TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ👆በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የአብሮነትና የምስጋና የአፍጥር ምሽት ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሚሊኒየም አዳራሽ የአብሮነትና የምስጋና የአፍጥር ምሽት እየተካሄደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው
/በኤልያስ መሰረት/

"ጋዜጠኛችን በሁለት ዙር ድብደባ ተፈጽሞበታል። እንደሰማሁት ደብዳቢ ፖሊሶቹ 'እስክንድር ይመጣል ብለን ነበር' እያሉ እኔን ሲጠባበቁ ነበር"--- #እስክንድር_ነጋ

"በተባለው ግለሰብ ላይ ምንም ድብደባ አልተፈፀመም። የጋዜጠኛ መታወቂያ እና ደብዳቤ ሳይዝ በድብቅ ካሜራ ሲቀርፅ ተይዞ መጣራት እያረግን ነው"--- የአራዳ ፖሊስ ባልደረባ ኮማንደር የኔወርቅ

እስክንድር እንደሚለው "ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ኢትዮጲስ ጋዜጣን 'ጉዳያችንን ዘግቡልን' ባሉት መሰረት ጋዜጠኛ ምስጋናው ጌታቸው በድብቅ የሚቀርፅ ሪኮርደር ይዞ ዛሬ ወደ ስፍራው አመራ። መነፅር ላይ ያለው ይህ ድብቅ ካሜራን ለመጠቀም የፈለግነው ፖሊሶች ተደራጅተው እንደሚጠብቁን ስላወቅን ነው። ጋዜጠኛው ስፍራው ላይ እንደደረሰ ካሜራውን ተቀብለው ደበደቡት። እንደገና በሁለተኛ ዙር ከ45 ደቂቃ በሁዋላ ድብደባ አደረሱበት። ከዛም 4 ኪሎ ብርሀን እና ሰላም አካባቢ ወዳለ ፖሊስ ጣብያ ወስደውታል። ፖሊስ አሁን እያለ ያለው ጋዜጠኛው ቃሉን ከሰጠ በሁዋላ አቃቤ ህግ ይወስናል ነው። ድብደባ ሲፈፀምበት ምስክር አለ ብንላቸውም ክስ መመስረት አትችሉም ተብለናል።"

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ኮማንደር የኔወርቅ ደሞ "ጋዜጠኛ ለመሆኑ መታወቂያ ይዟል እንዴ?" ብለው እኔኑ ጠይቀውኝ ከዛ እንዲህ ብለዋል። "የተደበደበ የለም። ፍቃድም መታወቂያም አልነበረውም። እኛ ገና ጋዜጠኛ መሆኑን እያጣራን ነው። ተደብቆ ሲቀርፅ የእኛ ፖሊሶች ይዘውታል። ፈቃድ የሌለው ሰው በድብቅ ሰው መቅረፅ አይችልም። ግን ጫፉን የነካው ሰው የለም።"

እስክንድር አክሎም "የጋዜጠኝነት ስራ ለመስራት ልዩ ፈቃድ አያስፈልገውም። አስፈላጊነት መስዋትነት እንከፍላለን እንጂ ሁሌ ደብዳቤ እያፃፍን ስራ አንሰራም" ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የለገጣፎ ተፈናቃዮች አቤቱታቸውን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ ማቅረባቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ 183 ያህሉ ተፈናቃዮች ያቀረቡት አቤቱታ ኦሮሚያ ክልል የሊዝ አዋጁን መሠረት አድርጎ ያወጣቸው ደንቦችና መመርያዎች መኖሪያ ቤታችን ስላፈረሰ የእኩልነትና ሰብዓዊ መብታችን ተነክቷል፤ እናም የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ይሰጥልን የሚል ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 37 ፍትሕ የማግኘት መብት በሰጠበት ሁኔታ በፌዴራል የሊዝ አዋጁ ለባለንብረቶቹ ምንም ዓይነት ካሳ ሳይከፈል የማስለቀቅ ሥልጣኑን ለአስፈጻሚ አካል ብቻ መስጠቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይቃረናል ይላል- ሰነዱ፡፡ 6 ነጥቦችን የያዘው አቤቱታ ለጉባኤው የቀረበው ግንቦት 2 ነው፡፡ በለገጣፎ ያለ ፕላን የተሠሩ ተብለው ከወራት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች መፍረሳቸው ይታወሳል፡፡ ተፈናቃዮቹ የ70 ሚሊዮን ብር ጉዳት ካሳ ክስ ሊመሰርቱ መሆኑም ታውቋል፡፡

Via #ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስጋት ያለበት አካባቢ የለም...

የ12ኛ እና 10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች ስጋት በሌለበት ሁኔታ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገለጸ። ኤጀንሲው እስካሁን ባለው ሁኔታ ስጋት ተብሎ የተለየ አካባቢ የለም ብሏል። ፈተናውንም ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቊን ዐስታውቋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል👆

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያሳለፍነው ቅዳሜ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባለሃብቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኘበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል፡፡

በምረቃው ስነስርዓትም ላይ የተከበሩ ክብርት አዳነች አቤቤ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትርና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣ የተከበሩ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ፣ የተከበሩ አቶ መሐመድ አህመዲን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ፣ የተከበሩ አቶ መሓመድ ጀማል የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ እና የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተገኙበት ሲሆን በአካባቢው ማህበረሰብ ወግና ስርዓት መሰረት የሆስፒታሉ የምርቃት ስነስርዓት በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተጀምሯል፡፡

በሆስፒታሉ ምርቃት ላይ የእለቱ የክብር እንግዶች የተለያየ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን አጠቃላይ የሆስፒታሉን ገጽታ እና የውስጥ ለውስጥ የሚደረጉ ዝግጅቶችንና የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችንም ጎብኝተዋል፡፡ ሆስፒታሉ በመጀመሪያው ምዕራፍ እስከ 110 ተኝተው ታካሚዎችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን ሁለተኛው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ እስከ 400 የሚጠጉ ተኝተው የሚታከሙ ታማሚዎችን ማስተናገድ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን በ2012 መጀመሪያ አካባቢ ሙሉ በሙሉ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥበትን ቦታዎች እንደ ካፌ፣ ምግብ ማብሰያ ቦታዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላይብረሪና ቤተ-ሙከራዎችን ተዟዙረው የተመለከቱ ሲሆን ከተማሪዎችም ጋር የተወሰነ ቆይታ በማድረግ የዩኒቨርሲቲውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ገምግመዋልም፡፡

ይህ ሆስፒታል በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ተመላላሽ ታካሚዎችን ጨምሮ በአመት እስከ 4 ሚሊየን ታማሚዎችን የማስተናገድ አቅም አለው።
ለዚህ ሆስፒታል ተገንብቶ መጠናቀቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ ለጉራጌ ልማት ማህበር፣ ለስራኖ ኮንስትራክሽን(ዮሐንስ ሐይሌ)፣ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ፕሮፌሠር ደጀኔ አየለ፣ ወ/ሮ ገነት ወልዴ፣ አቶ ብሩ ሚጎራ፣ ዶ/ር አብዱልሰመድ ወርቁ እንዲሁም ሌሎች የስራ ሐላፊዎች የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

Via የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአብሮነትና የምስጋና የኢፍጣር ምሽት!!

"ስንሰባሰብ፣ አንድ ስንሆን የሚኖረን ውበት ስንነጣጠል አይኖረንም" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የአብሮነትና የምስጋና የኢፍጣር ምሽት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸው ሙስሊሙ ማህበረሰብ በአንድነት ሲያፈጥር በመመልከታቸው ደስታ አንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ሙስሊሞችን ማገልገል የሚችል እስላማዊ ባንክ እንዲቋቋም መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቀ፡፡

የረመዳን ወር በፆም ስናሳልፍ በፍቅር፣ በአንድነት በቅንነት ሊሆን እንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕከት የተናገሩት፡፡

የረመዳን ወር ከውሸት እና ከማሳበቅ በመራቅ ፍሬያማ ፆም ማድረግ እንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሙስሊሙ አንድነትና ሰላም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይጠቅማል ብለዋል፡፡

የረመዳን ጾም ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ሲቀረው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች የመስገጃ ቦታዎችን እና መስጊዶችን ለማፅዳት ተዘጋጅተዋል ነው ያሉት፡፡ የሙስሉሙ ማህበረሰብም ዕለቱን ያላቸውን ለሌላቸው በማካፈል እንደሚያሳልፉት እምነቴ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በጀማ የሚሰግድበት እና የመላው አለም ሙስሊሞችንም ትኩረት የሚስብ መስጊድ ለመገንባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ባረቡት ጥያቄ መሰረት መንግስት ድጋፍ ዝግጁ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ግንባታ እንደ ነጃሺ መስጊድ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደነበራቸው ተሳትፎ በዚህኛው ግንባታም መላው የኢትዮጵያ የክርስቲያኖች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርበዋል፡፡

የሙስሊሙ ማህበረሰብ 4 ሚሊየን የዛፍ ችግኞችን ለመትከል ከአንድ ወር በኋላ በሚደረገው ሀገር አቀፍ ዘመቻ ንቁ ተሳታፊ አንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለTIKVAH-ETH አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ቤተሰብ አባላት በሙሉ፦

"ሰብአዊነት ለሰላም መሰረት"
እግር ጉዞ
የአለም ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀንን አስመልክቶ "ሰብአዊነት የሰላም መሰረት" በሚል መሪ ቃል መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የ5 ኪ.ሜ እግር ጉዞ ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ከልዩ ልዩ ደማቅ ዝግጅቶች ጋር ይካሄዳል።
ስለሆነም የዚህን የእግር ጉዞ ለማድመቅ የተዘጋጀውን ቲ-ሸርት በመግዛት እና በጉዞው ላይ በመሳተፍ የማህበሩ አጋር እና ደጋፊ እንዲሆኑ በገቢውም ሰብአዊ አገልግሎቱን እንዲያጠናክሩ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ዋጋው:- ቲ-ሸርት 130.00 ብር
ኮፍያ 50.00 ብር መሆኑን እያሳወቅን። ቲ-ሸርት እና ክፍያ በመግዛት ለመሳተፍ ለምትፈልጉ :-
1. ጋንዲ ሆ/ል አጠግብ በሚገኘው የኢትዮጽያ ቀይ መስቀል ማህበር
2. ፖሊስ ሆ/ል አካባቢ በሚገኘው አዲስ አበባ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ በስልክ ቁጥሮች 0911606337 , 0912055811, 0910122953, 0911642556, 0911448128 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
ቅድሚያ ለስብአዊነት!
#StopHateSpeech ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች የምትገኙ የተማሪ ተወካዮች/የተማሪ ህብረት/ እኒሁም የሰላም ፎረም አባላት በStopHateSpeech መድረክ ዙሪያ አብረን ልንሰራ ዝግጅት እያደረግን ስለሆነ መልዕክታቹን አስቀምጡልኝ/0919743630/@tsegabwolde/፦

√ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
√ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ
√ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ
√ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
√ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
√መቱ ዩኒቨርሲቲ

#ጅማ_ዩኒቨርሲቲ--የዚህ ሳምንት አዘጋጅ ሲሆን እስካሁን 8 ዩኒቨርሲቲዎች ጅማ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Dubbii(Haasaa) Jibbinsaa Irraa Of Has Qusannu!!/ #TIKVAH_ETH #Jimmaa
Dubbii(Haasaa) jibbiinsaa irraa of haa qusannu!

#Yuunivarsiitii_Jimmaa
#Yuunivarsiitii_Haramaayaa
.
.
.
Yeroo dhiyootti TIKVAH_ETH'n ni dhufna.
Waa'ee biyya teenyaa irratti waliin haa mari'annu!!!.

#NAGAA #JAALALA #TOKKUMMAA
👇
#BIYYA_TEENYAAF!!!.

Nuti dargaggoonni biyya teenya #ITIYOOPHIYAA jaalala, tokkummaa fi nagaan ni ijaarra!!!.

Dubbii (Haasaa) jibbiinsaa irraa of haa qusannu. #Stop_Hate_Speech