TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Alert‼️

በባህር ዳር ከተማ ተደጋጋሚ የመሳሪያ ተኩስ ድምፅ እየተሰማ እንደሆነ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። ድምፁ የሚሰማው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ አካባቢ እንደሆነ ነው የተጠቆመው። ጉዳዩ ምን እንደሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባህር ዳር...

"ፀግሽ ባህርዳር የርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ አካባባቢ ከፍተኛ #ተኩስ እየተሰማ ነው። መንገዱም ተዘግቷል። Becky ከባህርዳር"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር
/ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

"አሁን በባህር ዳር የሚገኝ ጋዜጠኛ በስልክ እንደነገረኝ "እየተከሰተ ያለው ነገር የከፋ ሳይሆን አይቀርም። ሰዎች በጥይት ተመተዋል እየተባለ ነው። ሁሉም በድንጋጤ ወደየቤቱ ለመግባት እየተሯሯጠ ነው"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሰበር_ዜና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገ። #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር

በፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት፣ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፈለገ ህይዎት ሆስፒታል አካባቢ የተኩስ ልውውጡ አሁንም እንዳለ ተሰምቷል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና #ባህር_ዳር

አካባቢያችሁን በንቃት ጠብቁ ተብሏል...

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን የጠቅላይ ሚንስትር ፕሬስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ፡፡ በክልሉ ዛሬ በተደራጀ ሁኔታ በመንግስት መዋቅር ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መሞከሩን አቶ ንጉሱ ገልፀዋል፡፡

በክልሉ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ የመሪ ድርጅቱ አዴፓ እና የአማራ ክልል ህዝብ ያገኘውን ነፃነትና ሰላም ለመንጠቅ እንዲሁም በህዝቡና በመንግስት ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተደራጀ እንቅስቃሴ መደረጉንም ነው አቶ ንጉሱ የገለፁት፡፡

የተደረገውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የፌደራል መንግስት የፀጥታ መዋቅር ክልሉን በተለይም ባህርዳር ከተማና አካባቢውን በቁጥጥር ስር አውሎ በተግባሩ የተሳተፉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ትእዛዝ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡ ህብረተሰቡም አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪም ቀርቧል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር

አልፎ አልፎ ከሚሰማ ተኩስ ውጭ፣ የተኩስ ልውውጡ ቆሟል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና #ባህር_ዳር

በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት #መክሸፉን አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል። ይህንን ድርጊት በፈፀሙት ላይ #እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ተሰጥቷል፤ እንቅስቃሴም ተጀምሯል ሲሉ ገልፀዋል።

Via #etv/#Elias_Meseret/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ #ባህር_ዳር

"ባህርዳር መንገዶች ተዘግተዋል። አሁንም የተኩስ ድምፅ ይሰማል። ሰላማዊ ሰዎች በዚህ የተኩስ ልውውጥ የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆኑ መደወል የምትችሉ ሰዎች ደውላችሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አድርጉ። ይህንን መልዕክት የደረሳችሁ ባህር ዳር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እላለሁ። ሰላም ለባህር ዳር!"

Via Seyum Argaw
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ላይ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚፃረር፣ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ለረጅም ጊዜ የታገሉለትን ሰላምና መረጋጋት ለመንጠቅ የተደራጀ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት ሙሉ በሙሉ እንደሚያወግዘው የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የፌደራል መንግሥት የጸጥታ መዋቅር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር አውሎ በፈጸሙት አካላት ላይ ተገቢውን ርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ተቀብሎ ተፈጻሚ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ጥቃት በመንግሥት መዋቅር ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ሕዝብ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅና ተረጋግቶ ሁኔታዎችን እንዲመለከት ጥሪ ቀርቧል።

ይህን ሕገ ወጥ ሙከራ ክልሉ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ክልልና መላው ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘው የሚገባ ሲሆን የፌደራል መንግሥት የታጠቁ ቡድኖችን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ የመቀልበስ፣ የመግታትና በቁጥጥር ሥር የማዋል ሙሉ ዐቅም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

"አሁን ላይ ባህር ዳር ተኩሱ ቆሟል። መረጋጋት እየተፈጠረ ነው። የአማራ ልዩ ኃይል ሁኔታውን እያረጋጋ እንደሆነ ታውቋል።" #በላይ_ማናዬ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል መንግስት ላይ ተሰነዘረ ያሉትን "መፈንቅለ መንግስት" አወገዙ። አሜሪካን ሀገር የሚገኙት የአዴፓ ሊቀመንበር "የፌደራል መንግስት ጉዳዩን በመከታተል አስፈላጊው #እርምጃ ይወስዳል" ብለዋል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው የአማራን ህዝብና ክልል የማይመጥን አሳፋሪና አሳዛኝ ክስተት ነው" :- አቶ ደመቀ መኮንን
----------------------------------------------------------------------
ዛሬ በአማራ ክልላዊ መንግስት የተቃጣው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና ጥቃት የአማራን ህዝብና ታሪክ የማይመጥን አሳፋሪና አሳዛኝ ክስተት እንደሆነ የኢፌዲሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ። አቶ ደመቀ ከአሜሪካ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩን የፌደራልና የክልል አካላት በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን ተጠያቂ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ይደረጋል ብለዋል። ህብረተሰቡም ውዥንብር ውስጥ ሳይገባ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አቶ ደመቀ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

Via #etv
Pic #elias_meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_መረጃ

በነገው ዕለት #በአዲስ_አበባ ከተማ ሊካሄዱ የነበሩት የጠዋቱ የኦሎምፒክ ሳምንት የመክፈቻ ፕሮግራም እና የከሰዓቱ የስጦታ-ለአዲስአበባዬ ፕሮግራሞች ሙሉ በሙሉ #ተሰርዘዋል

Via Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የፌደራል የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ በተደረገባት የባሕር ዳር ከተማ ተሰማሩ። የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት #መኮድ ተብሎ ከሚጠራው የጦር ሰፈር ወደ ከተማዋ የዘለቁ ወታደሮች የጸጥታ ቁጥጥር እያደረጉ ናቸው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ዜናዎች ከየቦታው እየወጡ ነው። አጣርተን፣ ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች ተቀብለን ትክክለኛውን ብቻ የምናቀርብ ይሆናል። ብዙ ዜናዎች እያጣራን ነው እውነት ሆኖ የተገኘውን ብቻ እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንዴት ከረማችሁ??

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከባለፈው ቅዳሜ አመሻሹን አንስቶ ሃዘን ፀንቶባት ቆይታለች። የሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ የሀዘን ቀናት ተውጆ ነበር። ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮም የኢንተርኔት አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ ተቋርጦ ቆይቷል። የWiFi እና #Broadband አገልግሎት ቢጀመርም የሞባይል ዳታ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በቤተ ጊዎርጊስ የቀብር ቦታ ተፈጽሟል።

🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባለፈው ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በአማራ ክልል መንግሥት ላይ በተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሕይወታቸው ያለፉ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ሥርዓተ ቀብር ትላንት በባሕር ዳር ተፈፅሟል።

በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ የቀብር ሥነ-ስርዓት ትላንት በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ገብርኤል ተከናውኗል፡፡

የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ከመከናወኑ በፊት ደግሞ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዮም የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና የሜጄር ጄኔራል ገዛኢ አበራ የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።

የቀብር ስነ ስርዓቱ በመቐለ ከተማ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ነው የተፈጸመው።

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጀኔራል ገዛኢ አበራ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሰዋታቸው ይታወሳል።

🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia