#update ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ። ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት መምህር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
Via AAMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via AAMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግር...
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል ያረቀቀዉ አዋጅ፦ «በተለይ በማኅበረሰቡና በሕዝቡ መካከል እኩልነት እንዲሰፍን» ለማጎልበት የወጣ ነው አለ። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ «በጥንቃቄ፤ ከሕገ-መንግሥቱም አጠቃላይ ከዜጎች መሠረታዊ መብቶች ጋር በማይጋጭ መልኩ አዋጁን ለማዘጋጀት ጥረት» መደረጉን ተናግረዋል። ረቂቁ በውይይት ላይ እንዳለ የገለጡት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፦ «በሕጉ ውስጥ የወንጀል ድንጋጌዎች» መካተታቸውን ተናግረዋል። «ማንነታቸውን ደብቀው በተለያየ መልኩ በተለይ [በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች] የዜጎችን፤ የብሔሮችን እና የሌሎች በሕገ-መንግሥቱ እና በሌሎች ሕግጋት የተረጋገጡ መብቶችን የሚጥሱና ከዚህ በተቃራኒ የሚንቀሳቀሱ» አካላት ሕግ ማክበር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። እነዚህ አካላት፦ ግለሰቦች፤ ቡድኖች፤ የፖለቲካ አካላት፤ የመንግሥት ተሹዋሚዎች፤ እንዲኹም የመንግሥት አለያም የግል መገናኛ ዘዴዎች ሊኾኑ እንደሚችሉ ገልጠዋል። «ይኽን ሕግ አክብረው መንቀሳቀስ» እንዳለባቸውም አሳስበዋል። «ከዚያ ባለፈ ግን የሕግ የበላይነቱን ለማስከበር በሕጉ ውስጥ በተቀመጠው የወንጀል ድንጋጌ መንግሥት አስፈላጊውን ርምጃ የሚወስድ መኾኑ ነው» ብለዋል።
Via DW

አለመግባባቱ ተፈቷል...ወሎ ዩኒቨርሲቲ‼️
ከቀናት በፊት #በወሎ_ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረው #አለመግባባት መፈታቱን የዩኒቨርሲቲው አኃላፊዎችና ተማሪዎች ተናገሩ፡፡ ባለፈው ማክሰኞ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በከሚሴና አጣዬ አካባቢዎች ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው በተቀሰቀሰ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንና ሌሎች መጠነኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ህክምና ተሰጥቷቸው ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ዶ/ር #አባተ_ጌታሁን ለዶየቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በተማሪዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የዞን ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተማሪ ተወካዮች ባደረጉት ጥረት ችግሩ መፈታቱንም አስታውቀዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሀኑ አሰፋ እርቅ መፈፀሙን አረጋግጠው የተቋረጠው ትምህርት የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር መናገራቸውን የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዘግቧል፡፡ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚያስተምራቸው ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች አሉት፡፡
ምንጭ-የጀመን ራድዮ

ጀማ ዩኒቨርሲቲ🔝
#የኢንተር_ሀኪሞች መብታችን ይከበር ደህንነታችን ይጠበቅ ለምንጠይቀው ጥያቄ አግባብነት ያለው ምላሽ ይሰጠን ብለዋል::

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ....
በነገው ዕለት ከሁለት ከተሞች የተውጣጡ እና ለ #StopHateSpeech እንቅስቃሴ ወልቂጤ የሚገቡትን የTikvah-Ethiopia የሰላም እና የፍቅር አምባሳደሮችን ስም ዝርዝር አሳውቃችኃለሁ::
የቤተሰባችንን አባላት በክብር እንደምትቀበሉልን ተስፋ አድርጋለሁ!!

ተዋወቋቸው!
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ አርቲስት ጸደንያ ገብረ ማርቆስ ን የጽዱ: ምቹ እና አረንጓዴ የጤና ተቋም የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ናት። አርቲስት አዜብ ወርቁ ደግሞ የጤናማ እናትነት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ናት።
https://www.facebook.com/sphmmc/
ትክክለኛ የቅዱስ ጳውሎስ ቻናል-t.iss.one/spmmc

#update የሱዳን ጦር ፕሬዝደንት ዑመር ሐሠን አል በሽርን ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ 16 ሰዎች መግደሉን የአገሪቱ የለውጥ አራማጆች አስታወቁ። የሱዳን የዶክተሮች ማሕበር በዛሬው ዕለት እንዳለው ባለፈው ሐሙስ ብቻ 13 ሰዎች ከጦር ሰራዊቱ በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል። ትናንት አርብ አንድ ወታደርን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ሰዎች መገደላቸውን ማሕበሩ ገልጿል። የሱዳን የዶክተሮች ማሕበር ለግድያው የመንግሥቱን ኃይሎች እና ስማቸውን ያልጠቀሳቸውን ታጣቂዎች ተጠያቂ አድርጓል።
የሱዳን ፖሊስ በትናንትናው ዕለት 16 ሰዎች የተገደሉት በተባራሪ ጥይት እንደሆነ ገልጾ ነበር። በፖሊስ መረጃ መሰረት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተካሔዱ ሰልፎች እና የመቀመጥ አድማዎች ሌሎች 20 ሰዎች ቆስለዋል።
አል-በሽር ተገፍተው ከሥልጣን ሲወርዱ ወታደራዊውን የሽግግር ምክር ቤት የመምራት ኃላፊነት የተረከቡት መከላከያ ምኒስትር እና ምክትል ፕሬዝዳንት አዋድ ኢብን አውፍ በተራቸው ገሸሽ ብለዋል።
በዳርፉር የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የሚከሰሱ ታጣቂዎችን ይደግፋሉ በሚል በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው አውፍ ጄኔራል አብደል-ፋታሕ ቡርሐን እንደሚተኳቸው አስታውቀዋል። ሥልጣናቸውን የለቀቁት ለሱዳን ጥቅም ሲሉ እንደሆነም ገልጸዋል።