TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሶማሌ ክልል‼️

መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም የሚጀመረው #ሦስተኛው_ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ በተሳካ መልኩ እንዲከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሶማሌ ክልል ገለጸ፡፡ የህዝቦች አንድነትንም ሆነ የሕግ የበላይነትን የማይፈልጉ #የመገንጠል አጀንዳ ያላቸው ኃይሎች ክልሉን መጠቀሚያ ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሙስጠፋ_ሙሐመድ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ የህዝብና ቤት ቆጠራው ዋና ዓላማ ህዝብ እንዲቆጠር ማድረግ ነው፡፡ የፌዴራል መንግስቱም ከዚህ የተለየ ዓላማ እንደሌለው ስለሚታወቅ ለቆጠራ መሳካት እንደ ክልል ከፌዴራል መንግስት ጋር በትብብር እንሰራለን፡፡ ለዚህም በድንበር አከባቢ ሊፈጠሩ ይችላሉ የሚባሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ እያስቀመጥን እንገኛለን፡፡

ይሁን እንጂ ቆጠራውን አጀንዳ ማድረግ የሚፈልጉ፤ ገና ምንም ሳይቆጠር ቁጥራችን ሊቀነስ ነው፤ እንዲህ ታስቧል፤ እንዲህ ተደርጓል፤ እያሉ #ውጤቱን ከአሁኑ ለመወሰንና የክልሉን አስተዳደር አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት የሚሞክሩ ሃይሎች አሉ፡፡ ክልሉ ግን አስተማማኝና ሊታመንበት የሚችል ሂደትን በመከተል፤ ምክንያታዊ የሆነ ውጤት እንዲመጣ ለማስቻል እየሰራ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል፣ በክልሉ ያለው አዲስ አመራር ለህዝቡ የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እየሰራና #ለውጡንም የህዝብ ጥቅም ማስጠበቂያ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ አንዳንድ ሃይሎች ግን ክልሉን የመጥፎ ሀሳባቸው ማስፈጸሚያ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ ሃይሎች ደግሞ የዚህን ክልል ህዝብ ሲገድሉና ሲጨፈጭፉ፤ የክልሉን በጀት ከክልሉ አመራር ጋር ሲመዘብሩ የነበሩ ጥቂት ጄኔራሎች እና የእነርሱ የፖለቲካ ነፍስ አባቶች ሲሆኑ፤ ይሄ ተግባር ደግሞ የመገንጠል ዓላማቸው ምዕራፍ ነው፡፡ የሶማሌ ክልል ሲረበሽ ‹ኢትዮጵያ ስለፈረሰች ምንም ማድረግ አይቻልም እኛም እንሂድ› የሚል አመለካከት ስላላቸውም የሚፈጽሙት ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegawolde @tikvahethiopia