TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጀማ🔝

"እሁድ እለት የሆኑ ግለሰቦች የጅማ ህክምና ማዕከል ውስጥ ሁለት ኢንተርኖች (ሀኪሞች) ላይ #ድብደባ ካደረሱ በኻላ ከዛሬ 01/8/11 ጀምሮ ኢንተርኖች #የሥራ_ማቆም አድማ አድርገዋል። በመቀጠለም ከላይ ያለውን #የአቋም_መግለጫ አውጥተዋል።”

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሰሞኑን በውጥረት ውስጥ የከረሙት አጣዬ ከተማ፣ ሞሉ ሜዳ፣ ይምልዎ፣ አላላ አማን ገበያ፣ አላላ ኩቢ ቢያ፣ እዝግዬ እና ሰንበቴ ከተማ ሰላም አየር መተንፈስ ጀምረዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ልዩ ሃይል፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የወረዳ አመራሮች፣ ቄሮዎች እና ህዝቡ በየደረጃው በመመካከር ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው፡፡ የተሽከርካሪ መንገዶች ተከፍተዋል፡፡ ከአጣዬ ከተማ እና አካባቢዋ በግጭቱ ምክኒያት የሸሹ ሰዎችን ወደ እየቤታቸው እየተመለሱ ነው፡፡ በማህበራዊ መዲያዎች የሚለቀቁ የሀሰት ወሬዎች ውሸት መሆናቸውን መላው ህብረተሰብ በመረዳት ተረጋግቶ የግል ስራውን እንዲሰራ መልዕክታችን ነው፡፡”

Via ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ተጥልለው የሚገኙ ከመተሐራ አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች ችግር ላይ ወድቀናል ብለዋል፡፡ የአማራና አርጎባ ብሄረሰብ ተወላጅ መሆናቸውን የገለጹት #ተፈናቃዮቹ ቤት ለቤት ጥቃት ስለመፈጸሙባቸው #እንደተፈናቀሉ ለDW ተናግረዋል፡፡ ብዛታቸው 748 ያህል ይሆናል፡፡ ተፈናቃዮቹ የተፈናቀሉት ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ምንጃር ወረዳ እና ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ የወሰን ግጭት በቅርቡ መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር፡፡

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከግንቦት 21 ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገልፃል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 400 ሺህ ብር የሚገመት የዕለት ደራሽ ቀለብ ዕርዳታ አደረጉ፡፡ ድጋፉን ከከተማዋ ነዋሪዎች በማሰባሰብ በኩል የከተማዋ ወጣቶች ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ታውቋል፡፡ ነዋሪዎቹ ዕርዳታ ያደረጉት በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ፣ ካራ ቆሬና አካባቢው በሰሞኑ ግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ዕለታዊ ድጋፍ ነው፡፡ ድጋፉንም ወደ አካባቢው ወስደው ለተጎጂዎቹ ማስረከባቸው ታውቋል፡፡ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች በንጹኃን ወገኖች ላይ የደረሰውን ጉዳት በሰላማዊ ሰልፍ ማውገዛቸው የሚታወስ ነው፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስሜን ተራሮች🔝

የስሜን ተራሮች ቃጠሎ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው:: የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ግጭ አካባቢ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እየተቃጠለ ነው። በፓርኩ አስተርጓሚና አስጎብኝ የሆነው ወጣት አስረሳኸኝ ሞላ ለአብመድ እንደገለፀው ቃጠሎው ሰፊ ቦታን ያካለለና #ለመቆጣጠር የከበደ ነው።

ከትናንት ጀምሮ እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከዛሬ እኩለ ቀን በኋላ ከአቅም በላይ መሆኑን ተነግራል። በቃጠሎው ምክንያት በአካባቢው ያለውን ማረፊያ ካምፕ ጥለው መውጣታቸውንም ነግሮናል።

የፓርኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው ደግሞ እሳቱ በከፍተኛ ነፋስ እየታገዘ በመሆኑ ለመቆጣጠር ማስቸገሩን ተናግረዋል። በተለይ ከቀኑ 6:00 ገደማ ጀምሮ እሳቱ ሰፊ ቦታን እያካለለ መሆን ተናግረዋል።

ከፍተኛ የሰው ኃይል እሳቱን ለመቆጣጠር መሠማራቱን የገለጹት አቶ ታደሰ ምግብ እየቀረበላቸው አሁንም ከዚያው ሥራ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ነዳጅ እና የነዳጅ ውጤቶችን የሚያስተዳድር ባለሥልጣን ለማቋቋም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቂቅ ሕግ እንደቀረበ ሸገር ዘግቧል፡፡ ረቂቁ የአዲሱ ተቋም ዐላማ በመላ ሀገሪቱ ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትን እና ሥርጭትን መቆጣጠር እንደሚሆን ይገልጻል፡፡ ደረጃውን የጠበቀ ነዳጅ ወደ ሀገር እንዲገባ እና ፍትሃዊ ሥርጭት እንዲኖር የቁጥጥር ሥርዓትም ይዘረጋል፡፡ ረቂቅ ሕጉ ከጸደቀ የባለሥልጣኑ ተጠሪነት ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ይሆናል፡፡

Via Sheger FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአልጀርያ ምክር ቤት ዛሬ አዲስ #የሽግግር ጊዜ መሪ ሰየመ። ባለፈው ሳምንት ሥልጣናቸውን በለቀቁት በቀድሞው የአልጀሪያ ፕሬዝዳንት አቤደላዚዝ ቡተፍሊካ ምትክ አብዱልቃድር ቤንሳላህን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት መርጧል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia