TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጨማሪ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ስለተከሰከሰው ቦይንግ 737 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለጋዜጠኞች መግለጫ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡

በመግለጫው አውሮፕላኑን ሲያበር የነበረው ከ8 ሺህ ሰአታት በላይ የማብረር ልምድ ያለውና ጥሩ የበረራ ሪከርድ የነበረው ካፒቴን #ያሬድ_ጌታቸው ሲሆን ግማሽ ኢትዮጵያዊና በግማሽ ኬኒያዊ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ረዳት አብራሪው #አህመድ_ኑር_መሀመድ ኑር የሚባል ከ200 ሰአት በላይ የበረራ ልምድ ያለው አብራሪ ነበር፡፡

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገለፃ አውሮፕላኑ ከተገዛ ገና 4 ወራትን ያስቆጠረና ምንም አይነች ችግር ያልነበረው ንፁህ አውሮፕላን ነበር፡፡
በተከሰከሰው አውሮፕላን ላይ የነበሩ 149 መንገደኞች እና 8 የበረራ አስተናባሪዎች ዜግነታቸው ተለይቷል፡፡

በአውሮፕላኑ ላይ 32 ኬኒያውያን፣18 ካናዳዊያን፣ 9 ኢትዮጵያውያን፣ 8 ጣልያውያን፣ 8 ቻይናዊያን፣ 8 አሜሪካውያን፣ 7 እንግሊዛውያን፣ 7 ፈረንሳውያን፣ 6 ግብፃውያን፣ 5 ጀርመናውያን ሲሆኑ ከ5 የኔዘርላንዳውያን ውስጥ 4ቱ የተባበሩት መንግስታት ፓስፖት የያዙ መንገደኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡

4 ህንዳውያን፣ 4 የስሎቫኪያ ዜጎች፣ 3 የኦስትሪያ ዜጎች፣ 3 ስዊድናውያን፣ 3 የራሻውያን፣ 2 የሞሮኮ ዜጎች፣ 2 የስፔናውያን፣ 2 ፖላንዳውያን፣ 2 እስራኤላውያን፣ 1 የቤልጄማዊ፣ 1 ኢንዶነዌዥያዊ፣ 1 ኡጋንዳዊ፣ 1 የመናዊ፣ 1 ሱዳናዊ፣ 1 ሰርቢያዊ፣ 1 ቶጓዊ፣ 1 ኔፓል፣ 1 ናይጄሪያዊ፣ 1 ሞዛንቢካዊ ዜጋ፣ 1 ሩዋንዳዊ፣ 1 ሶማሊያዊ፣ 1 ኖርዌያዊ፣ 1 የጅቡቲ ዜጋ፣ 1 አየርላንዳዊ እና 1 የሳኡዲ ዜጋ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia