TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስራ አጥነት ለፀጥታ ችግር...

በምስራቅ ወለጋ ዞን ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር #ዋነኛ መነሻው #የሥራ_አጥ ቁጥር መብዛት መሆኑን የነቀምት ከተማ ማዘጋጃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አስታወቁ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምት ከተማ ማዘጋጃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ቶሌራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ከአሁን ቀደም ለአካባቢው ጸጥታ መደፍረስ ሥራ አጥነት ዋነኛ ምክንያት ነበር። ብዙ ሥራ አጥ ወጣቶች ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ከተማዋ እየፈለሱ ሲሆን፤ የሥራ አጥ ቁጥር መብዛት ደግሞ በአካባቢው የጸጥታ ችግር እየሆነ መጥቷል።ይህም በከተማዋ ፋብሪካዎችና ሌሎች ሰፊ የሥራ ዕድሎች አለመኖራቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

እንደ አቶ ደረጀ ገለጻ፤ በተለያዩ ወቅቶች በአካባቢው ሲነሱ የነበሩት ግጭቶች መነሻቸው መሰረተ ልማትን ከማሟላት ባሻገር በርካቶች በሥራ እጦት ምክንያት በየጎዳናው ላይ በመውጣት ለችግር መዳረጋቸውና፤ የሥራ እድል ሳይፈጠርላቸው መቅረቱ ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው። በአሁኑ ወቅት በክልሉ መንግሥትም ሆነ በፌዴራል መንግሥት ደረጃ ችግሮች በስፋት ታይተው በከተ ማዋ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እንዲከናወኑ አቅጣጫ ቢቀመጥም የህዝቡ ጥያቄና የመንግሥት ምላሽ ተመጣጣኝ አልሆነም።

ትላልቅ ፕሮጀክቶች ካልተተገበሩ በስተቀር በመንግሥት በጀት ብቻ የሥራ አጥነትን ችግር መቅረፍ አይቻልም ያሉት ኃላፊው፤ ሰፋፊ ፕሮ ጀክቶችና ፋብሪካዎች የማይገነቡ ከሆነ ሁኔታው አስጊ መሆኑንና አቅሙን እየሸጠ ያለውን የአካባ ቢውን ማኅበረሰብ ጥያቄ በአፋጣኝ መፍታት እንደ ሚገባ ገልጸዋል። ለዚህም ከከተማ አቅም በላይ የሆኑትን ጥያቄዎች የክልሉ መንግሥትና የፌዴራል መንግሥት ትኩረት መስጠት እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

በነቀምት ከተማ የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር ብዛትን ሊቀንሱ ይችላሉ የተባሉ መሠረተ ልማቶች በከተማዋ አስተዳደር ታቅደው እየተሰሩ መሆናቸውን፤ ነገር ግን የህዝብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ፍልሰቱም በዚያው ልክ እየጨመረ በመምጣቱ፤ የከተማዋ የቆዳ ስፋቷም እየተለጠጠ በመሆኑ፤ የኢኮኖሚው ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ኃላፊው ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም ‹‹በቅርቡ የገበያ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል። በቅርቡም አገልግሎት ይሰጣሉ። እነዚህ የሥራ ዕድልን ይፈጥራሉ ተብሎ ይታሰባል። በዚህ ዙሪያ በተለይ በገበያ ማዕከል ላይ ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚኖር ተስፋ ተደርጓል።

በተቻለ አቅም #ሥራ_አጥ የሆኑት የሥራ ፈቃድ አውጥተው የሥራ ዕድሉ ተፈጥሮላቸው በተመጣጣኝ ዋጋ ተወዳድረው እንዲሰሩ ይደረጋል። አካባቢው ከለማ ህዝቡ አብሮ ኢኮኖሚውን ያሳድጋል። ከተማ አስተዳደሩ በራሱ በቂ አቅም ስለሌለው መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግለትም እየተጠየቀ ነው። ህዝቡ ይህንን ተገንዝቦ በራሱ ተነሳሽነት የሥራ ዕድል ፈጥሮ እንዴት መስራት እንዳለበት ባለን አቅም፣ ገንዘብም ሆነ እውቀት አክለንበት ወደ ሥራ እንዲገባ አቅደን እየሰራን ነው። ለዚህም የህዝብ መድረክ በመፍጠር በየጊዜው ውይይቶች ይደረጋሉ›› ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia