TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሊቨርፑል ደጋፊዎች ከአሁን ቀደም እንደሚያደርጉት እግርኳሱን አብሮ ከመመልከትና በኳሱም ከመዝናናት ባለፈ እርዳታ ለሚሹና ትምህርት መማርን እየፈለጉ በትምህርት መርጃ መሳርያዎች እጥረት ይህ ህልማቸውና ፍላጎታቸው ላልተሟላላቸው ወገኖች አቅማቸ በፈቀደ በመርዳት ህልማቸውን ብሩህ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል።

#እሁድ ነሀሴ 6 ሊቨርፑል የመጀመርያውን የውድድር አመት ጨዋታውን በአንፊልድ ዌስትሀምን በመግጠም ይጀምራል። ታድያ ይህንኑ ጨዋታ ኢትዮጵያ የሊቨርፑል ደጋፊዎች አንድ ላይ በመሆን የሚመለከቱት ሲሆን እግረ መንገዳቸውንም ድጋፍ ያደርጋሉ

ደብተር
እስኪርቢቶ
እርሳስ
መቅረጫ
ላጺስ እና የመሳሰሉ ቁሶችን አቅማችን በፈቀደ መጠን በቦታው ይዘን በመገኘት የበኩላችንን የምናደርግ ይሆናል።

ቦታው = ዋቢሸበሌ ሆቴል ጋርደን
ሠዓት = ከ 8:30 ጀምሮ
መግቢያ = የተለየ የመግቢያ ዋጋ የሌለው ሲሆን ሆቴሉ ሌሎች ጨዋታዎችን በሚያሳይበት የመግቢያ ዋጋ (20ብር)

ለምታደርጉት እርዳታ በፈጣሪ ስም ምስጋናን ቀድመን ማቅረብ እንወዳለን!
#አዲስ_አበባ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️በ2010 ዓ.ም የአመቱ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ኦቦ #ለማ_መገርሳ እንደሆኑ ይታወቃል። ካላይ የምትመለከቷቸው ፎቶዎች #እሁድ ዕለት የተላኩልኝ ናቸው ሁኔታዎች ሳይመቻችልኝ ቀርቶ አላቀረብኳቸውም ነበር።

©ዳንኤል(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምእራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ገላን ወረዳ ‘’የገዳ መጫ” የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ዝግጅቱ #መጠናቀቁን የወረዳው  የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የፊታችን #እሁድ በሚከበረው በዓል ከኦሮሚያ ክልል 10 ዞኖች የተውጣጡ አባገዳዎችና ሌሎች እንግዶች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡ በዓሉ #ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ከወረዳውና ከኢጃጂ ከተማ የተመለመሉ ፎሌዎችና ቄሮዎች ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ‼️

በአዲስ አበባ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ይካሄዳል የሚባለው ሰላማዊ ሰልፍ #ዕውቅና_የሌለው መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለfbc በላከው መግለጫ፥ አንዳንድ ግለሰቦች #ቅዳሜ እና #እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

ይሁን እንጂ ሰልፉ በከተማ አስተዳድሩም ሆነ በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑ ነው የተገለፀው።

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እና የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ሊካሄድ የታሰበው ሰልፍ ምንም ዓይነት እውቅና የሌለው መሆኑን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ አካላት የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር አስታውቋል።

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የተያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

ስለሆነም ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው በመሆኑ ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፎ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከገና በዓል ጋር ተያይዞ ደንበኞቹ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ በማሰብ #እሁድ (ታህሳስ 28 ቀን 2011 ዓ.ም) እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በተመረጡ ቅርንጫፎቹ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ከባንኩ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየውም የሚከተሉት ቅርንጫፎቹ ነገ ክፍት ናቸው።

1. አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ
2. ማህተም ጋንዲ ቅርንጫፍ
3. ሸገር ቅርንጫፍ
4. ስድስት ኪሎ ቅርንጫፍ
5. ሽሮሜዳ ቅርንጫፍ
6. ጥቁር አንበሳ ቅርንጫፍ
7. ፊንፊኔ ቅርንጫፍ
8. ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ
9. ጎተራ ቅርንጫፍ
10. አቃቂ ቅርንጫፍ
11. ባልቻ አባነፍሶ ቅርንጫፍ
12. ገዛኸኝ ይልማ ቅርንጫፍ
13. ገርጂ ቅርንጫፍ
14. ቦሌ መድሃኒዓለም ቅርንጫፍ
15. መስቀል ስኩዌር ቅርንጫፍ
16. ባምቢስ ቅርንጫፍ
17. ሰበታ ቅርንጫፍ
18. ዓለም ባንክ ቅርንጫፍ
19. ቤቴል ቅርንጫፍ
20. ዘነበ ወርቅ ቅርንጫፍ
21. ተስፋ ድርጅት ቅርንጫፍ

ምንጭ፦ epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia