TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሳይንስ እና ቴክኖ. ዩኒቨርሲቲ⬇️

አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ሊሰጥ ነው።

በ2011 #የአዳማና #የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ‘#በቀጥታ’ በበይነ መረብ ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኙት የአዳማና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለ2011 የትምህርት ዘመን የመሰናዶ ትምህርት ጨርሰው #ከፍተኛ ውጤት ያመጡትና ለፈተና ከቀረቡት 4 ሺህ 700 ተማሪዎች መካከል በፈተና በማወዳደር 3ሺህ ተማሪዎች ሊቀበል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፈተናው #ረቡዕ ነሃሴ 30፣ 2010 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ 11፡00 ድረስ በተለያዩ ክልሎች ባሉ 37 ዩኒቨርስቲዎች በቀጥታ በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፥ የመግቢያ ውጤቱ ለታዳጊ ክልሎች፣ ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ዝቅ እንዲል ተደርጓል ተብሏል፡፡

ፈተናው ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ሂሳብና ኢንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶቸን የሚያካትት ሲሆን፥ ዝቅተኛው የማለፊያ ውጤት ከ50 በላይ ሁኗል ተብሏል፡፡

ፈተናው በበይነ መረብ ከአንድ ማዕከል የሚተላለፍ ሲሆን፥ የወረቀት ብክነትንና የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደረግ ነው የተገለጸው፡፡

ታላላቅ ድርጅቶች ብዛት ያለው የሰው ሀይል ለመቅጠር በፈተና ማወዳደር በሚፈልጉበት ጊዜ ይህንን ስርዓት በመጠቀም ፈትነው ለቃለመጠይቅ ብቻ የሚፈልጉትን ሰው በመጥራት መቅጠር እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ይህንን የፈተና ስርዓት መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛውንም አካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርበኞች ግንቦት 7⬇️

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ #መቀሌ#አዳማና #አዲስ አበባን ጨምሮ በ32 ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ተገለጸ፡፡

ከአቀባበል ኮሚቴ በተገኘው መረጃ እሁድ ጳጉሜ 4/2010 ብርሀኑ ነጋን (ፕ/ር) ጨምሮ አመራሮቹ ኢትዮጵያ እንደገቡ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሕዝቡ ንግግር ያደርጋሉ፤ የስታዲየሙ ንግግር በኢሳትና ሌሎች ቴሌቪዥን ጣቢያዎች #በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል፡፡ በስታዲየሙ የሚገኘውን የሕዝብ መጨናነቅ ለመቀነስ በመስቀል አደባባይ በስክሪን ንግግሩ ይተላለፋል፡፡

መስከረም 6 እና 7 በባሕርዳር እና ጎንደር፣ መስከረም 12 በአዳማ አመራሮቹ የሚገኙበት ሕዝባዊ ትዕይንት ከተካሄደ በኋላ በተከታታይ ቀናት #በመቀሌ#ወልዲያ#ደሴ እና #አምቦ ተመሳሳይ ፕሮግራም ይኖራል፡፡

ንቅናቄው አቀባበሉን በተመለከተ ትናንት በሰጠው መግለጫ “በዕለቱ ሥነ ሥርዓት ለማስከበርና የሕዝብን ደሕንነት ለመጠበቅ ከተሰማሩ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ታሪካዊ የአቀባበል በዓሉ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲካሄድ” ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፓሪሱ ጥቃት⬇️

ፈረንሳይ በመዲናዋ በሰኔ ወር የፈነዳውን ቦምብ #ያቀነባበረው የኢራን የደህንነት
መስሪያ ቤት መሆኑን አረጋግጫለው አለች፡፡

በወቅቱ በፓሪስ ጎዳና ላይ ከኢራን የተሰደዱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንደነበሩ ተነግሯል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፈረንሳይ የሁለት #ኢራናውያንን እና ከሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ጋር የተያያዙ የባንክ አካውንቶችን አግዳለች፡፡

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘም ረዥም ጊዜ የፈጀ ምርመራ ካካሄደች በኋላ ነው ይፋ ማድረጓን ያስታወቀችው፡፡

የኢራን የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ የሆኑት ሰይድ ሐሺም #በቀጥታ ትዕዛዙን እንደሰጡ ተገልጿል፡፡

የደህንነት መስሪያ ቤቱ ቃልአቀባይ ፓሪስ የደረሰችበትን ምርመራ ተቀባይነት የለውም ያሉ ሲሆን በጀርመን ተያዙ ተያዙ የተባሉ ዲፕሎማታቸውንም እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ጥቃቱ የተፈጸመው የሁለቱ ሀገራትን የረዥም ጊዜ ወዳጅነት በማይፈልጉ ሴረኞች የተቀነባበረ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia