TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሴትነት!

#ሴትነት ሰው የመሆን ሁለንተናነት ነው። አንድ ሰው የሴትነትን ታላቅነት ካልተረዳ ገና #ሰው የመሆንን ሚስጢር አልተገነዘበም ማለት ነው። ምክንያቱም ሴት እናት ነች። እናት ደግሞ የማያልቅ ዘላለማዊ ፍቅርን በስስት የምትለግሰን #የፍቅርን ምንነት መገለጫ ናት። ታዲያ ከፍቅርና ፍቅርን ከማወቅ በላይ ምን ታላቅ የህይወት ሚስጢር ይኖራል? ምንም አይኖርም።

ሌላው ታላቅ ከሚያደርጓት ነገሮች ደግሞ በህይወት ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተጋፍጣ #በብልሃት እና #አሸናፊነት የምትወጣ ጠንካራ ፍጥረትነቷ ነው።

ሩህሩህነትን ከአፍቃሪነት ጋር ታድላ የተፈጠረች ለወንድ የህይወቱ ማገር እና ምሶሶ ናት። ወንድ ያለ ሴት ሙሉነት እና የህይወት ጣእም የሌለው ያላለቀ የእግዜር ጅምር ስራ ነው።

ሴት ልጅ ስቃይዋን እና ሃዘኗን መደበቅ ካስፈለጋት መከፋትዋን ሳታሳይ ደስተኛ በመምሰል ለምትወደው ሃሴትን መስጠት የምትችል ረቂቅ ፍጠረት ናት።

ሴትነትን ሆነው ካላዩት በእርግጥ ስለ ሴትነት ሙሉ በሙሉ መናገር የሚቻለው አይኖርም። ረቂቅ እና የህይወት ጣእም ሚስጢር አድርጎ ከፈጠራት ፈጣሪ በስተቀር።

ሴት ልጅ ከወንድ የጎን አጠንት ብትሰራም በህይወት ዘመኑ የጀርባ አጥንቱ ሆና ብርታትን እና ፀናትን የምትሰጠው “ሃይል” ናት። የታላላቅ ስኬቱ ጀንበር ሆና የምትፈነጥቅለት ነገር ግን ከእርሱ ልቃ የማትታይ የመድመቂያው ጮራ መፍለቂያ ናት።

ሴት ልጅ ከልብ የመነጨ ክብር ይገባታል። ሴትን የሚያከበር ራሱን #የሚያከብር ነው። ሴትን የማያከብር ቢኖር የህይወትን ጣእም እና ፍቅርን ካለማወቁም በላይ ሰው የመሆን ብቃት የጎደለው ነው።

ምንጭ ፦ ደንቢያ(ከማህበራዊ ድረ ገፅ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia