TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ከእስር ተፈቱ። አቶ ክርስቲያን ትናንት በምዕራብ ጎጃም ሰከላ ወረዳ ከስምንት የአብን አባሎች ጋር ነበር የታስሩት።

Via #BBC
🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምርጫው ይራዘም...

ኢህአፓ መጪው ምርጫ መራዘም እንደሚገባው ገለፀ። በአገሪቱ አሁን ባለው የጸጥታ ስጋትና ጫፍ የረገጠ ብሔርተኝነት ምክንያት የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መጪው ምርጫ መራዘም አለበት የሚል አቋም እንዳለው ኢህአፓ ገልጿል።

የኢህአፓ ከፍተኛ አመራርና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ቆንጅት ብርሃን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በአገሪቱ ብሔርተኝነትና ዘረኝነት ጫፍ የረገጠበት ደረጃ ደርሷል።

ወይዘሮ ቆንጂት አሁን ባለው የጸጥታ ሁኔታ ምርጫ ቅስቀሳ ማካሄድ አዳጋች በመሆኑ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ፓርቲያቸው ምርጫውን በአግባቡ ማካሄድ ይቻላል ብሎ አያምንም ብለዋል።

Via #EPA
🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስክሬናቸው ነገ አ/አ ይገባል...

የጀኔራል አብርሃ ወ/ማርያም (ኳርተር) አስክሬን ከታይላንድ ባንኮክ በመነሳት ነገ ዕሁድ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባል። በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም በመከላከያ ሰራዊት አባላትና በከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት አቀባበል ይደረግለታል ተብሏል።

Via #PetrosAshebafi
🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የብ/ጄ አሳምነው ድምፅ...

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ በአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ሊያረጋግጥ ይችላል የተባለ የድምፅ ቅጂ ይፋ ሆነ። የድምፅ ቅጂውን ይፋ ያደረጉት የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ሰጥየ ናቸው። አቶ ሙሉቀን ሰጥየ ጥቃቱ በተፈጸመበት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጋር ቢያንስ ሶስት ጊዜ በስልክ መነጋገራቸውን ገልጸዋል። 

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው እንደሆነ በተነገረለት የመልዕክት ልውውጥ ክልሉን በሚያስተዳድረው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን ሲናገሩ ይደመጣል። በቴሌቭዝን ጣቢያው በተላለፈው ድምፅ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው መሆናቸው የተገለጸው ሰው «በአዴፓ አመራሮች ላይ የሕዝቡ ሰላማዊ እና የመኖር መብቱ ጥያቄ ውስጥ ስለገባ፤ የሕዝብን ጥያቄ ለማንሳት በመቸገራቸው፤ የሕዝቡን ጥያቄ በመቀልበሳቸው በድርጅቱ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል። እንዳትደነግጥ» ሲሉ ይደመጣል። አቶ ሙሉቀን ግን በወቅቱ በመደናገጣቸው ምክንያት «እርምጃ የተወሰደው እነ ማን ላይ ነው?» ብለው አለመጠየቃቸውን ለአማራ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ተናግረዋል። በመልእክት ልውውጡ «ሁሉም ከጸጥታ ቢሮ የሚሰጠውን መመሪያ እንዲጠብቅ» ትዕዛዝ ሲተላለፍ ይደመጣል።

በዚሁ የድምፅ ቅጂ «እዚህ አካባቢ ማኅበረሰቡ ወደ ቤቱ እንዲገባ፤ የአካባቢው የጸጥታ ኃይል እና ሚሊሻ ደግሞ ራሱን እንዲቆጣጠር» የሚል ትዕዛዝ ጭምር ይገኝበታል። የአማራ ክልል እና የፌድራል መንግሥት ባለሥልጣናት ተሞክሮ ከሽፏል በተባለው መፈንቅለ-መንግሥት የጥቃት ዒላማ ከነበሩ ተቋማት መካከል የአማራ  ብዙኃን  መገናኛ ድርጅት እንደሚገኝበት በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እንደገለጹት፥ ከሰሞኑ በተፈጸመው ድርጊት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎችን የክልሉ የጸጥታ ኃይል ለህግ እያቀረበ ነው።

ድርጊቱ ከተፈጸመበት ቀን እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስም ከ300 በላይ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽነር አበረ ገልጸዋል። ግለሰቦችን ወደ ህግ ለማቅረብ በተደረገው እንቅስቃሴም ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ።

የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱንና ማጣራቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፥ ከተያዙት መካከል ጉዳያቸው ተጣርቶ የሚለቀቁ እንደሚኖሩም አመላክተዋል።

በነባሮች እና አዲስ በሰለጠኑት የልዩ ኃይል አባላት መካከል ልዩነት እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ክልሉ ጠንካራ የጸጥታ ኃይል እንዳይኖረው የተሰራ የፖለቲካ ሴራ እንጂ ምንም አይነት ልዩነት እንደሌለም ነው የተናገሩት።

ህጋዊ ትጥቅ ያላቸውን ግለሰቦች ትጥቅ የማስፈታት ስራ ተጀምሯል እየተባለ የሚሰራጨው ወሬ የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ ታስቦ የሚናፈስና ከእውነት የራቀ አሉባልታ መሆኑንም ኮሚሽነር አበረ ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ ስጋት ውስጥ እንዳይገባም መልዕክት ያስተላለፉት ኮሚሽነሩ ፥ ክልሉ ሙሉ በሙሉ #በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

Via #EPA
🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#warning #fakenews

ህጋዊ ትጥቅ ያላቸውን ግለሰቦች ትጥቅ የማስፈታት ስራ ተጀምሯል እየተባለ የሚሰራጨው ወሬ የክልሉን #ሰላም ለማደፍረስ ታስቦ የሚናፈስና ከእውነት የራቀ አሉባልታ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ገልፀዋል።

🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራል መንግስት በባህርዳር እና በአዲስ አበባ በተፈፀመው የግድያ ወንጀል እጃቸው አለበት ያላቸወን ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የሚደነቅ መሆኑን የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። ዶክተር ደብረጺዮን በትናንትናው እለት በሰጡት መግለጫ፥ መንግስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እያደረገ ላለው ጥረት የትግራይ ክልል ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

Via #fbc
🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተዛውሯል...

በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስታዲዬም ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በፀጥታ ስጋት ለሌላ ግዜ ተዛውሯል።

🗞ቀን 22/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌስቡክ አስተያየት ሰጪዎች እነማን ናቸው

#አብዛኞቹ በተለያዩ #የፌስቡክ_ፖስቶች ላይ/በዜና ማሰራጫዎች፣ በታዋቂ ግለሰቦች ገፅ፣ በአክቲቪስቶች እንዲሁም በሌሎች.../ የስድብ ናዳ የሚያወርዱት፤ ህዝብን የሚያሸብሩት፤ ሀገሪቱ ፍፁም እልቂት ውስጥ ልትገባ እንደሆነ የሚዝቱት፤ እርስ በእርስ ፍጅት እንዲነሳ የሚቀሰቅሱት፤ በተላለፉ መረጃዎች ላይ በሙሉ ስድብ እና ጥላቻን፣ አሉባልታን የሚፅፉት አብዛኞቹ #ሀሰተኛ ገፅ ናቸው። የሰዎቹ ማንነት የማይታወቅ፣ ምስላቸው የሌለ፣ ለግጭት እንዲሁም ህዝብን ለማወናበድ የተከፈቱ ናቸውና ተጠንቀቁ። በምታነቡት አስተያየትም ተስፋ አትቁረጡ።

በሌላ በኩል...

ትክክለኛ አመለካከታቸውን #በስድብ እና በኃይል ለመግለፅ የሚሞክሩም እንዳሉ ልታውቁ ይገባል። ማስረጃን አቅርቦ ከመከራከር ይልቅ ስድብ ባህል ያደረጉ ወገኖች አሉና ከቻልን ቀርበን እናስተካክላቸው።

ኢትዮጵያ ሰላም ትሁን፤
ዜጎቿም ሰላም ወጥተው ይግቡ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አላችሁ!

የተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን በዛሬው እለት #አስመርቀዋል። በዛሬው እለት ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ፣ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል።

TIKVAH-ETH ለተመራቂዎች እና ለቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ ለማለት ይወዳል!!

ፎቶ #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የመንግሥትን የ2011 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያቀረቡ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦች እና ቡድኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት 48 የሽብር ቡድን አባላት፣ 799 ብሔርን መሠረት ባደረገ ጥቃት የተጠረጠሩ መሪዎችና የፀጥታ አካላት፣ በኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች የተጠረጠሩ 34፣ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር 64 ግለሰቦች፣ እና 51 ሰዎች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝቅቅር በሕግ ጥላ ሥር ውለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን በሪፖርታቸው ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች እንደተፈናቀሉም ተናግረዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 400 ሺህ የሚሆኑት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተፈጠረ ድርቅና የተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል፡፡

በሀገሪቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች በሚኖሩበት ክልል ውስጥ የተፈናቀሉ ሲሆን 800 ሺህ ዜጎች ደግሞ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል የተፈናቀሉ መሆናቸውን በሪፖርቱ አመላክተዋል፡፡

አሁን ላይ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን የሚበልጡት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱና ቀሪዎቹን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የ2019 የዩኔስኮ ፌሊክስ ሁፉዌ ብዋኚ (Félix Houphouët-Boigny) የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለይ በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ላይ በነበራቸው ከፍተኛ ሚና ለሽልማቱ የታጩ መሆናቸውንም ዩኔስኮ አሳውቋል።

መቀመጫውን ፈረንሳይ ፓሪ ያደረገው የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም ዩኔስኮ አስቀድሞ ሽልማቱን ለመስጠት የፊታችን ጁላይ 9 ቀን መርሐ ግብር ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ተቋሙ የሽልማቱን መስጫ ቀን ላልተወሰነ ቀን ማራዘሙን አሳውቋል። https://en.unesco.org/news/ceremony-award-felix-houphouet-boigny-unesco-peace-prize-ethiopian-pm-abiy-ahmed-ali

Via #PetrosAshenafi
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰሜን አሜሪካ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል በአትላንታ ተጀምሯል፡፡ ለ36ተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባላሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍፁም አረጋ ተገኝተው ፌስቲቫሉን በይፋ ከፍተዋል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአማራ ክልል ለሦስት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ተሰጥቷል፤ በዚህም መሠረት፡-

•አቶ አገኘሁ ተሻገር----የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ፣

•አቶ አረጋ ከበደ----የክልሉ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣

•ኮሎኔል ጌታቸው ብርሌ----የክልሉ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና በምሥራቅ አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ስኬታማውና በኢትዮጵያ ገበያም ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳየው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ቦብ ኮሊሞር ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ድርጅታቸው አስታደቀ። ሳፋሪኮም የዋና ሥራ አስፈጻሚውን ዜና እረፍት ይፋ ባደረገበት መግለጫው ላይ እንዳመለከተው፤ ቦብ ኮሊሞር በ61 ዓመት እድሜያቸው በካንሰር ምክንያት ዛሬ ጠዋት ቤታቸው ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሰሜን ኮሪያ በማቅናት ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ተገናኝተዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሰሜን ኮሪያ ያቀኑ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ናቸው።

🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ኮሎኔል #ጌታቸው_ብርሌ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ፦ ኮሎኔሉ ከብርጋዴየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ እና ከብርጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ ጋር 9 ዓመት በእስር አሳልፈዋል። #Ethiopia #Amhara

Via #TesfalemWoldeyes
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: አዲሱ የአማራ ክልል ሚሊሺያ ጽህፈት ኃላፊ አቶ #አረጋ_ከበደ። አቶ አረጋ የክልሉ የወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል። #Ethiopia #Amhara

Via #TesfalemWoldeyes
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: አቶ አገኘሁ ተሻገር----የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ! #ETHIOPIA #AMHARA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነአቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ ላይ ቀሪ አንድ የዐቃቢ ሕግ የምስክር ቃል ለመስማት ዛሬ የተሰየመው ችሎት ምስክሩ ባለመቅረባቸው ድጋሜ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

በክስ መዝገብ ተራ ቁጥር አንድ ላይ የቀሪ አንድ ምስክር ቃል ለመስማት ለዛሬ ቀጠሮ የተሰጠ ቢሆንም ምስክሩ በተለያዩ ችግሮች ምክያት ሊቀርቡ ስላልቻሉ ለሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

በዚሁ የክስ መዝገብ ሦስተኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ከጤና ችግር ጋር በተያያዘ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን ጥያቄም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia