TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ👆የፋሲካ በዓል በተለያዩ የአለም ሀገራትም እየተከበረ ይገኛል። በእየሩሳሌም፣ በሩሲያ፣ በቤላሩስ፣ በግሪክ፣ በሜቄዶንያ እንዲሁም በሞሎዶቪያ ያለውን የበዓሉን አከባበር ከላይ ባሉት ፎቶዎች መመልከት ትችላላችሁ።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉሙዝ
(ትኩረት‼️)

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዊ ወረዳ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰው ሕይወት እየጠፋ፣ አካል እየጎደለና ንብረት እየተዘረፈ መሆኑን ነዋሪዎች ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

ከቀናት በፊት በዳንጉር ወረዳ በጫኝና አውራጆች መካከል በተነሳ ግጭት የተጀመረው አለመረጋጋት ወደተለያዩ አካባቢዎች #መስፋፋቱን ነው ነዋሪዎቹ ያስታወቁት፡፡

ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አስተያዬታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ‹‹እረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ከብቶቻችንም እየተነዱ እየተወሰዱ ነው፡፡ ትናንት ገበያ መውጣት አልቻልንም፤ ዛሬም #በዓሉን ለማክበር ተቸግረን ፍርሃት ውስጥ ነን›› ብለዋል፡፡

ማምቡክ መንደር 49 አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ደግሞ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ዛሬ ገበያ ነበር፤ ገና ከመቆሙ በጠዋቱ ተበትኗል፡፡ በጫካው ውስጥ ተኩስና ቀስት ማስወንጨፍ አለ፡፡ ከዳንጉር አካባቢ ነው የግጭቱ መሠረት ያለው፤ መንግሥት በፍጥነት ሊደርስልን ይገባል፡፡ ሰዎች በየጫካው እየሞቱ ነው›› ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለትም የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው መድረሱንም ገልጸዋል፡፡

የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በበኩሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ተከስቶ የነበረዉ የፀጥታ ችግር አንጻራዊ #መረጋጋት ላይ መሆኑን ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ በአሽከርካሪ እና ጫኝና አውራጅ ሥራ በተሠማሩ ወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተነግሮ ነበር፡፡

አሁን ላይ ችግሩን የፈጠሩ ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን እና ተጨማሪ የሰዉ ሕይወት #እንዳይጠፋ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉሙዝ

የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ችግር ወደተፈጠረባቸው አካባቢዎች ገብተው ለማረጋጋት እየሰሩ ይገኛሉ እንዲሁም ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ እየሠሩ እንደሚገኙ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቋል።

በሌላ በኩል...

ነዋሪዎች አሁንም ስጋት ላይ እንደወደቅን ነው፤ ሰው እየሞተ ነው ንብረትም እየተዘረፈብን ነው ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልግልን ሲጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ መረጃዎች እየተከታተልኩ አሳውቃለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ👆

"ዛሬ በወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በበጎ አድራጎት ዘርፉ አማካኝንት በወልቂጤና በጉብርየ አካባቢ የሚገኙ አረጋዊያንና ወላጅ አልባ ህፃናትን በመሰብሰብ በአሉን በጋራ አክብሮአል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የግቢያችን የአስ/ል/ኮ/ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ #ገነት_ወልዴ እና የም/ማ/አ/(የምርመርና ማህበረሰብ አገልግሎት) ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሲሳይ_ሸዋአማረ የተገኙ ሲሆን ባስተላለፉትም መልዕክት መስዋትነት ከፈለው ሀገራችንን እስከ ክብሯ ላቆዩልን አባቶችና አናቶች ክብርና ፍቅር ልንሰጣቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ለእናት ሀገራቸው ሰላም ተግተው እንዲፀልዩ ጠይቀዋል። በፕሮግራሙም ተማሪዎች የአረጋዊያኑን #እግር_ያጠቡ ሲሆን አባቶችም ተማሪዎችን እና በፕሮራሙ ላይ የተገኙትን እንግዶች #መርቀው ለሀገራችን #ሰላም ፀሎት አድረገዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የእስልምና እምነት ተከታይ እናትና አባቶች ለተማሪዎቹ የመቻቻል ባህላችንን በተግባር ያሳዩ ሲሆን እንሱም የታላቁ የረመዳን ወር ፆም መቃረቡን አስታውሰው ሁላችንም እንደየእምነታችን ለሀገራችን ሰላም በጋራ ዱአ (ፀሎት) እንድናደርግ ጠይቀዋል፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሮታራክት ኢትዮጵያ👆

"#የሮታሪ_ኢንትርናሽናል አካል የሆነው ሮታራክት ኢትዮጵያ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ #ጎዳና ላይ ለሚኖሩ ከ1000 ሰዎች በላይ #የምሳ_ማብላት እና የአልባሳት ድጋፍ በማድረግ #የትንሳኤ_በዓልን አክብሯል።"

Via Yenusshemsu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ የአራዳ ክፍል ከተማ ምክር ቤት አጋዥና ደጋፊ የሌላቸውን አረጋዊያን አሰባስቦ በመመገብ የፋሲካን በዓል በጋራ አከበረ። ምክር ቤቱ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል ሃሳብ ደጋፊ የሌላቸውን አረጋዊያን አሰባስቦ በመመገብ የፋሲካ በዓልን በጋራ አክብሯል። ምክር ቤቱ ባደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ በሬ ገዝተው በማረድ ችግረኛችና አቅመ ደካሞችን መመገብ ችለዋል። ይህ በጎ ተግባር የተደረገላቸው አረጋዊያንም ደስታቸውን በመግለፅ ለአድራጊዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥናት ሪፖርቱ ይፋ ሊደረግ ነው...

ከአካባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ #ተቃውሞ የቀረበበት ንብረትነቱ የሚድሮክ ጎልድ የሆነው #የለገደምቢ ወርቅ ማውጫ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት ሪፖርት በመጪው ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ በለገደምቢ ወርቅ ለማምረት የሚጠቀምበት ኬሚካል በአካባቢውና በማኅበረሰቡ ጤና ላይ ቀውስ እንደፈጠረ በመግለጽ፣ የሻኪሶ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማታቸው የማዕድን ሚኒስቴር ጉዳዩ በገለልተኛ ወገን እስኪጣራ የኩባንያው የማዕድን ምርት ፈቃድ ከአንድ ዓመት በፊት ማገዱ ይታወሳል፡፡

ሚያዝያ 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር አቶ #ሳሙኤል_ሁርቃቶ፣ በገለልተኛ ባለሙያዎች በሚድሮክ ጎልድ ኩባንያ አሠራር ላይ ሲካሄድ የነበረው ጥናት ሪፖርት #በመጪው ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስጠንቶ የነበረ ቢሆንም፣ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ ሚኒስቴሩ የሚድሮክ ጎልድን ፈቃድ #ካገደ በኋላ ከኩባንያው ኃላፊዎች፣ ከአካባቢው ኅብረተሰብ ተወካዮችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ተጨማሪ ጥናት በገለልተኛ ወገን እንዲከናወን ከስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል፡፡

የካናዳ መንግሥት ለማዕድን ሚኒስቴር በሚሰጠው የድጋፍ ፕሮግራም፣ በለገደምቢ ወርቅ ማውጫ ላይ ለሚካሄደው ጥናት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በካናዳ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደተካሄደ ታውቋል፡፡ በጥናቱ ግኝት ላይ ተመርኩዞ ሚኒስቴሩ የውሳኔ ሐሳብ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡ ሚድሮክ ጎልድ ሥራው በመቋረጡ ለከፍተኛ ኪሳራ እንደተዳረገ በመግለጽ፣ ጥናቱ በአፋጣኝ እንዲሠራ ሲወተውት መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በማዕድን ኩባንያዎችና በአካባቢ ማኅበረሰቦች ስለሚፈጠሩ ግጭቶች የተናገሩት አቶ ሳሙኤል፣ አንዳንድ ኩባንያዎች የማኅበረሰብ አቀፍ ሥራ እንደማያከናውኑ ከክልል መንግሥታት ጋርም ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከፌዴራል መንግሥት የማዕድን ሥራ ፈቃድ የተሰጣቸው ኩባንያዎች በክልል ውስጥ ደሴት ሆነው የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ከክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አያደርጉም፡፡ ክልሉም ምን እንደሚሠሩ አያውቅም፡፡ ልክ ችግር ሲፈጠር ኩባንያዎቹ የክልሉን መንግሥት ያናግራሉ፤›› ያሉት አቶ ሳሙኤል፣ ይህን አሠራር ለመለወጥ ሚኒስቴሩ በማዕድን ኩባንያዎችና በክልል መንግሥታት መካከል መልካም የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ክልሎች የማዕድን ኩባንያዎች የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች አውቀው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በማኅበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ሊነገሩ የሚገቡ መልካም ሥራዎች የሠሩ ኩባንያዎች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡

ሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማውጫን በ1989 ዓ.ም. ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በጨረታ በ172 ሚሊዮን ዶላር መግዛቱ ይታወሳል፡፡ የወርቅ ማውጫው በዓመት አራት ቶን ወርቅ የማምረት አቅም አለው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia