#update ጦላይ ማሰልጠኛ ጣቢያ ሥልጠና ላይ ያሉ ከ150 በላይ የኦነግ የቀድሞ ታጣቂዎች መመረዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ችግሩ የተከሰተው ትናንት በቁርስ ሰዓት በሚጠጡት ሻይ ነው፡፡ 129ኙ ትናንቱን ለሕክምና ወሊሶ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን 20ዎቹ ደሞ ዛሬ እንደገቡ የሆስፒታሉን ሐኪም ተናግረዋል፡፡ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት እንደታየባቸውም ተገልጧል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ዛሬ ከቀትር በኋላ ባወጣው መግለጫ ሁሉም ታማሚዎች በጥሩ ጤንነት ሁኔታ እንደሚገኙ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡ የህመማቸው መንስዔ እየተጣራ ቢሆንም የምግብ መመረዝ እንደሆነ የተወራው ግን #የተሳሳተ መረጃ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡
በተያያዘ ዜና ...
ዛሬ ማለዳ የወሊሶ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ የአድማው መንስዔ ጦላይ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሉ የኦነግ የቀድሞ ታጣቂዎች ተመርዘዋል የሚል ዜና መሰራጨቱ ነው፡፡ በአድማው ሳቢያ ከወሊሶ-አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ-ወሊሶ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ ወጣቶች መንገዱንም ዘግተዋል፡፡ በከተማዋ የመንግሥት ተቋማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም አገልግሎታቸውን አቋርጠዋል፡፡
Via #BBC(#WAZEMA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ዐለም ዐቀፉ ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ለጌዲዖ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ሰብዓዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ ድርጅቱ ባሰራጨው መግለጫ ሌሎች ነፍስ አድን ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቋል፡፡ ባለፈው መጋቢት በጌዲዖ ተፈናቃዮች ባደረገው ጥናት ከ5 ዐመት በታች ያሉ ሕጻናትና ነፍሰ ጦሮች የገጠማቸው ከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አስቸኳይ የሚባለውን ወለል ያለፈ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ አሁን ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የተመጣጠነ ምግብ እያቀረበ መሆኑን ገልጧል፡፡ ለ200 ከ5 ዐመት በታች ሕጻናትም ሕክምናና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቧል፡፡ በቀጣይ በስደተኛ መጠለያዎች የንጽህና ንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ ይሰራል፡፡
Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግስት ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ያደርግ የነበረውን የግብር ቅናሽ አቆመ‼️
.
.
መንግስት ያገለጉሉ መኪናዎች ከውጭ ሲገቡ ያደርግ የነበረውን #የቀረጥ_ስሌት ቅናሽ ከትላንት ጀምሮ አቆመ።
መንግስት ከዚህ ቀደም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ላለማበረታታት እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል በተባለ የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ መመሪያም ያገለገሉ መኪናዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ ለመኪናዎቹ ቀረጥ ሲከፈል ፣ ከተሽከርካሪዎቹ ዋና ዋጋ ላይ የአገልግሎት ዋጋ ተብሎ እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ የይደረግ የነበረውን የቀረጥ ስሌት እንዲተው አድርጓል።
በዚህም መሰረት ከአሁን በሁዋላ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሀገር ውስጥ ሲገቡ የሚከፍሉት ቀረጥ የሚሰላው ከዋና ዋጋቸው ላይ መኪናው ላገለገለበት እስከ 30 በመቶ ተቀንሶ ሳይሆን በዋና ዋጋቸው ይሆናል ማለት ነው። ይህም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡበት የነበረውን ማበረታቻ በእጅጉ ይጎዳዋል። የሀገር ውስጥ የመኪና ዋጋም ላይ ከፍተኛ ጭማሬን ሊያስከትል እንደሚችል ይጠበቃል።
መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን አዘው መመሪያው እስኪወጣ ያልገባላቸው አስመጪዎች በምን እንደሚታዩ ገና ግልጽ አልሆነም። መንግስት ይህን የታክስ አሰራር በማስቀረት ለነዳጅ ግዥ የሚያወጣውን ምንዛሬ ለመቀነስ እንዳሰበም ይነገራል።