TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ አዲሱ አረጋ‼️

"...ሰሞኑን #እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ካሉ ከተሞች አንዱ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ እና በመደበኛ ሚዲያም ጭምር ህገ ወጥ ግንባታ ላይ እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ በለገጣፎ ለገዳዲ ብቻ እየተደረገ ያለ እና #ብሄር ለይቶ #እርምጃ አስመስሎ እየቀረበ መሆኑን አስተዉለናል፡፡ ይህ #ስህተት ነዉ፡፡ እስካሁን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 25 ከተሞች በተደረገ እንቅስቃሴም ህግን ብቻ ባማከለ 36,117 ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡"

https://telegra.ph/ህገ-ወጥ-ግንባታን-በተመለከተ-አቶ-አዲሱ-አረጋ-02-22
ሰላማዊ ሰልፍ አልተጠራም‼️

በአዲስ አበባ ከተማ እሁድ የካቲት 17/2011 ዓ/ም #በመስቀል_አደባባይ ሠላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል #ጥያቄ ያልቀረበለት መሆኑን ለኮሚሽኑ የገለፀ ሲሆን ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው።
በመሆኑም #ሰልፍ_እንወጣለን በሚል በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ #በጥብቅ አሳስቧል።

ይህን ተላልፎ በሚገኙ አካላት ላይም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ #እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማሳሰቢያ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል #ጥያቄ አልቀረበለትም።

በመሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ ተጠራ የተባለው ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው።

ስለሆነም #ሰልፍ_እንወጣለን በሚል በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ይህን ተላልፎ በሚገኙ አካላት ላይም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ #እርምጃ_የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

መንግስት በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ ናቸው #ባላቸው ግንባታዎች ላይ የማፍረስ #እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመረጋጋት ረገብ ብሏል። ከተማዋም ወደቀደመ #ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

በአሶሳ ወረዳ ከ190 በላይ የሚሆኑ የሚሊሺያ አባላት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ #ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸው ተገለፀ። ይህን ባደረጉ አመራሮች ላይም ህጋዊ #እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በክልሉ የሰላም ግንባታና የፀጥታ ቢሮ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊ አቶ #ደርጉ_ዚያድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ደረጃ የሚሊሺያ ሰራዊትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከሰሞኑ የሚሊሺያ ሰራዊት አባላት ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ለውጡን ማስቀጠል የሚችል የሚሊሺያ ሰራዊት መዋቅር ለመዘርጋት በሚያስችል መልኩ ግምገማ ተካሂዷል። በዚህም ከአሶሳ ወረዳ ብቻ 140 የሚሊሺያ አባላት በክብር ተሰናብተዋል። እንዲሁም ሰኔ 17 በአሶሳ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 9 የሚሊሺያ አባላት በህግ #ቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአሶሳ ወረዳ 190 የሚሆኑ የሚሊሺያ ሰራዊት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል ያሉት አቶ ደርጉ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ብለዋል። የክልሉን የሚሊሺያ ሰራዊት በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን አቶ ደርጉ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበበ የስራ ፍቃዳቸዉን ባላሳደሱ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ #እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበበ ከተማ ዉስጥ በ2011 የንግድ ፍቃዳቸዉን ማሳደስ የሚጠበቅባቸው 251 ሺ 6 መቶ የንግድ ተቋማት ቢኖሩም፣ ፍቃዳቸዉን እስከ ታህሳስ 30፣2011 ዓ.ም ድረስ ማደስ የቻሉት ግን ከ218ሺ አይበልጡም ተብሏል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዳንሻ ከተማ ወቅታዊ ሁኔታ‼️

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው #ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የትግራይ ክልል መንግሥት አስታውቋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ የትግራይ ክልል መንግስት ዐስታውቋል፡፡ የከተማዋ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሽከርካሪዎች ላይ እየወሰዱት ያለው #እርምጃ የተቃወሙ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተው እንደሰነበቱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ግጭቱ በመስጋት የዳንሻ ነዋሪዎች ከተማዋ ለቀው በአቅራብያቸው ወደሚገኙ አካባቢዎች #መሰደዳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ትግራይ ዞን ፀገዴ ወረዳ የምትገኘው ዳንሻ ከተማ ካሳለፍተው ሳምንት ጀምሮ ግጭት ስታስተናግድ ሰንብታለች፡፡ የአካባቢው ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች «ሕገ ወጥ» ያልዋቸው ሞተር ብስክሌቶችና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መያዝ መጀመራቸው ተከትሎ በተከሰተው አለመግባባት ወደ ሁከት ገብታ የሰነበተችው ዳንሻ ከረቡዕ የካቲት 20 ጀምሮ በከተማዋ በተስተዋለ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ከሞቱት በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች እየታከሙ መሆኑ ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ በፖሊስና እርምጃው በተቃወሙ ወጣቶች መካከል የተከሰተው ግጭቱ እየተባባሰ መቀጠሉ ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ዳንሻን እየለቀቁ መሆኑ ሰምተናል፡፡ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር የነበረው በድህንነት ስጋት ምክንያት ከተማዋ ለቆ አሁን ሑመራ እንዳለ የሚናገረው ፀሐዬ የተባለ አስተያየት ሰጪ በግል ንብረቱ ጨምሮ በብዙዎች ሀብት ላይ ውድመት መድረሱ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል፡፡

እንደ ጀርመን ራድዮ ምንጮች መረጃ ግጭቱ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ የከተማዋ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት አቋርጠው ሰንብተዋል፡፡ በከተማዋ ቅኝት ማድረጉ የሚናገረው ተመስገን ካሳሁን የተባለ የአይን እማኝ፡ ዳንሻ ዛሬ በአንፃራዊነት #ተረጋግታ ውላለች ብሏል፡፡ የተወሰነ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መመልከቱም ተናግሯል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግጭቱ ለማብረድ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ የትግራይ ልዩ ሐይል ፖሊሶች በቦታው #ተተክተዋል፡፡

የዳንሻን ጉዳይ አስመልክተን የተጠየቁት የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊዋ ወይዘሮ #ሊያ_ካሳ የክልሉ መንግስት ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተናግረዋል፡፡ ግጭት የፈጠሩ አካላትም "ሕግ የማስከበር ተግባር የማይዋጥላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው" ብለዋል፡፡ በከተማዋ ትራፋክ ተቆጣጣሪዎች የተወሰድ እርምጃ ክልል የለየ እንዳልሆነና ሕግ የማስከበር ተግባር ብቻ መሆኑ ሐላፊዋ ለጀርመን ራድዮ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኢትዮጵያ #የጥፋት ኃይሎች በስፋት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን የምዕራብ ኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በወሰደው #እርምጃ ማረጋጋት እንደተቻለ የኢፌዴሪ መከላከያ ምክትል ኢታማጆር ሹም ጀኔራል #ብርሃኑ_ጁላ ተናገሩ ። ዛሬ የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በአሶሳ ከተማ ገምገማ አካሂዷል። በግምገማው ወቅት ህብረተሰቡ ከነበረበት የሥጋት ስሜት ወጥቶ በአካባቢው #ሠላማዊ በሆነ መንገድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተገልጿል፤ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ይገባል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia