TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ADDISABEBA የሞተር ብስክሌትና የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ክልከላና የእንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ከትላንት ሐምሌ 1 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

Via #ሸገርራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 2.2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሳሪያ ለታይዋን ለመሸጥ መወሰኑን ፔንታገን አስታውቋል። የሽያጭ ስምምነቱ 108 አብራምስ ታንኮች፣ 250 ስቲንገር ሚሳኤሎችና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ያካትታል ነው የተባለው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ፦ https://telegra.ph/AMA-07-09
#update በውጭ ሀገር የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡ የዕውቅና ሽልማቱ የተበረከተላቸው ለመገናኛ ብዙኃንና ለኪነ ጥበብ ነፃነት መከበር ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ታውቋል፡፡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹የሚገባቸውን ጥቂቶች በማበረታታት ብዙዎችን ማትጋት ይቻላል›› ብለዋል፡፡ የዕውቅና ሽልማቱ የተሰጠውም አምባሳደር ፍጹም በተገኙበት እንደሆነ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በመተከል ዞን #ማንዱራ ወረዳ ሰሞኑን ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ 14 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ፡፡

በቤኒሻንጉ ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ሰሞኑን ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ገልጿል፡፡

በማንዱራ ወረዳ ገነተ ማሪያም ቀበሌ ተከስቶ የነበረው ግጭት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡ ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ በግድያና በማስተባበር ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 14 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ባየታ ተናግረዋል፡፡

የጸጥታ ኃይሉ እያደረገ ባለው ክትትል ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በርካታ ቀስቶች እና አንድ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል፡፡

የአከባቢውን የፀጥታ ችግር ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ የክልሉ የፀጥታ ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ ከአመራሩ ጋር በጋራ እየሰሩ ሲሆን ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም የአካባቢውን ሠላም ለመመለስ ተባባሪ እንዲሆን አቶ አበራ ጠይቀዋል፡፡

የአካባቢውን ሠላም አስተማማኝ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ግጭቱን በማባባስ እና በማስተባበር የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በፀጥታ ስጋት ምክንያት ተስተጓጉሎ የነበረው የአከባቢው የፀጥታ ችግር ወደመረጋጋት እየተመለሰ ሲሆን መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት አለመቋረጠሩንም ከመተከል ዞን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvagethiopia
#ጎንደር #Gondar

"ትላንት እና ከትላንት በፊት የጎንደር ውሎ ይህን ይመስል ነበር። ዛሬ ግን ጎንደር ሰላም ነው። እስከ 4 ሰኣት አካባቢ ሱቅ አልተከፈተም ነበር አሁን ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ጎንደር ሰላም ናት።" #Abrsh ከጎንደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በጎንደር ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሷል"

ዛሬ ይህን መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ተመልክተን ጎንደር የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትን ጠይቀናቸው "ነጭ ውሸት" ነው ወጣቱ ከመከላከያ ጋር አልተጋጨም፤ ህዝባዊ ተቃውሞ የሚያስብል አይደለም ብለውናል። ህዝቡም ከእንዲህ ያሉ #ግጭትን ከሚቀሰቅሱ እና ከሚያባብሱ #ሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲያርቅም መክረዋል።

•Ethiopian Dj ~ የፌስቡክ ገፅ
•የተከታዮቹ ብዛት:1,928,218

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጎንደር #Gondar

2.8 ሚሊዮን የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት "Mereja.com" የተባለ ገፅ በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ #ወጣቱ ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ጋር ችግር ውስጥ እንደገባ ዘግቦ ከ1 ሰዓት በኃላ መረጃውን ከገፁ ላይ አጥፍቶታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ስያሜያቸው "ብሄር ተኮር" የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ፌዴሬሽኑ የእግር ኳስ ሜዳዎች ውስጥ ጠብ የማይቆም ከሆነ ጨዋታዎች ካለ ተመልካች እንዲካሄዱ የሚያደርግ ርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አክሎ ገልጿል፡፡

Via VOA Amharic
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጌዲዮና በምዕራብ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው የነበሩና ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል ለአራት ዓመት የሚቆይ መርሃ ግብር ይፋ ተደረገ። መርሃ ግብሩን የተባበሩት የመንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የሚመራው ሲሆን፥ 20 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያስፍልግ መሆኑም የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

Via #fbc
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ #አስቸኳይ ስብሰባ ማድረግ ጀምሯል፡፡ #ደኢሕዴንም ስብሰባ እያካሄደ ነው፤/የደኢህዴን ስብሰባ ለ3 ቀናት ተብሎ ነበር የተጀመረው ስብሰባው ዛሬም #እንደቀጠለ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር አሚን አማን ጋር በመሆን የጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የእድሳት በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ላለፉት በርካታ ዓመታት የውስጥም ሆነ የውጪ እድሳት ሳይደረግለት ቆይቷል፡፡

Via @mayorofficeAA
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NewsAlert በሲዳማ ዞን የሚንቀሳቀሱ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት የቀረበውን የህዝበ ውሳኔ ቀን በአስቸኳይ ይፋ እንዲደረግ ጠየቁ። ጥያቄውን ያቀረቡት የሲዳማ አርነት ንቅናቄ «ሲአን»፣ የሲዳማ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ «ሲብዴ ፓ» እና የሲዳማ ሀድቾ ዴሞክራሲያዊ ደርጅት« ሲሀዴ ድ» ናቸው ።

Via #DW
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ 249 የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ። የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጉተን ሌሊሳ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት76 ሽጉጦች፣ 138 ጠብመንጃዎችና 35 ጩቤዎች የተያዙት ሰሞኑን በመኖሪያ ቤትና በኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ ነው። ከዚህም በተጨማሪ 90 የሺሻ እቃዎች መያዛቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኮማንደር ጉተን እንዳሉት መሳሪያዎቹ ሊያዙ የቻሉት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ ክትትል ነው። ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር ኮማንደሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Via #ኢዜአ
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews የአማራ ክልል ልዩ ኃይል #ሊፈርስ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ/በተለይም በfacebook/ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews ሌተናል ጄነራል #ሃሰን_ኢብራሂም ታሰሩ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጎንደር #Gondar

ጎንደር ከተማ #ሰላማዊ መሆንዋን ምክትል ከንቲባ በሪሁን ካሣዉ ገልፀዋል። ትላንት አነስተኛ ውዝግብ ከተማ ውስጥ መፈጠሩን ያነሱት ምክትል ከንቲባው የነበረውን አነስተኛ ዉዝግብ ተጠቅመዉ ረብሻ ለማስነሳት የሞከሩ እና አንዳንድ ያልተገባ ነገር ለመፈፀም የሞከሩ፤ ድርጊታቸዉን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል፤ #ከጀርባቸዉ ማን እንዳለም እያጣራን ነዉ ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

Via #DW
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትላንትናው ዕለት በጎንደር ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር አንዳንድ የንግድ ተቋማት ላይ #ጉዳት መድረሱን፤ የደረሰውን የጉዳት መጠንም የማጣራት ስራ መጀመሩን #የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ኮማንደር ማረልኝ ወንድሙ ተናግረዋል። በጥፋቱ የተሳተፉ ግለሰቦችም በቀጣይ የማጣራት ስራ ከተከናወነ በኋላ በህግ #ተጠያቂ እንደሚደረጉም ገልፀዋል።

🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ ለባለሀብቶች ሊሰጥ ነው፡፡ ከሆንግ ኮንግ የመጡ የባለሀብቶች ቡድን አባላት የኢንዱስትሪ ፓርኩን #ነገ እንደሚረከቡ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሃምሌ 2/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአገር አቀፍ ደረጃ ተከስቶ የነበረው የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ #እየቀነሰ ቢሆንም ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል።

ተጨማሪ ያብቡ👇
https://telegra.ph/CH-07-09