TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ምርጫ ቦርድ በመጭው ሰኞ ለጋዜጠኞች መግለጫ እሰጣለሁ ብሏል፡፡ መገናኛ ብዙሃንም ተገኝተው እንዲዘግቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ መግለጫው በቦርዱ አዲስ አወቃቀር፣ በአዳዲስ ቦርድ አባላት አሰያየም፣ በምርጫ በጀት፣ በሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ጥያቄና የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘምና ተፈናቃዮች በምርጫው ላይ ስለሚፈጥሩት ተጽዕኖ በሚሉት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል- ይላል የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ፡፡

Via #አዲስ_ስታንዳርድ/wazema/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ ኤሊያስ የታሰረው ቅዳሜ ማታ እንደሆነ ነው የተሰማው፤ ከታሳሪው ጋር ባለፉት 2 ቀናት የተያዙ 14 ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ ዛሬ ጧት ፍርድ ቤት ባቀረባቸው ጊዜ #በሽብር ወንጀል እንደሚከሳቸው መግለጡን አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡ ችሎቱ ለሐምሌ 29 ቀጥሯል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ከባለ ሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ ነው፡፡

Via #አዲስ_ስታንዳርድ/#wazema/
🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia