#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን አካዳሚ ለሦስት ዓመታት ያሰለጠናቸውን 559 ተማሪዎችን #በማስመረቅ ላይ ይገኛል። በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ #ተወልደ_ገብረማርያም ተገኝተዋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 40ዎቹ ፓይለቶች፣ 58 ቴክኒሻን እና 123ቱ ደግሞ ሆስተስ ናቸው። እንዲሁም 286 የሚሆኑት ደግሞ የማርኬቲንግ ባለሙያዎች ሲሆኑ 52 የሚሆኑት ደግሞ የምግብ ዝግጅት ባለሙያ ናቸው ተብሏል።
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ❓
ያለምንም መፈናቀል ለ800ሺ ዜጎች መኖሪያ ቤት መስራት የሚያስችለው ጥናት #አልተተገበረም ተባለ።
https://telegra.ph/ያለምንም-መፈናቀል-ለ800ሺ-ዜጎች-መኖሪያ-ቤት-መስራት-የሚያስችለው-ጥናት-አልተተገበረም-03-09

Telegraph
ያለምንም መፈናቀል ለ800ሺ ዜጎች መኖሪያ ቤት መስራት የሚያስችለው ጥናት አልተተገበረም
አዲስ አበባ፡- በፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2009 ዓ.ም የተሰራውና በአዲስ አበባ ከተማ ምንም አይነት ሰው ሳይፈናቀል፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሳይፈጠር መኖሪያ ቤት መስራት የሚያስችለው ጥናት እስካሁን ተግባራዊ አለመሆኑን ተገለፀ፡፡ በአስተዳደሩ የመሬት ልማትና ከተማ አስተዳደር ኤጀንሲም ጥናቱን አላውቀውም ግን የራሴን አዲስ ጥናት እያጠናሁ ነው ብሏል፡፡ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት…
ባህር ዳር ማረሚያ ቤት‼️
#በባሕር_ዳር ማረሚያ ቤት በተከሰተ የፀጥታ ችግር የሰው ሕይወት ማለፉንና ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ውብሸት መኮንን ለአብመድ እንደተናገሩት የፀጥታ ችግሩ የተከሰተው ትናንት ከቀኑ 7፡00 አካባቢ ነው፤ የችግሩ ምክንያት ደግሞ ‹‹አደንዛዥ ዕፅ እና ሞባይል ወደ ማረሚያ ቤቱ ገብቷል›› የሚል ጥቆማ ለማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች ደርሷቸው ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ታራሚዎች ውስጥ ለፍተሻ በገቡበት ወቅት የማፈን ሙከራ በመደረጉ ነው፡፡
ወደ ታራሚዎች የገቡትን 6 የፖሊስ አባላትን ለማፈን ጥረት መደረጉና አምስቱ ከመታፈን ማምለጣቸውን የገለጹት ኃላፊ ‹‹አንደኛው የፖሊስ አባል ግን በታራሚዎች በመታፈኑ እንዲለቁት ድርድር ቢደረግም ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ይህንን ተከትሎ ታራሚዎች ወደ ፖሊሶች ድንጋይ መወርወር እና ጉዳት ማድረስ በመጀመራቸው የአድማ ብተና ፖሊሶችን እገዛ በመጠየቅ በአስለቃሽ ጋዝ ለማስለቀቅ እና ለማረጋጋት ጥረት ተደርጎ ነበር›› ብለዋል ኮማንደር ውብሸት፡፡
በአመፁ ‹‹አንሳተፍም›› ያሉትን ታራሚዎች አመፅ ቀስቃሾቹ ጉዳት እንዳደረሱባቸውም ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡ እስከዛሬ ጥዋት ባለው መረጃም የአራት ታራሚዎች ሕይወት ማለፉን ኮማንደሩ አረጋግጠዋል፡፡ በመጨረሻም ታፍኖ የነበረው አንድ አባል ትናንት ተለቅቋል፡፡
ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ታራሚዎች ቁጥር በውል ባይታወቅም ከ20 እንደሚበልጡም የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡ ተጎጅዎቹ በፈለገ ሕይወት እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ነግረውናል፡፡
ምንጭ:- አብመድ

#update በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአዲስ አበባ ከተማ መካከል ያለውን የአስተዳደር ወሰን ውዝግብ በተመለከተ ዘላቂ መፍትሄ የሚያስቀምጥ ኮሚቴ ተቋቋመ።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ፦
በከተማችን ሀዋሳ ከየካቲት 28 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ውይይት እንድቋረጥ ተደርጓል።
ውይይቱ የተቋረጠበት ዋናው ምክንያት ለውይይቱ በቀረበው ሰነድ ውስጥ የተካተቱ አንዳንድ ነጥቦች የሲዳማን ብሄር ህገ መንግስታዊ መብቶችን የምጻረሩ እንደሆኑ በመረዳት የብሄሩ ተወላጅ የሆኑ አመራር በሙሉ የቀረበው ሰነድ ለውይይት የማይጋብዝ እንደሆነ አቋም በመያዝ ከስብሰባው ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ በ29/06/2011 ዓ/ም; አጠቃላይ ክልላዊ መድረኩን ለማስኬድ ምቹ ሁኔታ ስላልነበረ መድረኩ ሊቋረጥ ችሏል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በዕለቱ በከተማው የሚገኙ የሲዳማ ብሄር ወጣቶች በዲርጊቱ ላይ ስሜታቸውን ከገለጹ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደየቤታቸው ተመልሷል።
በአሁኑ ሰአትም በከተማው የሚገኝ ህብረተሰብ ያለምንም የጸጥታ ስጋት የዘወትር ተግባር በአግባቡ በማከናወን ላይ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ህብረተሰቡን እንዳይረጋጋ ለማድረግ አቅደው የሚሰሩ አንዳንድ ሚድያዎች እና በግለሰብ ደረጃ በማህበራዊ ገጾች ላይ አፍራሽ መልዕክቶች እየተለቀቁ ስለሚገኙ ህብረተሰቡ በዚህ ሳይሸበር የዘወትር ተግባሩን እንዲያከናውን ከተማ አስተዳደሩ ጥርውን ያቀርባል።
(ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመ.ኮሙ.)

ወንጀል ነክ መረጃ‼️
በሞያሌ ከተማ በጦር መሳሪያ በመታገዝ ከባድ የሰው #መግደል ሙከራና ግድያ የፈፀሙ ግለሰቦች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተ።
1ኛ ተከሳሽ ወታደር ማትያስ ሞጉሬ እና ሌሎች 5 ተከሳሾች በወንጅል ሕጉ አንቀጽ 27(1)፣32(1)(ለ) እና 539 (1) (ሀ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ሰውን ለመግደል በማሰብ መጋቢት 01 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት ሲሆን በሞያሌ ከተማ ልዩ ቦታው ሸዋ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በክስ መዝገቡ የተጠቀሰው 3ኛ ተከሳሽ ኮ/ል አብርሃ አረጋይ ማንኛውንም ጸጉረ ልውጥ ሰዎችን ተኩስ እና ግድሉ በማለት፣ ለ2ኛ ተከሳሽ አስር አለቃ ሀብታሙ ተገኝ፣ ለ4ኛ ተከሳሽ ወታደርር አብዱልፈታህ ዱቦ ለ5ኛ ተከሳሽ አስር አለቃ ስለሺ ሽናሞ እና ለ6ኛ ተከሳሽ አስር አለቃ አስደናቂ ወረና ትዕዛዝ በመስጠት ተከሳሾች በተለያዩ ሰዎች ላይ በክላሽ ጠመንጃ ጥይት በመተኮስ የአካል ጉዳት፣ የግድያ ሙከራና የግድያ ወንጅል በመፈፀማቸው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የካቲት 28 ቀን 2011ዓ.ም በአንድ መዝገብ በ6ቱ ተከሳሾች ላይ 15 ክስችን መስርቷል፡፡
ተከሳሾች በመከላከያ እስር ቤት ለ 9ወራት በምርመራ ላይ ቆይተው ከወርሃ ጥቅምት2011 ዓ.ም ጀምሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቆይተዋል፡፡
አቃቤ ህግም በ1ኛ ተከሳሽ ላይ በሁለት የግድያ ሙከራና በአንድ ከባድ ግድያ፣ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ በ3 ከባድ ግድያ በ1 ከባድ የግድያ ሙከራ፣ በሶስተኛ ተከሳሽ ላይ በ4 ከባድ የግድያ ሙከራ በ6 ከባድ ግድያዎች በ4 ተከሳሽ በአንድ ከባድ ግድያ በአንድ ከባድ ግድያ ሙከራ በ5 ተከሳሽ በ2 ከባድ የግድያ ሙከራና በ3 ከባድ ግድያ በ6 ተከሳሽ ላይ በአንድ ከባድ የግድያ ሙከራና በአንድ ከባድ ግድያ አቃቤ ሀግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡
ተከሳሾች #ተከላካይ_ጠበቃ በግላቸው ማቆም እንደማይችሉና መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ለፍርድቤቱ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ፍርድቤቱም መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ፈቅዶ ለመጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም የክስ ሂደቱን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

#update በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት የሟቾች ቁጥር 5 ደረሰ፤ አንድ የፖሊስ አባልም የደረሰበት አልታወቀም፡፡ ትናንት በግምት ከቀኑ 7-8፡00 ባለው ጊዜ በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት ግጭት መቀስቀሱና የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ቀደም ብሎ ተዘግቦ ነበር፡፡ ዘግይቶ በወጣ መረጃ ደግሞ በግጭቱ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል፤ የሟቾች አስከሬንም ለቤተሰቦቻቸው ተሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንድ የፖሊስ አባል እስካሁን #አልተገኘም፡፡ የተንቀሳቃሽ ስልኩ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ መገኘቱንና የፖሊስ አባሉ ግን እስካሁን ያለበት ሁኔታና ቦታ አለመታወቁ በማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር #ውብሸት_መኮንን ተገልጿል።
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንነው ረሳናቸው❓
(ጌዲኦ-ኢትዮጵያ)
በቡድን ተከፋፍለን፤ ህይወታችንን በማይቀይሩ አጀንዳዎች ተጠምደን ስንቱን ስንባባል የምንውል ሰዎች ምነው ስለነዚህ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን ለመናገር አፋችን ተለጎመ?
ሰው ነኝ የምንል ሁሉ፤ኢትዮጵያዊ ነኝ የምንል ሁሉ ምንነው ታዲያ እነዚህ ምስኪን ወገኖቻችንን ዞር ብለን ማየት አቃተን?
በማዕበራዊ ድረገፅ በማይረቡ እና ህይወታችንን በማይቀይሩ ወሬዎች ላይ አስተያየት ስንሰጥ የምንውል ሰዎች ምነው እነዚህን ምስኪን ወገኖቻችን ረሳናቸው?
ምነው ከመንጋው ተነጥለን፤ እንደሰው አዝነን ስለነዚህ ሰዎች ችግር እና መከራ ብንነጋገር፤ ሰውነትን መርሳትስ ተገቢ ነው? ነገስ የኛ መውደቂያ የት እንደሆነ እናውቅ ይሆን?
ወገኖቼ ተኝተናል እንንቃ!
አካሄዳችን ሊታረም ይገባል!
አመለካከታችን ሊታረም ይገባል!

ጌዲኦ❓
በጌዲኦ ዞን #ገደብ እና #ጎቲቲ ወረዳዎች በርካታ ተፈናቃዮች ያለ ምግብ እና ህክምና #እርዳታ በስቃይ አሉ። በህክምና እጦት 15 ህጻናት #የአይናቸውን_ብርሃን አተዋል። አብዛኞቹ በመጠለያ እና በምግብ እጦት #በመሰቃየት ላይ ናቸዉ። የተራድኦ ድርጅቶች እርዳታ ማቅረብ #አልቻልንም ብለዋል። ወቅቱ የዝናብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቸግሩን የከፋ አድርጎታል።
Via Bisrat Melese