቆማቸውን ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመጪው ሀምሌ 22/2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን ለመትከል እቅድ ተይዞ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው፡፡
በእለቱም:-
* በትግራይ ክልል 12 ሚሊዮን
* በአማራ ክልል 108 ሚሊዮን
* በኦሮሚያ ክልል 126 ሚሊዮን እንዲሁም
* በደቡብ ክልል 48 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

@tsegabwolde @tikcahethiopia
#update ሳውዲ በየመን ድሮኖች ላይ ጥቃት መፈፀሟን ገለጸች፡፡ የየመን 3 የስለላ ድሮኖች ጅዛን እና አብሃ በተባሉ የየመን አዋሳኝ ወደ ሳውዲ ከተሞች ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በሳውዲ አየር ሀይል መደምሰሳቸውን ወታደራዊ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

በመንግስት የሚመራው ሳውዲ ፕረስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ቦምብ ተሸካሚ ድሮኖቹ በየመን በሚንቀሳቀሱት የሀውቲ አማፅያን የሚመሩ ቢሆንም ድርጊቱን በዋናነት የምታቀነባብረው ኢራን መሆኗን ነው የገለፀው። ሳውዲ በየመን ላይ በምትወስዳቸው ጥቃቶች የተነሳ ንፁሀን ዜጎች ምን ያህል እየተሰቃዩ መሆኑን አንድ የየመን ሰብዓዊ መብት ቡድን ገልጿል፡፡

ቡድኑ እንዳለው የሳውዲ የአየር ጥቃት ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን ኢላሚ ያደረገ በመሆኑ ብዙ ጥፋቶችን በየመን አስከትለዋል ብሏል፡፡ እስካሁን በተደረጉ የአየር ላይ ጥቃቶች ቢያንስ ወደ 175 ንፁሀን እንዲሁም 165 ህፃናትን ጨምሮ መገደላቸው ተገልጿል፡፡

በአደጋው ከ427 በላይ የቆሰሉ ንፁሀን ሲኖሩ ይህም 172 ህፃናትን ያካትታል ነው ያለው፡፡ ይህም ቁጥር ለ 150 ጊዜ በተደረጉት የአየር ላይ ትቃት ብቻ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
የየመኑ የሰብዓዊ መብት ቡድኑ ይህንን ሪፖርት ያወጣው ከ2 ሺህ በላይ የመናውያንን በማነጋገር መሆኑን የአሜሪካው ዜና አውታር ኤፒ ዘግቧል፡፡

Via AP/ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዓባይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሠራተኞች ከ16 እስከ 25 ሚሊዮን ብር ይሆናል የተባለ ገንዘብ ወደ አዲስ አበባ ይዘው ሲገቡ፣ በቁጥጥር ሥር ውለው መታሰራቸውን ሪፖርተር ዘገበ።

የባንኩ ሠራተኞች ናቸው የተባሉት ግለሰቦች ገንዘቡን ከመሃል ሜዳ፣ ደብረ ብርሃንና በዚያው አካባቢ ካሉ የዓባይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ቢሮዎች ሰብስበው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ እያሉ፣ ወደ አዲስ አበባ መዳረሻ አካባቢ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነግሯል፡፡

ግለሰቦቹ እንዴት? ለምን? በማን ፈቃድ? ገንዘቡን ሰብስበው ይጓዙ እንደነበር፣ እንዲሁም የገንዘቡን ትክክለኛ መጠን እንዲያብራሩ የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ የኋላ ገሠሠን በግል ስልካቸው ሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ሪፖርተር ጋዜጣ አነጋግሯቸው ነበር፡፡

አቶ የኋላ፣ ‹‹ገና እያጣራሁ ነው፡፡ ልጨርስና እንነግራችኋለን፡፡ ነገ ደውሉልኝ፤›› ያሉ ቢሆንም፣ በቀጠረው መሠረት ማክሰኞ ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ቢደውልላቸውም ሆነ አጭር መልዕክት ቢላክላቸውም ምላሽ አልሰጡም፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የባንኩ ሠራተኞችም ሆኑ ገንዘቡ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ እንዳልተለቀቁ የሪፖርተር ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

Via #ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር ፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ሐምሌ 15 ይጀምራል፡፡

ምክር ቤቱ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት የቀረቡትን የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ሹመት እና የ2012 ረቂቅ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

የምክር ቤቱ ስብሰባ ከሐምሌ 15 እስከ 18/ 2011 ዓ.ም ባሉት ቀናት በባሕር ዳር እንደሚካሄድ መርሀ ግብሩ ያሳያል፡፡

ምንጭ ፡- አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዎላይታ ዞን ምክር ቤት ክልል ለመሆን ያሳለፈውን ውሳኔ ደኢሕዴን ለደቡብ ክልል ምክር ቤት እንዳይቀርብ አዘግይቷል ሲል የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ወቀሰ።

ድርጊቱ «ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሐዊ እና ኢ-ሞራላዊ» ነው ያለው ንቅናቄው «የዎላይታ ብሔር ጥያቄ በአስቸኳይ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ ሕዝበ-ውሳኔ እንዲያደራጅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያስተላልፍ» በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/WRS-07-17
የ3.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ...

በህይወት ዘመናቸው አንድ ጊዜ ብቻ ሎተሪ የቆረጡት ጡረተኛ የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ዕድለኛ መሆናቸውን የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ የሱፍ መሐመድ በልዩ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ በሁለት ነጠላ ትኬቶች የ3 ሚሊየን 500 ሺህ ብር ዕድለኛ መሆን ችለዋል።

አቶ የሱፍ ሎተሪ ይደርሳል ብለው እንደማያስቡና “የውሸት ትርክት ነው” ብለው ያምኑ ስለነበር ሎተሪ ቆርጠው እንደማያውቁ ነው የተናገሩት።

ነገር ግን አንድ ቀን ሰፈራቸው አካባቢ ጫማ እያስጠረጉ የሎተሪ አዟሪ መጥቶ ሎተሪ ይግዙኝ ሲላቸው 20 ብር አውጥተው ነበር ልዩ ሎተሪን የቆረጡት።

ይህ በህይወት ዘመናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የቆረጡት ሎተሪ ግን እሳቸው ከሚያምኑት በተቃራኒ ሚሊየነር አድርጓቸዋል። አቶ የሱፍ ጦረተኛ ሲሆኑ የሶስት ልጆች አባት ናቸው፡፡

በደረሳቸው ገንዘብም ምን እንደሚሰሩበት ሲናገሩ “ፈጣሪ የቤት ችግሬን አይቶ ይህን ገንዘብ ስለሰጠኝ ሳልውል ሳላድር ቤት ነው የምገዛበት” በማለት ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ኤዴሌ ኮድር ተፈራርመውታል። ስምምነቱ ዩኒሴፍ በ2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
(ከሲዳማ ዞን መ/ኮ/ፅ/ቤት የተሰጠ ማሳሰቢያ)

የ55ቱ ብሔር ብሔረሰብ መቀመጫ ከተማ አርባ ምንጭ እንዲሆን መደረጉን የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ ገለፁ ተብሎ በጋሞ ሚዲያ ኔት ወርክ የተገለፀው ስህተት መሆኑን የሲዳማ ዞን የሕዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ባለፈው የዴኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን ተከትሎ በተላለፉት ውሳኔዎች መነሻ የተዛቡና በትክክል ከምንጩ ያልሆኑ አሉባልታዎች በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ሲተላለፉ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን እንዲሁም በተሳሳተ ሁኔታ የዴኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሲዳማ ብሔር ውጪ ያሉትን በሙሉ በአርባ ምንጭ ከተማ ማዕከል አድርገው እንዲቀጥሉ ተወስኗል በማለት የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል ተብሎ በመለቀቁ በአንዳንድ ሚዲያዎች ሼር እና ላይክ በማድረግ ኮሜንቶች በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ የሲዳማ ዞን የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ደርሶበታል፡፡

ይህ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ከሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ያልወጣ መረጃ መሆኑንና ምንም ዓይነት ገለፃ ያልሰጡበት ጉዳይ በመሆኑ መቆም አለበት፡፡

በተጨማሪም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ በጋሞ ሚዲያ ኔት ወርክ በኩል የተሳሳተ መረጃ በሶሻል ሚዲያ ላይ የተለቀቀው ስህተት በመሆኑ ለሁሉም ሶሻል ሚዲያ ተከታዮች የማስተካከያ መልዕክት ያስተላልፉ ዘንድ በመጠየቅ ለወደፊቱም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ሳያጣሩ ሼር እና ላይክ እንዳያደርጉ ለሁሉም ሚዲያ ተከታዮች መልእክት ማስተላለፋቸውን የሲዳማ ዞን ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ያሳስባል፡፡

ሲዳማ ዞን መ/ኮ/ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በፅ/ቤታቸው እንዲሁም የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ እና የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ሱካሬ ሹዳ በተከታታይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።

Via #SMN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

በመቐለ ዙርያ ሮማናት ተብሎ የሚታወቅ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ 300 ገደማ ዜጎች መንግስት ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው ቤቶቻች እያፈረሰ ነው ሲሉ ቅሬታቸው አቀረቡ። የጀርመን ራድዮ ያነጋገርናቸው ቅሬታ አቅራቢዎች በትላንትናው ዕለት ብቻ ከ200 በላይ የሚገመቱ ቤቶች "ሕጋዊ አይደሉም" ተብለው ፈርሰዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ከፍተኛ የሀብት ውድመት እንደገጠማቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል፡፡

Via #DW
ፎቶ: ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ታስረው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ታስረው የሚገኙ የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ጠይቀው ሲመለሱ መሆኑን የአብን ሊቀመንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አመራሮቻቸውና አባሎቻቸው የታሰሩት በቀዝቃዛ ቦታ፣ የፀሐይ ብርሃን በማያገኙበትና ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በማይችል ሁኔታ በመሆኑ እንዲሻሻልላቸው ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተው ሲወጡ፣ መውጫ በር ላይ አቶ ክርስቲያንን እንደያዟቸው ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው መርማሪ ፖሊስ በነጋታው ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ፣ ምድብ ወንጀል ችሎት እንዳቀረባቸውም አስረድተዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ለምን አቶ ክርስቲያንን በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸውና እንዳሰራቸው ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፣ ተጠርጣሪው ወጣቶችን መሣሪያ እንደሚያስታጥቁና እንደሚያደራጁ በማስረዳት ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት መጠየቁም ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ክርስቲያንም ወጣቶችን መመልመልና ማደራጀት ሥራቸው መሆኑንና ከእስርም ሲለቀቁ የሚቀጥሉት ሥራቸው እንደሆነ ተናግረው፣ መሣሪያ ያስታጥቃሉ ስለተባለው ግን ፖሊስ ማስረጃ ካለው እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ፣ ለሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ስብሰባውን ረግጦ የወጣ አንድም የማዕከላዊ ኮሜቴ አባል የለም።" #ደኢህዴን #SEPDM

"...በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ስብሰባውን ረግጠው የወጡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አሉ ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆን የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽ/ቤት ኃላፊ ጓድ ሞገስ ባልቻ ገልፀዋል።" #ደኢህዴን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአድዋ ማዕከል ግንባታ ተጀምሯል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር እና የታሪካዊ ድሉን ሁለንተናዊ ይዘት ለትውልድ ለማሻገር ሊገነባ የታሰበው የአድዋ ማዕከል በዛሬው ዕለት ግንባታው ተጀምሯል፡፡

የአድዋ ማዕከል ግንባታ ለረዥም ጊዜያት ሳይለማ በቆየው እና ከሚድሮክ ተመላሽ በተደረገው ቦታ ላይ የሚካሄድ ሲሆን የግንባታው ወጪ ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የዓድዋ ማዕከል ግንባታው ሲጠናቀቅ ከሚሰጠው ማህበራዊና ታሪካዊ ፋይዳ በተጨማሪ በውስጡ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ ፦

✿ የአድዋ ሙዚየም
✿ ከ2000 ሰው በላይ የሚይዝ የዓድዋ አዳራሽ
✿ እያንዳንዳቸው 400 ሰው የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት አዳራሾች
✿ የሲኒማ አዳራሽ
✿ ቤተ-መፅሐፍ
✿ የስፖርት ማዘውተርያዎች እና ጂሞች
✿ የህፃናት መጫወቻ እና የማቆያ ስፍራ
✿ የጌጣጌጥ መደብሮች
✿ የቤተ-ስዕል ማዕከላት
✿ ዘመናዊ የባስ እና የታክሲ ማቆሚያ
✿ ከ600 መቶ መኪና በላይ የመያዝ አቅም ያለው ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ተርሚናል
✿ ካፌዎች እና የምግብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት
✿ ለንባብ አገልግሎት የሚሆኑ የአረንጓዴ ስፍራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

China Jiangsu International E.T.C.C በተባለ አለም አቀፍ ኩባኒያ ግንባታው የሚካሄደው የአድዋ ማዕከል በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት የሚደረግ ይሆናል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ በውስጡ "ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!" የሚል የአዲስ አበባ ከተማ 'ዜሮ(0.00) ኪ.ሜ' ምልክት ያርፍበታል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ዜና

በእሳት ቃጠሎ ጉዳት የደረሰበት የስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሳር ምድር ሙሉ ለሙሉ አገግሟል ተባለ፡፡ የፓርኩን የደን ሽፋን ለማሳደግ 50 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉም ተነግሯል፡፡

Via #ShegerFM
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Joseph Joseph
አፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜውን ጨዋታ
በቴሌግራም ግሩፓችን
ገምተው ይሸለሙDon't forget subscribe our Telegram channel
Join @hopemusics @josehope
#NewsAlert

"ለሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የምርጫ ቦርድን ስራ በትእግስት መጠባበቅ ይገባል'" አቶ ቃሬ ጫዌቻ
.
.
#የክልልነት ጥያቄው በህገ-መንግስቱ መሰረት ምላሽ እንዲያገኝ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስራ በመጀመሩ መላው የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በትዕግስት እንዲጠባበቁ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አስታወቁ።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ቃሬ ጫዊቻ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ዙሪያ ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ እንዲቻል ቅድመ-ዝግጅቱን ጀምሯል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ህዝበ ውሳኔውን ለማድረግ እንዲያስችል በደቡብ ክልልና በሲዳማ ዞን መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በመለየት ማሳወቁንና እስከ ሐምሌ 19 ድረስ ዝርዝሩን በጽሁፍ ማቅረብ እንዲቻል የጊዜ ገደብ መስጠቱን አስታውቀዋል።

የሲዳማ ዞን አስተዳደር ከክልሉ መንግስትና ከደኢህዴን ጋር በመሆን በጥያቄው ዙሪያ በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙና ምርጫ ቦርድ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንደሚደረግ በመግለጹ መላው የሲዳማ ተወላጆችና ወጣቶች ጉዳዩን በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

ቦርዱ በህዝበ ውሳኔ ማደራጀት ዙሪያ ከሲዳማ ዞንና ከክልሉ መንግስት ጋር በተለያዩ ጊዜያት መወያየቱን ያስታወሱት አቶ ቃሬ ህዝበ ውሳኔውን አምስት ወር ባልሞላ ጊዜ አደራጅቶ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert አንድ ታጣቂ፣ በኢራቋ የኩርዶች ከተማ አረቢል ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ በዛሬው ቀን በፈፀመው ጥቃት፣ እስካሁን በተረረጋገጠው መሠረት አንድ የቱርክ ዲፕሎማት መገደሉን፣ መንግሥዊው የቱርኩ ዜና አውታር ዘግቧል።

መንግሥታዊው ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ የቱርክ ምክትል ዋና ቆንስላ የነበረው ዲፕሎማት አረቢል ውስጥ በሚገኘው የቆንስላ ጽ/ቤት በሥራ ገበታው ላይ ነበር። ሌሎች በርካታ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው የተዘገበ ቢሆንም፣ እስካሁን ግን የሞቱትንም ሆነ የቆሰሉትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ማወቅ አልተቻለም።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ ያስመርቃል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ፍሬው ተገኘ ለአብመድ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ሐምሌ 13/2011 ዓ.ም የሚያስመርቀው፡፡

በዕለቱም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፋ ሙሃመድ ዑመር ለተመራቂዎች መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል፡፡ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ ከሀይማት አባቶች፣ ከጎሳ መሪዎች፣ ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ከልዩ ልዩ የኅብረሰተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 100 የልዑክ አባሎቻቸውን ይዘው ወደ ባሕር ዳር እንደሚመጡ ነው የሚጠበቀው፡፡

የልዑኩ አባላትም የባሕር ዳርና አካባቢዋን የመስህብ ሥፍራዎች እንደሚጎበኙና የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥርን የሚያጠናክሩ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቆቦ አካባቢ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ተከፍቷል!

ጉዳዩ እንዲህ ነው: ትናንት አንድ ነዳጅ የሚጭን ቦቴ መኪና ባጃጅ ገጭቶ ወደ ሀረር ያመልጣል። እሱ መኪና ተመልሶ እንዲመጣ ለማስገደድ ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር የሚወስደው መንገድ ላይ ቆቦ አካባቢ (ከጭሮ ትንሽ አለፍ ብሎ) መንገድ ተዘጋ። በዚህ ወቅት የአንዳንድ ቦቴ መኪኖች መስታወት ተሰብሯል። አሁን በምስሉ ላይ የሚታየው ገጭቶ አመለጠ የተባለው ቦቴ ወደ ስፍራው ስለተመለሰ መንገዱ ክፍት ሆኗል።

Via #Elias_Mesert

@tsegabwolde @tikvahethiopia