TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ግብፅ‼️

ግብፅ ከ5 ሺህ በላይ ተከታይ ያላቸው እና #የሀገር_ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ይዘቶችን የሚያሰራጩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲዘጉ የሚያስችል ህግ ይፋ አደረገች፡፡

የግብፅ የመገናኛ ብዙሃንን የሚቆጣጠረው አካል ይፋ ያደረገው ይህ አሰራር በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ከፍተኛ የሆነ ገደብ እንዳላው ነው የተነገረው፡፡

አዲሱ ህግ የሀገሪቱ ከፍተኛው የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ አካል ሀሰተኛ ዜናዎችን የሚያሰራጩ አካላትን ለማገድ እንደሚያሰችለውና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከ 14 ሺህ 400 ዶላር ቅጣት ለመጣል እንደሚያስችለው ተነግሯል፡፡

ይህ አዲስ አሰራር በትናንትናው ዕለት ተግባራዊ መደረግ የጀመረ ሲሆን፥ እርምጃው የኤል ሲ ሲ አስተዳደር ተቃዋሚዎችን ለመቆጣጠር እንደሚያስችለው ተጠቁሟል፡፡

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ግብፅ በመገናኛ ብዙሃን እና ጋዜጠኞች ላይ የወሰደቸው እርምጃ መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፥ በዚህም በርካታ ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

እርምጃው ኢ ህገ መንግስታዊ ነው ያሉት የግብፅ አንጋፋ ጋዜጠኞች የመገናኛ ብዙሃንን ነፃነት በመጋፋት የመንግስት ባለስልጣናት በመገናኛ ብዙሃንን ቁጥጥር እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የሀገሪቱ ከፍተኛው የሚዲያ ተቆጣጣሪ አካል ሃላፊ ሙሃመድ አህመድ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ጋንታ አፈሹም ወረዳ  አዘባ ጣቢያ  በተባለ ቦታ በትናትናው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት፡፡

በዚህ የትራፊክ አደጋ በ15 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በአዲግራት ሆስፒታል የህክማና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡

በዚህ አደጋ ሁለት ህፃናት ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው እንደተረፉ የተነገረ ሲሆን በአሁን ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

አደጋው ያጋጠመው የህዝብ ማመላሻ አውሮቶብስ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲግራት ከተማ ወደ አዘባ ጣቢያ በሚጓበት ወቅት ገደል ውስጥ በመግባቱ እንዳጋጠመ የወረዳው የትራፊክ ፓሊስ አስተባባሪ ዋና ሳጅን #ርግበ_ገብረትንሳኤ ለfbcአስታውቀዋል፡፡

የአደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የትራፊክ ፓሊስ አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ🛬አቡዳቢ🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አቡዳቢ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቡዳቢ ሲደርሱ የአቡዳቢ ልዑል ሼክ ሞሃመድ ቢንዛይድ እና ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካ መንግሥት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ለመብረር እንዴት ፈቃድ እንዳገኘ #እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አፄ ቴዎድሮስ‼️

ብሪታንያ ከዛሬ 150 ዓመት በፊት ከንጉሰ ነገስት አጼ ቴዎድሮስ አስከሬን ላይ የተወሰደውን #ፀጉራቸውን ዛሬ ለኢትዮጵያ ታስረክባለች። ቅርሱን ለመረከብ የኢትዮጵያ የባህል የቱሪዝም እና የወጣቶች ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሳ ለንደን ናቸው። የርክክብ ሥነ-ስርዓቱም ዛሬ ማምሻውን ርዕሰ ከተማ ለንደን በሚገኘው የብሪታንያ ብሔራዊ የጦር ቤተ-መዘክር እንደሚካሄድ DW ዘግቧል።

በዚሁ ሥነ-ስርዓት ላይ በቅርቡ የተሾሙት በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሀ ሻውል ፣ብሪታንያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዶክተር ኂሩት በለንደን ቆይታቸው 300 የሚሆኑ የኢትዮጵያ የጽሁፍ ቅርሶች የሚገኙበትን የብሪታንያ ብሔራዊ የመጻህፍት ቤተ-መዘክር ገብኝተዋል። በዚሁ ወቅት ከቤተ- መዘክሩ ጋር የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙት ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ ቅርስ የሆኑት እነዚህ ጽሁፎች ወደመጡበት ወደ ኢትዮጲያ እንዲመለሱ በይፋ ጠይቀዋል።

የዛሬ 151 ዓመት ብሪታንያ አጼ ቴዎድሮስ ያሰሩዋቸውን ሚስዮናውያን እና የብሪታንያ ተወካዮችን ለማስለቀቅ ዘመቻ በከፈተችበት ወቅት የኢትዮጵያ ሐብት ተመዝብሯል። ያኔ በሽጉጣታቸው የራሳቸውን ህይወት ያጠፉትን የአጼ ቴዎድሮስን ፀጉር ጨምሮ ልይ ልዩ የኢትዮጵያ ቅርሶችና ሀብቶች ተዘርፈው ወደ ብሪታኒያ ተወስደዋል። ብሪታንያ የተወሰደው የንጉሠ-ነገሥቱ ልጅ ልዑል ዓለማየሁም እዚያው ተቀብሯል። የልዑሉን አጽም እና የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ ጥረት ከተጀመረ ቆይቷል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ለንደን የሚገኘውን የብሪታንያ ብሔራዊ ቤተመዘክር ጎብኝቷል። በጉብኝታቸው ወቅትም በቤተ መዘክሩ ስለ ሚገኙት የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ቅርሳ ቅርሶች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ፎቶ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በረከት ስምዖንና ታደሠ ካሳ ዛሬ በባሕር ዳር ዙሪያ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስም ነገ አቶ ታደሠን ጨምሮ በ9 ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ሌላ ክስ እመሰርታለሁ ብሏል፡፡ ቀደም ሲል በተፈቀዱለት ቀናትም ከሀገር ውስጥና ከውጭ የምስክሮችን ቃል መቀበሉንና ሰነዶችን መመርመሩን አስረድቷል፡፡ ሆኖም የዳሽን ቢራ አክሲዮን ሽያጭ ላይ የክልሉ ኦዲተር ሥራ ስላላጠናቀቀ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ግን በጥር 17ቱ ችሎት ኦዲቱ 90 በመቶ ተጠናቋል ስለተባለ ድጋሚ ተጨማሪ ጊዜ እንዳይሰጥ ቢጠይቁም ችሎቱ 8 ቀን ፈቅዷል፡፡ ተከሳሾቹ ጠበቃ ማቆም አልቻልንም በማለታቸው መብታቸው ይከበር ሲል ማዘዙን የአማራ መገናኛ ብዙኻን ዘግቧል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ያልፈረሰ ልብ ሲኖርህ በፈረሰ ከተማ ላይ አበባ ትተክላለህ፤ የፈረሰ ልብ ሲኖርህ ያልፈረሰ ከተማን ለማፍረስ በዘርና ሃይማኖት ተቧድነህ ለጦርነት ታሟሙቃለህ።

#AbrahamYeTsigeLij

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሼር #share
(ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ)

መርፌ ዓይናማ ናት ባለ ስለት ችግሩ የፊቷን እንጂ የሚከተላትን አታይም፤ እናም ጨርቅ ላይ እሷ አለፍኩ ብላ የክርና የገመድ መዓት ታስገባበታለች፡፡ የእኛ ሀገር አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ጦማሪዎችም ልክ እንደ መርፌዋ ናቸው።

እነርሱ ሀገር በሚወጋ መርፌያቸው እየወጉን ሲጓዙ እንደ ክር አያሌዎች መድረሻቸውን ሳይጠይቁ ይከተሏቸዋል።

ድረ ገጻቸውን የሚያነብላቸው ተከታታይና ደጋፊ ማብዛታቸውን እንጂ ሀገርና ሕዝብ ላይ እየተከሉ ያሉትን አደጋ፣ እየረጩት ያለውን መርዝ ሊያዩት አልቻሉም።

ባለፉት ጥቂት ወራት ሀገራችን ያስመዘገበቻቸውን የድል ስኬቶች በመዘርዘርና ከእርሱም ትይዩ የገባችበትን የፖለቲካ ቀውስ ለእናንተ በማስታወስ ጊዜአችሁን ማባከን ኣይገባም፡፡ አሁን ያለው ትልቁ ቁም ነገር ከዚህ ከገባንበት አሳሳቢ ቀውስ ራሳችንንም፣ ሀገራችንንም እንዴት እናውጣት የሚለው ነው።

ሁለት የገመድ ጽንፎችን ይዘው የቆሙ ኃያላን በሚያደርጉት ጉተታ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን አደገኛ ውጥረት ውስጥ የከተቱበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

ልበ ሥውር ሆኖ ግራና ቀኝን በጥሞና ማስተዋል በተሳነው ጽንፈኛ ቡድን የሀገራችን አየር ምድሯ ሰላምና ተስፋን ከመተንፈስ ይልቅ የስጋትና የውድመት ደመናን አርግዞ የመከራ ዶፉን ሊጥል ከአናታችን በላይ መጣሁ መጣሁ ይላል።
መካረር እዚህም እዚያም በርትቷል፡፡ ተፈጥሮ ነውና የተወጠረና የተካረረ ጉዳይ ቆይቶ መበጠሱ አይቀርም፡፡

“የማን ቤት ጠፍቶ ፣የማን ሊበጅ ፣ ያውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ” የሚለው የሽፍቶች ፈሊጥ እንጂ የሰላማዊ ዜጎች መመሪያ አይደለም።

በእውነት ኢትዮጵያዊነት የሚፈተንበት ወቅት እየመጣ ነው፤ ማንም ጣፋጭ ዘርና ፍሬ ነኝ ብሎ ሊኮራና ሊመጻደቅ የሚችለው የግንዱ ሥር እስካለ ብቻ ነው፡፡ የግንዱን ሥር ቆርጦና ነቅሎ በቅርንጫፉና በዘሩ መኩራት የሞኝ ጨዋታ ይሆናል።

በውስጣችን አንጠፍጥፈን ያላወጣነው ዐቅም፣ ያልተጠቀምንበት ችሎታ ካለ፣ እርሱን ኢትዮጵያን ለማዳንና ለመገንባት እንጂ በማኅበራዊ ሚዲያ ዐውደ ውጊያ ሀገር ለማተራመስ ልናውለው አይገባንም ነበር።

ሥልጣኔ ሕዝብን በዕውቀት መክበብ እንጂ በሐሰት መረጃ ማጨናነቅ አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ኃላፊነታቸው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን መታደግ ነው፡፡ በጣም ጥቂት ለሆኑና ጊዜያዊ ጥቅም ለሚያስገኙ የፖለቲካ ቡድንተኞች አለበለዚያም የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታይና ደጋፊን ማስደሰትና ማስፈንደቅ አይደለም።

ኢትዮጵያዊነት ለኢትዮጵያ መሥራት፣ ኢትዮጵያን ማስደሰት እንጂ ኢትዮጵያን በሐሰት መረጃዎች ማሸበር አይደለም፡፡ ሊሆንም አይገባም።

በዘመናት ውስጥ የሀገራችንን ህልውና የሚፈታተኑ አያሌ ፈተናዎች ገጥመውን ያውቃሉ፡፡ ነገራችን ቀጥኖ የሚበጠስ የሚመስልበትም ጊዜ ታልፏል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ምንም ብትቀጥን ጠጅ ናት በእንግዳ ደራሽ በውኃ ፈሳሽ የምትፈርስ አይደለችም።

በማኅበራዊ ሚዲያ በጣም የበዙ የሐሰት መረጃዎች ይተላለፋሉ፤ ሐሰት ጮኾ ስለተነገረ፣ ጎልቶ ስለተጻፈ፣ በብዙ ሰዎች ስለ ተደገፈ ወይም በታዋቂ ሰዎች ስለተወራ እውነት አይሆንም፡፡ ኢትዮጵያ ግን የዘላለም እውነት ነች።

በሐሰት ዜናም ሆነ በአሉባልታ የማትፈርስ ጽኑዕ መሠረት ያላት እውነት ናት፡፡ ታሪክ ወለል አድርጎ እንደሚያረጋግጥልን ሐሳውያን እንጂ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከንቱ ሆነው አያውቁም።

ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን እንጂ ለአንዱ እሥር ቤት ለሌላው ቤት አይደለችም፡፡ እገሌ የዚህ ወይም የዚያ ማኅበረሰብ አባል ስለሆነ በተለየ መልክ ተጠቃሚ ወይም ተጎጂ መሆን አለበት ብሎ የሚያስብ ካለ እርሱ የምናሳክመው እንጂ የምንከተለው አይደለም።

የትም እንወለድ፣ የየትኛውም ብሔር አባል እንሁን፣ ኢትዮጵያ ሁላችንንም በእኩልነት ማገልገል አለባት፡፡ ይህ፣ አቋማችን ነበር፤ አሁንም በጽኑ እናምንበታለን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!"
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መጋቢት 10፣ 2011 ዓ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዓፄ ቴዎድሮስ የራስ ፀጉር በአሁኑ ሰዓት በይፋ ለኢትዮጵያ ተላልፎ እየተሰጠ ነው!

Via Petros Ashenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
National Steering Comitte_20-3-2019.pdf
496.4 KB
በፌዴራል ደረጃ የተቋቋመው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ በመጪው ወር የሚካሄደው የመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ያደረገው ውይይት፦

Via የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር (ለTIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia