TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ወለጋ🔝

ጠ/ሚር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ከኦሮምያ ርዕሰ መስተዳድር #ለማ_መገርሳ ጋር በመሆን በምዕራብ ወለጋ የቄለም ወለጋ ዞን ካሉ ወረዳዎች አንዷ የሆነችው ቤጊ ወረዳ የማኅበረሰብ አባላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ🔝

ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ስለማጠናከር፣ በሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ስለማስጠበቅና በሰላምና ደኅንነት ዙሪያ ተባብሮ ስለመሥራት ተወያይተው ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሴ በበኩላቸው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለቀጣናው ውሕደት የወሰዷቸውን ርምጃዎች በማንሣት አስተዳደራቸው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በይብልጥ ተቀራርቦ አብረው እንዲሠሩ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበሉ ገልፀዋል። በተጨማሪም ወደፊት በጋራና በተናጠል ቀጣይ ውይይቶችን ለማካሄድ ተስማምተዋል። ሲያጠቀልሉም ሁለቱ ወገኖች ስለ ወደብ አጠቃቀምና ሌሎችም የኢኮኖሚ ትሥሥር ላይ ተወያይተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia