TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር የምስጋና እና የሽኝት ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል። የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብሩ በአዳማ ከተማ ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው። በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የትግራይ ክልል ምክተል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተገኝተዋል። በተጨማሪም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናት የምስጋና እና የሽኝት መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በቀጣዩ ሳምንት ወደ ቻይና ያቀናሉ፡፡ የጉዟቸው ዐላማ Belt & Road Forum for International Cooperation በተሰኘው ሁለተኛው የቻይና ዐለም ዐቀፍ የኢኮኖሚ መድረክ ላይ ለመሳተፍ መሆኑን ፎርቹን አስነብቧል፡፡ በጉባዔው 40 የሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል፡፡ ጉባዔው "Belt and Road Cooperation: Shaping a Brighter Shared Future በሚል መሪ ቃል እኤአ ከሚያዚያ 26 እስከ 27 ይካሄዳል፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋምቤላ #የሙርሌ_ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት #ጥቃት አደረሱ‼️
.
.
በጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኡቶዉ ኡኮት ገለፁ።

ኃላፊው አክለውም ለኢፌድሪ መከላከያም ድንበር አቋርጦ የገባ የታጠቀ ኃይል እንዳለ በማሳወቅ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው መጠየቃቸውን ይናገራሉ።

አቶ ኡቶዉ እንደሚሉት በጋምቤላ በዚህ ሰዓት በጋ ስለሆነ እና ክልሉን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያጋራው ድንበር ሰፊና ክፍት ስለሆነ የታጣቂዎች የመግባትና የመውጣት አዝማሚያ አለ።

የሙርሌ ታጣቂዎች ባለፈው ወር ድንበር አቋርጠው በመግባት ከኑዌር ዞን ጂካ ወረዳ አንድ ሕፃን መውሰዳቸውን ያስታውሳሉ።

እንዲሁም ከዚሁ ወረዳ 150 ከብት እና 234 ፍየሎችንም ዘርፈዋል ያሉት ኃላፊው ከሳምንት በፊት ጆር በሚባል አካባቢ ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከእነርሱ ወገን ሰው መጎዳቱን ይናገራሉ።

አቶ ኡቶዉ ክልሉ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻ በመጠቀም ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በቅርብ የሙርሊ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት ባደረሱባቸው አካባቢዎች መሄዳቸውን የሚናገሩት ኃላፊው የአካባቢው ነዋሪ ስጋት እንዳለበት መታዘባቸውን ገልፀዋል። ክልሉ የነዋሪውን ስጋት ለማስወገድ እና ቀዬውን ለቅቆ እንዳይሄድ የተለያዩ የማረጋጋት ስራዎችን መስራታቸውንም ተናግረዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከሁለት ዓመት በፊት፤ በኑዌር ዞን እና አኙዋ ዞኖች ገብተው 234 ሕፃናት አፍነው ሲወስዱ፣ ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ከ2ሺህ በላይ ከብቶች መውሰዳቸውንም ኃላፊው ጨምረው ያስታውሳሉ።

በወቅቱ የኢፌድሪ መከላከያ ኃይል ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባትና ታጣቂዎቹ የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ጥቃት በመፈፀም ታፍነው ከተወሰዱት ሕፃናት መካከል ከ100 ሕፃናት በላይ ወደ ቤተሰቦቻቸው መልሷል። ቀሪዎቹ ግን የደረሱበት አልታወቀም።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አሜን_መሀመድ ተገኝቷል! ሁላችሁም ላደረጋችሁት #ትብብር ቤተሰቦቹ ከልብ #አመስግነዋችኃል!! #እናመሰግናለን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሞኑን መንግሥት ድጋፍ እንዲያድርግለት ለመጠየቅ መዘጋጀቱን የዋዜማ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ መንግሥት ግን የካፒታል ድጋፉን የሚለቀው ባንኩ የወሰዳቸውን ማሻሻያዎች አጥጋቢ ከሆኑ ብቻ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ከሦስት ዐመት በፊት መንግሥት ለባንኩ ማገገሚያ የ2.5 ቢሊዮን ብር ድጎማ ቢሰጠውም ብዙም መሻሻል አላሰየም፡፡ ባንኩ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ብድሮችን ማስመለስ ባለመቻሉ ሕልውናው አደጋ ውስጥ የወደቀበት ሲሆን አጠቃላይ ካበደረው 46 ቢሊዮን ብር 40 በመቶው የተበላሸ ብድር እንደሆነ ራሱ አምኗል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በአዳማ ከተማ የምስጋና እና የሽኝት ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህ ፕሮግራም ላይ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ ለኢትዮጵያውያን‼️

በካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ #በሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ #ኢትዮጵያውያን በሙሉ #ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ። በአሁኑ ወቅት በሊቢያ የተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተስተዋለ መሆኑን ኤምባሲው አስታውቋል።

በሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የጸጥታ ሁኔታዎች በአስተማማኝ ደረጃ እስኪረጋጉ ድረስ ማንኛውም ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ከመሄድ እንዲቆጠቡ ጠይቋል።

ኤምባሲው አክሎም በሀገሪቱ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

ማንኛውም ድንገተኛ ሁኔታዎች ካጋጠማቸውምን በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ለኤምባሲው በመደወል እንዲያሳውቁም በካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሶ ጠይቋል።

የስልክ ቁጥሮቹም፦

(202) 33353696
(202) 33355958
(202) 33355937
(202) 37616269 ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
 
#update የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከስድስት ወራት በፊት #ተቃጥለው የነበሩ ሱቆች በአዲስ መልክ አስገንብቶ ለነጋዴዎች አስረከበ፡፡ በተለምዶ አሮጌ ገበያ በመባል የሚታወቀውና የከተማው ትልቁ ገበያ መስከረም 29/2011 ዓ.ም.ነበር ደንገተኛ ቃጠሎ የደረሰበት። የከተማው አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ተስፋዬ ርክክቡ ማምሻውን በተካሄደበት ወቅት እንደገለጹት 730 ሱቆችን በውስጡ ያካተተው የገበያው ስፍራ ግንባታ 40 ሚሊየን ብር የፈጀ ነው። ለግንባታው የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችና አመራሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብና የእምነት ተቋማት ድጋፍ ማድረጋቸውም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል። በርክክብ ስነስርዓቱ የከተማው ምክትል ከንቲባ ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጀነራል ዋቆ ጉቱ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ዛሬ ከሰዓት በትምህርት ቤቱ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ 37 ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን እና አስፈለጊው የህክምና ድጋፍ ተደርጎላቸው አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተገልጿል። የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት ራሳቸውን ስተው የወደቁ ተማሪዎችን ወደ ቤቴል ሆስፒታ እንዲወሰዱ በማድረግ ህክምና ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ህክምና ከተደረገላቸው በኋላም 34 የሚሆኑ ተማሪዎች ተሽሏቸው በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ሶስቱ ተማሪዎች ተጨማሪ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በቤተል ሆስፒታል በተደረገው ምርመራ ይሄነው የሚባል ውጤት ባለመገኘቱ የታካሚዎቹ የደም ናሙና ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን ከአዲስ ቲቪ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech-----አባያ ካምፓስ👆

#በአባያ_ካምፓስ----አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ከTIKVAH-EHT ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 2ኛው #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ #ዝግጅት በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia