TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቆም ብለን …

በርካታ የአለም ሀገራት የማህበራዊ ሚዲያ ቴክኖሎጂን በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና በፖለታካዊ ዘርፎች ለተጎናጸፉት ውጤት ሁነኛ መሳሪያ አድርገው እየተጠቀሙበት ነው፡፡ በተቃራኒው ከነበሩበት የእድገት ሂደት እና ከሰላማዊ ህይወት አሽቆልቁለው ማንም አካል አትራፊ ወዳልሆነበት በእርስ በርስ #ጦርነት ሀገራቸውን #አፍርሰው ለዜጎቻቸው ሞት፣ በረሀብ አለንጋ መቀጣት፣ ለወረርሽኝና  ስደት መዳረግ እጣፈንታቸው እንዲሆን የጥላቻና የሀሰት መረጃዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ በተለያዩ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ይፋ እየተደረገ ነው፡፡

በሚወርድባቸው የከባድ ጦር መሳሪያ ወደ ፍርስራሽነት በመቀየር ላይ ያሉትና እስካሁን #መቋጫ መፍትሄ ያላገኘው የመካከለኛው መስርቅ የቅድመ ስልጣኔ ምድር የነበረችው ሀገረ #ሶሪያን እና ለኢትዮጵያ የቅርብ ጎረቤት በሚባል አቅራቢያ የምትገኘው #የመን በምሰሌነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያም ለዜጎቿ ህይወት የሚበጁ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ዘመኑ ከፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ ቴክኖሎጂ መጠቀም የምትችልበት ምቹ ሁኔታዎች እየሰፋ ቢመጡም በተቃራኒው በቴክኖሎጂው በሚሰራጩ የሀሰት ወሬዎች፣ ብሄርን ወይም  ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ የጥላቻ መረጃዎች ያለገደብ የሚለቀቅበት ሁኔታ አመዝኖ የስጋት ምንጭ  እየሆነ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያ የሆነ ቡድን ወይም አካል መነሻው ምን እንደሆነ ለማወቅ በሚያዳግት መልኩ በስሜታዊነት የሚፈረጅበት፣ የጥላቻ መረጃዎች  እየተፈበረኩ በተቀናበሩ ፎቶዎች የሚቀርብበት፣ በሀገሪቱ ለረጅም ጊዜያት ጸንተው ለነበሩ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶችን ለሚንዱ የጥላቻ መረጃዎች መጫዎቻ ሜዳ ሲሆን ይስተዋላል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ባሉ የሀሰትና የጥላቻ መረጃዎች በሀሪቱ ላይ እየፈጠሩ ባለው ችግርና መፍትሄው ላይ  ውይይት ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይም ሀገራችን ከማህበራዊ ሚዲያ ምን አተረፈች? በማለት በጥያቄ ሀሳባቸውን ማካፈል የጀምሩት በቀድሞው የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ  ቡድን መሪ  አቶ በቀለ እውነቱ በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ከሚሰጡት ጠቀሜታ ይልቅ  ጉዳቱ እየበዛ  ነው ያሉት፡፡

ለመልካም ነገር የተጠቀሙ የአለም ሀገራት ፈለግ በመከተል ቢሰራበት በርካታ  ተግባራትን  በቀላሉ ለመከውንና አማራጭ  የመሆን  አቅም ያለው  ቴክኖሎጂ ነው ያሉት አቶ በቀለ “እኛም እያደረሰ ያለውን ጉዳት በመቀነስ እውቀት ለሚጨምሩና ኑሮን ለሚያቀሉ ተግባራት ማዋል ላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል’’ ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ ሚዲያውን እየተጠቀመ ያለው ቢያንስ መጻፍና ማንበብ የሚችል የህብረተሰብ ክፍል ነው የሚሉት ባለሙያው መረጃን በመመልከትም ሆነ ሀሳቡን  ተቃውሞና ደግፎ የሚሳተፈው አካል ለበጎ ተግባር የመጠቀም ሂደት ገና አልዳበረም በማለትም  ትዝብታቸውን ገልጸዋል፡፡

በማህበራዊ ገጾች የሚተላለፉ መረጃዎችን የማመዛዘን አቅም ማዳበር ይጠይቃል  የሚሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አቢዮት ባዬ፤ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 17 ሚሊዮን ባላይ መድረሱንም ጠቁመዋል፡፡

ቀደም ሲል ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ባለመረጋገጡ ሰዎች በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ባህል እንዲዳብርና መብት እንዲከበር ማንነታቸውን በመደበቅ በስውር የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከፍተው ለዴሞክራሲ መጎልበት የሚሰሩበት ወቅት እንደነበር ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

ከሞላ ጎደል ነገሮች በተስተካከሉበት በአሁኑ ወቅት ሀሳብን በነጻነት ለመግልጽ ምቹ በሆነት ዘመን በተቃራኒው ሀሰተኛ መረጃዎችን አቀናብሮ በማሰራጨት ዴሞክራሲን የሚያቀጭጭ፣ ብሄርን ከብሄር ወይም በሃይማኖቶች መካካል ቅራኔና ግጭት ለመፍጠር እየተሰራ ይታያል ይላሉ። ለሀገር ሰላምና አንድነትም ስጋት እየሆነ ይገኛል ነው ብለዋል፡፡

ሀሰተኛ ወሬዎችን እያጋነነ የሚያሰራጨው አካል ምን ፍላጎት ቢኖረው ነው? ለምን ይነግረኛል? ብሎ እራስን በመጠይቅና መረጃውን ከሌሎች ታማኝ ምንጮች በማጣራት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ነው ዶከትር አቢዮት  የገለጹት፡፡

የጥላቻ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት አላማቸው ለበርካታ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚዎች መልእከታቸውን መበተን በመሆኑ ሀሳቡን ደግፎ ወይም ተቃውሞ ምላሽ ባለመስጠት የድርጊቱ ፈጻሚዎችን አንድም እራሳቸውን ከሀሰት መረጃ እንዲያርሙ ወይም የተከታይነት ተጽኖ ማመናመን እንደሚገባም ባለሙያው መክረዋል፡፡

በሌላ ሰው ወይም ተቋም ስም ሀሰተኛ የማህበራዊ ገጽ በመክፈት የፈጠራ ወሬን ተዓማኒነት በሌላቸው ፎቶዎች በማቀናበር ሀገርንና ዜጎችን አደጋ ላይ የሚጥል መረጃዎችን የሚያስተላልፉ አካላትን ለማስቆም እንደሀገር ቆም ብለን ማሰብ አያስፍልገንም? በማለት ሀሳባቸውን በጥያቄ ያነሱት የሀይማኖት አባት ሀጂተሸለ ኪሮ እንዳሉት ወጣቱ ትውልድ የሀገሩን አንድነትና ሰላም አስጠብቆ ማስቀጠል አለበት ፡፡

“ማህበራዊ ሚዲያ በብሄሮችና በሃይማኖቶች መካካል የጥላቻ ወሬ መርጨት  ብቻ አይደለም” የሚሉት ሌላው  የሃይማኖት አባት አባ መላከሂወት ወልደየሱስ  በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ ጭምር የአሉባልታና የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት የመተማመንና የመከባበር  ባህልን እየሸረሸረ ነው ብለዋል፡፡

በርካታ የመረጃ አማራጮች መኖር መልካም አጋጣሚ መሆኑን የነገሩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት መምህር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ፤ መረጃዎች ሁሉ እውነተኛና ጠቃሚ ባለመሆናቸው ተፈትሸውና ተለይተው መወሰድ እዳለባቸው ይመክራሉ፡፡

“በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ የሚቀርቡ መረጃዎች፤ የበሰለ የፖለቲካ ሀሰብን ከማቅረብ ይልቅ የአንድ ግለሰብን ወይም ቡድንን ስሜትና የጥላቻ መረጃ የሚቀርቡበት ሜዳ ሆኗል” የሚሉት ዶክተር ጌታቸው ህብረተሰቡ ስጋቱን እየተረዳው መምጣቱን ነው የተናገሩት።

መደበኛ የመገናኛ ብዙሃን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መሻሻሎችና አማራጭ የህዝብ የመረጃ ምንጭ እየሆነ ቢመጣም ለበርካታ አመታት “ለገዢው ሃይል  የሚዘምር” ነበር ይላሉ።

ዶክተር ጌታቸው እንደሚሉት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለህብረተሰቡ የማስተማር፤ በቁጥር እያደገ በመጣው የኤፍ ኤምና ቴሌቭዥን መገናኛ ዘዴዎች መንግስት መረጃዎችን በፍጥነት መስጠትን በመፍትሄነት መጠቀም ግድ ይላል። ማንነቱን ያልገለጸ አካልን ጓደኛ ማድረግም ሆን መከትል እንደማያስፍልግም በማስረዳት፡፡

የድሬ ትዩብ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም ነገሰ  ፌስ ቡክ የመጠቀሚያ ቴክኖሎጂውን በየጊዜው ይበልጥ ቀላልና ባለብዙ አማራጭ እያደረገው መምጣቱ በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን አደጋ ያባብሰዋል የሚል ስጋት ነው ብለዋል።

አቶ ቢኒያም  “በድሬ ትዩብ ስም በተከፈት የሀሰተኛ  ገጽ ላይ በተለቀቀ የአንድ ድርጅት ስም ማጥፋት መረጃ እኛን ጥፋተኛ ሊያደርግ የነበረን ድርጊት የፌስቡክ ባለቤት ጋር በአካል በመሄድ ሀሰተኛ መሆኑን በማስረዳት የኛን ትክክለኛ ገጽ በማረጋገጥ ከችግሩ ዳን” በማለት በተሞክሮነት አንስተዋል፡፡

አሁን በሀገሪቱ  በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት ጥናት ላይ የተመሰረትና ቴክኖሎጂውን በአግባቡ በመጠቀም ብሎም ውጤት ካስመዘገቡ  ሀገራ ተሞክሮ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡

የጥላቻ ሀሳቦችን የሚያንጸባርቁ  ገጾችን የሚከላከል አንድ ተቋም በማቋቋምና በቂ እውቀት ያላቸው ባለሞያዎችን መድቦ መስራት ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ፌስቡክ በአፍሪካ ያለውን አገልግሎት
"ለኢትዮጵያውያን #ከሶሪያ የተላኩ መልእክተኞች"!

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሶሪያ ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ #ምፅዋት ሲለምኑ የሚያሳይ ምስል በብዛት እየተሰራጨና share እየተደረገ ይገኛል።

አዎን ቢገባን ብናስተውለው እነዚህ ሶሪያኖች እኛ ሐገር የተላኩት ከፈጣሪ መልእክተኛ ሆነው ነው። አሁንም ልብ ካልገዛን፣ ጥላቻን ትተን ይቅርታን ካልተላበስን፣ መለያዬትን ትተን አንድነትን ካልያዝን፣ የጦርነት አታሞ/ ከበሮ መደለቅ ካላቆምን እንደ እነዚህ ሶሪያኖች ትሆናላችሁ ተጠንቀቁ ሲል ነው የላከልን፤ ከእንግዲህ መለያየትን፣ ዘረኝነትን የምትሰብኩ የጦርነት ነጋሪን የምትጎስሙ #ጦርነት ናፋቂዎችና እነሱን ተከትላችሁ የምታብዱ ተከታዮቻቸው ፈጣሪ ከዚህ በላይ ወርዶ አይነግራችሁምና ልብ ግዙ።

አንደበታችሁ ሰላምን ያውራ፣ እግራችሁ ወደ ጥፋት ሳይሆን ወደ ሰላም መንገድ ያቅኑ፣ እጆቻችሁ የመሳሪያ ቃታን ሳይሆን በሐሳብ የምታሸንፉበት እስክርቢቶን ይያዙ። ኢትዮጵያ ፈርሳ ላትፈርስ ተለያይተን ላንለያይ ትዝብት ላይ አትውደቁ። ጉልበታችሁንም አትጨርሱ።

©Kibrom Adhanom Ghebreyesus
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይሄ ፊልም አይደለም!! የግጭት እና የጦርነት ውጤት መሬት ላይ ያለው እውነታ ነው!! ጦርነት እና ግጭት #ፌስቡክ ላይ #ተዘፍዝፎ እንደመለፍለፍ ቀላል ከመሰለህ ሶሪያ፣ የመን፣ ደቡብ ሱዳን ጎራ በል በጥይት ድምፅ ስትሳቀቅ፤ ያቀረብከውን ምግብ ለመብላት ሲያቅትህ፤ ብር ኖሮህ ምግብ ለመግዛት ከቤትህ ለመውጣት ሲከብድህ፤ መብራቱና ኔትዎርኩ ተቋርጦ ጨለማ ውስጥ ስትቀመጥ ያኔ #ግጭት እና #ጦርነት ትርፉ ምን እንደሆነ ይገባሃል!!
.
.
#ሰላም_ብቻዋን_ታዋጣለች!!
#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈጣሪ ያውቃል⁉️

በረሐ እና ባሕር አቋርጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚተሙት ኢትዮጵያውያን በየመን ጦርነት እንዳለ እንኳ አያውቁም። አንድ ወደ #ጅቡቲ የተሰደደ #የመናዊ በመንገድ ያገኟቸውን ኢትዮጵያውያን «ወዴት ነው የምትሔዱት? በመንገዳችሁ ጦርነት አለ ስንላቸው ፈጣሪ ያውቃል» የሚል መልስ ሰጡን ሲል ለኢኤንኤን ተናግሯል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ድረ-ገፅ እደሚጠቁመው በየመን የርስ በርስ #ጦርነት

•5,900+ ሰላማዊ ሰዎች #ተገድለዋል

•9,400+ ሰላማዊ ሰዎች #ቆስለዋል

•3 ሚሊዮን ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል

•22.2 ሚሊዮን ሕይወታቸውን ለማቆየት የለት ደራሽ ዕርዳታ #ጥገኛ ናቸው

•2.5 ሚሊዮን ሕፃናት ከትምህርት ገበታ እርቀዋል፤ ቢሆንም #ኢትዮጵያውያኑ ፈጣሪ ያውቃል እያሉ መንገድ ላይ ናቸው።

Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌስቡክ ጦረኞች...

#የቃላት_ጦርነትና እስጥ አገባ ከሮና ገሮ ሲያበቃና ሲበጠስ ነው ሀገራት ወደ #ጦርነት ውስጥ የሚገቡት፡፡ ለዚህም ይመስላል የቻይናው ከሚኒስት መሪ የነበሩት ማኦ ዜዱንግ ጦርነት የፖለቲካ ትግሉ በሌላ መልኩ ቀጣይነት ነው ያሉት፡፡ ማሕበራዊ ድረገጾች ከፍተኛ የኃሳብ ፍልሚያ የሚካሄድባቸው ከጦርነት ያልተናነሱ አውድማዎች ናቸው፡፡ የማሕበራዊው ሚዲያ ጥይት ባይጮህበትም ከመድፍና ታንክ በላይ #በሰው_ሕሊና ውስጥ የሚያጓራ ከሚሳኤልም በላይ ተምዘግዝጎ የሚወነጨፍ፣ የሚጮህና አናዋጭ፤ በስሜታዊነት የሚነዳ ለጥፋትም የሚያነሳሳ ነው፡፡ #ፌስቡክ የኃሳብ ፍልሚያና ግብግብ የሚካሄድበት ጎራ መሆኑ በጀ እንጂ ሌላማ ቢሆን የከፋ እልቂትና ውድመት ሊያመጣ ይችል የነበረ የዘመኑ ሚዲያ ነው፡፡

ሙሉውን ፅሁፍ ያንብቡ👇

https://telegra.ph/የፌስቡክ-ጦረኞች-03-04