TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

#የማታለል_ወንጀል የፈጸመው የዓባይ ባንክ ሠራተኛ በእስራትና ገንዘብ ተቀጣ። ተከሳሽ በረከት በርሄ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 696/ሐ የተመለከተውን ክልከላ በመተላለፍ አባይ ባንክ አክሲዮን ማህበር ለሰራተኞቹ የሚሰጠውን የቤት መግዣ እና የመስሪ ቦታ ብድር አገልግሎት ለመጠቀም በማሰብ በሌላ ሰው ተመዝግቦ የሚገኝን መኖሪያ ቤት እንደ መያዣ አድርጎ በማቅረብ 656,774 ብር ከባንኩ ወስዷል፡፡

ተከሳሽ ማስገመት የሚገባው የመኖሪያ ቤት ዋጋ 441,696.87 ብር ሆኖ ሳለ ባንኩን በማሳሳት የሌላ ሰው የሆነ ቤትን በ656,774 ብር በማሰገመት ባንኩ 173,235 ብር እንዲያጣ ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው ከባድ የማታለል ወንጀል ተከሷል፡፡

ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ ያስረዱልኛል ያላቸውን ማስረጃዎችን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎትም የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በ3 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ17,000 ብር እንዲቀጣ ወስኗል።

ምንጭ፦ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia