TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰላም ተምሳሌት-ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ!!

በነገው ዕለት ከ3 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ #የTIKVAH_ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ። ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል #የተሰባሰቡት እኚህ #ወጣቶች ሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ #ፍቅር እንዲነግስ ጥላቻ እንዲወገድ፤ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እንዲታረም መልዕክት ያስተላልፋሉ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካላት፤ ተማሪዎች ህብረት የተለያዩ ማህበራት እና ክበባት እኚህን የሰላም እና የፍቅር መልዕክተኞች፤ የንፁህ ልብ ባለቤት #ወጣቶችን ለመቀበል እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ተስፋ እኛ የሀገሪቱ ወጣቶች ነን!!
በፍቅር ተደጋግፈን ሀገራችንን እንገነባለን!!

ቦታ - የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ
ሰዓት - ምሽት 12:00

ፍቅር፤ ተስፋ፤ አንድነት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ-የTIKVAH_ETH ቤተሰቦች!!#tikvahethiopia

#StopHateSpeech -- #Spread_LOVE_not_hate.

በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንገናኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስራ አጥነት ለፀጥታ ችግር...

በምስራቅ ወለጋ ዞን ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር #ዋነኛ መነሻው #የሥራ_አጥ ቁጥር መብዛት መሆኑን የነቀምት ከተማ ማዘጋጃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አስታወቁ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምት ከተማ ማዘጋጃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ቶሌራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ከአሁን ቀደም ለአካባቢው ጸጥታ መደፍረስ ሥራ አጥነት ዋነኛ ምክንያት ነበር። ብዙ ሥራ አጥ ወጣቶች ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ከተማዋ እየፈለሱ ሲሆን፤ የሥራ አጥ ቁጥር መብዛት ደግሞ በአካባቢው የጸጥታ ችግር እየሆነ መጥቷል።ይህም በከተማዋ ፋብሪካዎችና ሌሎች ሰፊ የሥራ ዕድሎች አለመኖራቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

እንደ አቶ ደረጀ ገለጻ፤ በተለያዩ ወቅቶች በአካባቢው ሲነሱ የነበሩት ግጭቶች መነሻቸው መሰረተ ልማትን ከማሟላት ባሻገር በርካቶች በሥራ እጦት ምክንያት በየጎዳናው ላይ በመውጣት ለችግር መዳረጋቸውና፤ የሥራ እድል ሳይፈጠርላቸው መቅረቱ ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው። በአሁኑ ወቅት በክልሉ መንግሥትም ሆነ በፌዴራል መንግሥት ደረጃ ችግሮች በስፋት ታይተው በከተ ማዋ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እንዲከናወኑ አቅጣጫ ቢቀመጥም የህዝቡ ጥያቄና የመንግሥት ምላሽ ተመጣጣኝ አልሆነም።

ትላልቅ ፕሮጀክቶች ካልተተገበሩ በስተቀር በመንግሥት በጀት ብቻ የሥራ አጥነትን ችግር መቅረፍ አይቻልም ያሉት ኃላፊው፤ ሰፋፊ ፕሮ ጀክቶችና ፋብሪካዎች የማይገነቡ ከሆነ ሁኔታው አስጊ መሆኑንና አቅሙን እየሸጠ ያለውን የአካባ ቢውን ማኅበረሰብ ጥያቄ በአፋጣኝ መፍታት እንደ ሚገባ ገልጸዋል። ለዚህም ከከተማ አቅም በላይ የሆኑትን ጥያቄዎች የክልሉ መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት ትኩረት መስጠት እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

በነቀምት ከተማ የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር ብዛትን ሊቀንሱ ይችላሉ የተባሉ መሠረተ ልማቶች በከተማዋ አስተዳደር ታቅደው እየተሰሩ መሆናቸውን፤ ነገር ግን የህዝብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ፍልሰቱም በዚያው ልክ እየጨመረ በመምጣቱ፤ የከተማዋ የቆዳ ስፋቷም እየተለጠጠ በመሆኑ፤ የኢኮኖሚው ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ኃላፊው ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም ‹‹በቅርቡ የገበያ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል። በቅርቡም አገልግሎት ይሰጣሉ። እነዚህ የሥራ ዕድልን ይፈጥራሉ ተብሎ ይታሰባል። በዚህ ዙሪያ በተለይ በገበያ ማዕከል ላይ ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚኖር ተስፋ ተደርጓል።

በተቻለ አቅም #ሥራ_አጥ የሆኑት የሥራ ፈቃድ አውጥተው የሥራ ዕድሉ ተፈጥሮላቸው በተመጣጣኝ ዋጋ ተወዳድረው እንዲሰሩ ይደረጋል። አካባቢው ከለማ ህዝቡ አብሮ ኢኮኖሚውን ያሳድጋል። ከተማ አስተዳደሩ በራሱ በቂ አቅም ስለሌለው መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግለትም እየተጠየቀ ነው። ህዝቡ ይህንን ተገንዝቦ በራሱ ተነሳሽነት የሥራ ዕድል ፈጥሮ እንዴት መስራት እንዳለበት ባለን አቅም፣ ገንዘብም ሆነ እውቀት አክለንበት ወደ ሥራ እንዲገባ አቅደን እየሰራን ነው። ለዚህም የህዝብ መድረክ በመፍጠር በየጊዜው ውይይቶች ይደረጋሉ›› ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አለሙ ስሜ...

በትላንትናው ዕለት የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማእከላዊ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር አለሙ ስሜ ከኃላፊነታቸው ተነስተው፤ በምትካቸውም አቶ አዲሱ አረጋ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮዽያ አየር መንገድ #ቻይና ስሪት የሆኑ ሲ919 ሞዴል አውሮፕላኖችን ለመጠቀም የሚያስችለውን ምክክር እያደረገ እንደሆነ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያምን ጠቅሶ ዥንዋ ዘግቧል። ሲ919 ቻይና ስሪት የመንገደኞች አውሮፕላንን ጥቅም ላይ ለማዋል አየር መንገዱ ኮሚቴ አቋቁሞ ከሚመለከታቸው የቻይና ኩባንያዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ እንደሆነም ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። ኮማክ (COMAC) በተሰኘ ምህፃረ ቃል የሚታወቀው የቻይና የንግድ አውሮፕላኖች አምራች ኮርፖሬሽን የምርት ውጤት የሆኑትን አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮዽያ በማምጣት ሃገሪቷን የአፍሪካ የቻይና አቪዬሽን ማዕከል የማድረግ ሃሳብ እንዳለ ዋና ስራ አስፈፃሚው መግለፃቸውን መረጃው ጠቁሟል። አየር መንገዱ በቻይናና አፍሪካ መካከል የሚኖረውን ግንኙነት የቻይናን የአቪዬሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማጠናከር አላማ እንዳለውም አቶ ተወልደ ተናግረዋል። የኢትዮዽያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደምም ከመንገደኞች አውሮፕላን ጋር የተያያዙ የተለያዩ ማሽነሪዎች እና መገልገያዎችን ከቻይና እንደሚያስመጣ የጠቆመው ዘገባው አየር መንገዱ የቻይና ከተሞች ወደሆኑት ጉዋንⶱ እና ቤጂንግ በየቀኑ እንዲሁም በሳምንት ሶስቴ ደግሞ ወደ ቼንግዱ በረራ እንደሚያደርግ አመልከቷል። በተጨማሪም አየር መንገዱ በየቀኑ ወደ ሆንኮንግ እና ሻንሃይ የካርጎ በረራዎችን ያደርጋል። ቻይና ሰራሹ ሲ919 እኤአ በሜይ 5/2017 ሻንሃይ ከሚገኘው ፑዶንግ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የተሳካ የሙከራ በረራ ማድረጉንም ዥንዋ በዘገባው ማጠቃለያ ላይ አንስቷል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ‼️
.
.
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለፕሬዝዳንትነት ቦታ ብቃቱና ፍላጎት ያላቸዉ አመልካቾች #እንዲወዳደሩ ጥር 24/2011 ዓ.ም በተለያዩ ሚዲያዎች ባወጣዉ ግልጽ ማስታወቅያ መሰረት አመልካቾች መረጃቸዉን በማስገባት በተለያዩ ደረጃዎች ዉድድር ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።

በምርጫ ሂደቱም ከ250 በላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት የዩቨርሲቲዉ ሴኔት እና የስራ አመራር ቦርድ በቀን 01/07/2011 ዓ.ም. የቃለ-መጠይቅ ፓናል በማካሄድ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩና ማጣሪያዎችን አልፈው የደረሱ 9 #እጩዎችን በመገምገም 5 እጩዎችን ለዩኒቨሲቲዉ የስራ አመራር ቦርድ አስተላልፏል፡፡

የዉድድሩ ሂደት የተመራዉ የሳይንስና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስቴር ባወጣዉ መስፈርት ሲሆን ሂደቱን ለመምራት አምስት ሰዎችን የያዘ ኮሚቴ ተቋቁሞ በየደረጃዉ ግምገማ ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ ኮሚቴዉ ከቦርድ አባላት፣ ከሴኔት አባላት፣ ከተማሪ፣ ከመምህራን እና ከአስተዳደር ሰራተኞች ተወካይ የተዉጣጣ ሲሆን የዉድድር ማስታወቂያ ከማዉጣት ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲዉ የስራ አመራር ቦርድ ጉባኤ የሂደቱን ዉጤት እስከ ማሳወቅ ድረስ በትጋት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በዚሁ መሰረት የዩኒቨርሲቲዉ የስራ አመራር ቦርድ ሚያዚያ 02/2011 ዓ.ም ባካሔደው ልዩ ጉባኤ 3 እጩዎችን (ዶ/ር ጀማል አባፊጣ፣ ፕሮፌሰር አርጋዉ አምበሉ እና ዶ/ር ናቃቸዉ ባሹን) በእጩነት ለሳይንስና ክፍተኛ ት/ት ሚኒስቴር ኣቅርቧል:: የሳይንስና ክፍተኛ ት/ት ሚኒስቴርም ዶ/ር ጀማል አባፊጣን ከሚያዚያ 11/2011 ዓ ም ጀምሮ አዲሱ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነዉ እንዲያገለግሉ መርጧቸዋል፡፡

ዶ/ር ጀማል አባፊጣ የዩኒቨርሲቲዉ ነባር መምህር እና ተመራማሪ ሲሆኑ በተለያዩ ደረጃዎች በዩኒቨርሲቲውና ከዩኒቨርሲቲው ውጭ በሃላፊነት ያገለገሉና በአሁኑም ወቅት የማህበረሰብ አገልግሎት ቢሮ ዳይሬክተር ሆነዉ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለዚህ ሃላፊነት በመመረጥዎ የተሰማዉን ልባዊ ደስታ እየገለጸ መልካም የስራና የስኬት ዘመን እንዲሆንልዎ ይመኛል፡፡

ሚያዚያ 11/2011 ዓ.ም
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶ/ር ጀማል ኣባፊጣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነዉ ተመርጠዋል። #ጅማ_ዩኒቨርሲቲ

Via JIMMA UNIVERSITY
@tsegabwolde @tivahethiopia
አቶ ሽመልስና አቶ አዲሱ🛫ደንቢዶሎ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ እና የኦሮሞ ዴክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ #አዲሱ_አረጋ ከደንቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ዛሬ ወደ #ደንቢዶሎ አቅንተዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዶክተር አሚር አማን...

"ዶ/ር #ጀማል_አባፊታ የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት በመሆን ተሹመዋል። የዩኒቨርስቲው ኢንተርን ሀኪሞች ያነሷቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ ዛሬ ከፌደራል መስሪያ ቤት ተወካዮችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት የሚያካሂዱ ይሆናል።መልካም የስራ ዘመን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢንተርን ሀኪሞች...

በጅማ ዩኒቨርስቲ #የኢንተርን_ሀኪሞች ባነሷቸው ጥያቄዎች ዙሪያ አዲሱ #ፕሬዘዳንት/ዶክተር ጀማል አባፊታ/ ከሚመለከታቸው የፌደራል መስሪያ ቤት #ተወካዮች እና ሌሎች አካላት ጋር #ውይይት ያደርጋሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደቀያቸው እየተመለሱ ነው...

ከደቡብ ክልል ጎፋ ዞን፣ መሎ ኮዛ ወረዳ ከወራት በፊት በተፈጠረ ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው #መመለስ ጀመሩ። ከአካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ ከ37 ሺ በላይ የባስኬቶ ብሔረሰብ አባላት በመጠለያ ጣቢያዎች በቆዩባቸው ጊዜያት የከፋ ችግር አሳልፈዋል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia